ወ/ር ብርቱካን ሚደቅሳ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የጣፉት ደብዳቤ

ወ/ር ብርቱካን ሚደቅሳ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የጣፉት ደብዳቤ

ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የሕግ አስፈጻሚ ኃይል ያስፈልጋል ብለዋል

ኢዛ (ቅዳሜ ሰኔ ፲፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 19, 2021)፦ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫን (ምርጫ 2013) ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ተጠባባቂ የሕግ አስፈጻሚ ኃይል የምርጫ ቦርድ ለሚጠይቃቸው ጥያቂዎች ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መመሪያ እንዲያስተላልፉ የምርጫ ቦርድ ጠየቀ።

ትናንት የተጻፈውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ይዞ ያደረገው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈው ደብዳቤ፤ “የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ የሚያስፈልግ ተጠባባቂ የሕግ አስፈጻሚ ኃይል ለዚህ አገራዊ ሰላማዊ እና ሕጋዊ ኦፐሬሽን ቅድሚያ በመስጠት ፍጥነትና የተላበሰ ምላሽ ለቦርዱ ጥያቄዎች እንዲሰጡ አስፈላጊውን መመሪያ ያስተላልፉ” ብሏል።

ቦርዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያውን እንዲያስተላልፉ የሚል ጥያቂውን ያቀረበው በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 161 መሠረት ስለመኾኑም በወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ተፈርሞ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላከው ደብዳቤ ያመለክታል።

ቦርዱ ከዚህ ጥያቄው ባሻገር በተለያዩ ጥቂት ቦታዎች ላይ ሳንካዎች ቢገጥሙ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድ በማንኛውም ተቋም ሥር የሚገኝ የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ አቅም ለማግኘት መንግሥት የሚያግዝበት ሁኔታ እንዲመቻችና ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመሪያ እንዲሰጡ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጠይቀዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ