ሲሳይ ፊዳ

ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ

ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ የተገደለው በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ አስፍጠው ሲጠብቁት በነበሩ ሁለት ታጣቂዎች ነው

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 10, 2021)፦ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) የምሥራቅ ወለጋ የራዲዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ትናንት በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው ሸማቂ ቡድን መገደሉ ተሰማ።

በቄለም ወለጋ ዞን የኦቢኤን ራዲዮና ቴሌቭዥን ቅርንጫፍ ጋዜጠኛ ሲሳይ ፊዳ ግድያው የተፈጸመበት በድንቢዶሎ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ ትናንት እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ማምሻውን 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው።

የቄሌም ወለጋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፤ የጥቃቱ አድራሾችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ሲል፤ ኦቤኤን ደግሞ የዞኑን ፖሊስ ጠቅሶ እንደዘገበው ጋዜጠኛው የተገደለው ከሰርግ ሲመለስ በመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ አድፍጠው ሲጠብቁት በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ነው። የጥቃቱ አድራሽም ሸኔ እንደኾነም ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል ለቤተሰቦቹ፣ ለዘመድ አዝማዶቹ፣ ለዘመድ አዝማዶቹና ለሥራ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ