ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም

የሰሜን ዕዝ አዛዥ በመኾን የተሾሙት ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም

የሕወሓት ደጋፊዎች ዛቻዎች እየሰነዘሩ ናቸው

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 29, 2020)፦ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አራት የነበሩትን ዕዞች ወደ ስድስት በማሳደግ እንዲዋቀር ካደረገ በኋላ፤ መቀመጫውን መቀሌ ላደረገው የሰሜን ዕዝ አዲስ አዛዥ ተሾመ።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሰሜን ዕዝ አዛዥ በመኾን የተሾሙት ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም ናቸው። ሜጀር ጄኔራል በላይ ስዩም የምሥራቅ ዕዝን በአዛዥነት ይመሩ እንደነበር ታውቋል።

ይህ ሹመት የተሰጠው ባለፈው ሳምንት ሕወሓት ሰሜን ዕዝን በተመለከተ አነጋጋሪ የተባለ መግለጫ በሰጠ ማግስት ነው።

ሕወሓት የሰሜን ዕዝን በተመለከተ አውጥቶት በነበረው መግለጫ፤ በሰሜን ዕዝ ምንም ዐይነት የአመራር ለውጥ አይደረግም የሚል ነበር። እንዲሁም በትግራይ ክልል ያለው የሰሜን ዕዝ ሠራዊት መሣሪያ ማንቀሳቀስ አይችልም የሚለው መግለጫ፤ ከትግራይ ክልል የሰሜን ዕዝ መሣሪያ የሚንቀሳቀስ ከኾነ ለሚፈጠው ችግር ኃላፊነት አንወስድም ብሏል።

ይህ የሕወሓት መግለጫ ብዙ እያነጋገረ ሲሆን፤ የአዲሱ የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሹመትን ተከትሎም የሕወሓት ደጋፊ ናቸው የተባሉ የማኅበራዊ ገጾች ላይ የተለያዩ ዛቻዎች እየተሰነዘሩ ነው።

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ሁለት አዳዲስ ዕዞችን በማከል ቁጥሩን ወደ ስድስት ሲያሳድግ፤ አዲስ የተደራጁት ሁለቱ ዕዞች “ሰሜን ምዕራብ ዕዝ” እና “ማዕከላዊ ዕዝ” በመባል የሚጠሩ ናቸው።

ሰሜን ምዕራብ ዕዝ መቀመጫውን ባሕር ዳር የሚያደርግ ሲሆን፤ ማዕከላዊ ዕዙ ደግሞ መቀመጫውን አዲስ አበባ እንደሚኾን ተጠቅሷል።

ወደም ብለው የነበሩት የሰሜን፣ የደቡብ፣ የምሥራቅ እና የምዕራብ ዕዞች ሲሆኑ፤ እነዚህ ዕዞች እንደቀድሞው ባሉበት ሥራቸውን የሚቀጥሉ ይኾናል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ