አቶ በቀለ ሙለታ (በግራ)፣ አቶ አድማሱ ዳምጠው (በቀኝ)

ከሥልጣናቸው የተነሱት አቶ በቀለ ሙለታ (በግራ)፣ እንዲሁም አዲሱ ተሿሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው (በቀኝ)

በምትካቸው አዲስ ተሿሚዎች ተተክተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 25, 2020)፦ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ለአንድ ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አቶ በቀለ ሙለታና ምክትላቸው አቶ ብሩክ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በአዲስ ተተክተዋል።

ከነኀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሁለቱም ከፍተኛ የተቋሙ ኃላፊዎች ከኃላፊነተአቸው የተነሱበት ምክንያት እስካሁን ግልጽ ባይኾንም፤ እነርሱን ተክተው አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ኃላፊነቱን ተረክበዋል ተብሏል።

አቶ በቀለን ተክተው የፋና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመኾን የተሾሙት፤ የቀድሞው የኦሮሚያ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ናቸው ተብሏል።

በምክትል ሥራ አስፈጻሚነት ደግሞ የአማራ ብዙኃን መገናኛ የአዲስ አበባ ቢሮ ኃላፊ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሰጠኝ እንግዳ ስለመሰየማቸው የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገልጸዋል።

ተሰናባቹ አቶ በቀለ ፋናን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ ከመሰየማቸው በፊት የኢዜአ (የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት) ሥራ አስኪያጅ ነበሩ።

በአሁኑ ወቅት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ