ሐሰተኛ የብር ኖቶች እና ሕገወጥ መሣሪያዎች

በግለሰቡ ቤት የተያዙት ሐሰተኛ የብር ኖቶች እና ሕገወጥ መሣሪያዎች

ግለሰቡ ተሰውሯል

ኢዛ (ሰኞ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 17, 2021)፦ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአንድ ግለሰብ ቤት 112 ሺህ ብር ሐሰተኛ የብር ኖቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የፃግብጂ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከፍተኛ በግለሰቡ ቤት ውስጥ 110 ሺው ሐሰተኛ ባለ ሁለት መቶ የብር ኖቶች ሲሆኑ፤ ሁለት ሺህ ብሩ ደግሞ የባለመቶ ብር ኖቶች ናቸው።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግለሰቡ በሚገኝበት ቀበሌ ሕገወጥ ድርጊት ለመፈጸም የተዘጋጀ ግለሰብ እንዳለ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ፍተሻ ሲደረግ ሐሰተኛ የብር ኖቶቹ ሊያዙ ችለዋል።

ኾኖም ድርጊቱን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ ፖሊስ ያልያዘው ሲሆን፣ ክትትል እየተደረገበት ነው ተብሏል። ከሐሰተኛ ገንዘቦቹ ሌላ አንድ ሽጉጥም በዚሁ ተፈላጊ ግለሰብ ቤት ውስጥ መገኘቱ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ