Birtukan Mideksa

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

ውጤቱን የሚቀይር ቅሬታ ካለ ዳግም ምርጫ ይደረጋል

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 29, 2021)፦ በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ተወዳዳሪ የኾኑ የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫው ወቅት በ160 የምርጫ ክልሎች አጋጠመን ያሉትን ቅሬታዎችን ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ገለጸ።

ሰብሳቢዋ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ቦርዳቸው በ160 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የፖለቲካ ድርጅቶች ያቀረቡትን ቅሬታ ተቀብሏል።

ቦርዱ እነዚህን ቅሬታዎች በፍጥነት እንደሚፈታ በማመልከትም፤ በማጣራቱ ሒደት ላይ የምርጫውን ውጤት ሊለውጡ የሚችሉ ካሉ በድጋሚ ምርጫ ሊካሔድ የሚችልበት የምርጫ ክልሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመው ይህም በሕግ የተቀመጠ ነው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ የመጨረሻ ውጤቱን ሊያዘገየው ይችላል የሚል ሥጋት እንደሌላቸውም አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ግን የምርጫ ቦርድ ውጤቱን በቶሎ እንዳይገለጽ እንደማነቆ ኾኖ የያዘው በርካታ አቤቱታዎች በፓርቲዎች በኩል በመቅረቡ መኾኑንም የቦርዱ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሳይመለከቱ አላለፉም።

ይህም ኾኖ ግን የተረጋገጡ የምርጫ ክልሎች እና አነስተኛ ቅሬታና አቤቱታ የቀረቡባቸውን የምርጫ ክልሎች ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ቶሎ ቶሎ ይፋ ማድረግ እንደሚጀምር አመልክቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ