ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የስንብቱን ደብዳቤ የጻፉት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 7, 2020)፦ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባልነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁና ይህንንም ጥያቄያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ዶ/ር ጌታሁን ካሣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸው ተገለጸ።

እንደምጮች ገለጻ፤ ዶ/ር ጌታሁን ከቦርድ አባልነታቸው በይፋ መሰናበታቸውን የሚያረጋግጠው ደብዳቤ የተጻፈላቸው ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ነው።

ዶ/ር ጌታሁን ከቦርድ አባልነታቸው የለቀቁበትን ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም፤ የማልስማማባቸው ነገሮች አሉ በሚል በደፈናው አስተያየት መስጠታቸው ይታወሳል። ስለምክንያታቸው እየተሰራጩ ካሉ ወሬዎች ውስጥ፤ ምርጫ ቦርድ የኢሕአዴግን መፍረስ መፍቀድ የለበትም፤ የኢሕአዴግ መፍረስ አገር ያፈርሳል ብለው ተከራክረው እንደኾነ ተደምጧል።

በጥያቄያቸው መሠረት ዶ/ር ጌታሁን በይፋ የተሰናበቱበት ደብዳቤ ግልባጭ ለሚመለከታቸው አካላት ተልኳል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ