በዓቃቤ ሕግ ሞት ይገባዋል የተባለው የጀኔራል ሳዕረ ገዳይ በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ
አሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ
የመታሰቢያ ሐውልታቸው ተጠናቀቀ
ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 28, 2021)፦ በሞት እንዲቀጣ ዓቃቤ ሕግ ጥያቄ ያቀረበበት በቀድሞ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳዕረ መኮንን ግድያ የተከሰሰው አሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፤ በዕድሜ ልክ ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ ተወሰነ።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት በዓቃቤ ሕግ የቀረበውን የሞት ቅጣት በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት በመለወጥ ውሳኔውን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ የሰጠው አሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ አራት የቅጣት ማቅለያ በማቅረቡ፤ ቅጣቱ በዕድሜ ልክ እሥራት እንዲቀልለት ኾኗል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጄኔራል ሳዕረ መኮንን እና የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት ሥራ መጠናቀቁንና በቅርቡ እንደሚመረቅ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳመለከቱት የመታሰቢያ ሐውልቶቹን አስተዳደሩ የገነባቸውና በቅርቡ የሚመረቁ ስለመኾኑም አመልክተዋል። (ኢዛ)



