House of Peoples’ Representatives of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የአገር መከላከያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ዴኤታዎች ለፓርላማው ማብራሪያ ሰጥተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 29, 2021)፦ ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጣሊያን መንግሥታት ጋር በመከላከያ ረገድ ተባብሮ ለመሥራት የሚያስችለው ረቂቅ ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።

ከሁለቱ አገራት ጋር የመከላከያ የትብብር ስምምነት የአገር መከላከያ ሠራዊትን አቅም ለማሳደግና ከሁለቱ አገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ከማጠናከር በላይ ያሉትን ጠቅሜታዎች ለፓርላማው ከቀረበ በኋላ በረቂቁ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ተወስኗል።

በዚህ ረቂቅ ጠቀሜታ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ የሰጡት የአገር መከላከያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ዴኤታዎች ናቸው።

ዛሬ የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለፓርላማ የተመራ መኾኑን መዘገባችን አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ