አትሌት ቀነኒሳ በቀለ Kenenisa Bekeleቀሪዎቹን ሁለቱን ካሸነፈ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ተቋዳሽ ይሆናል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2001 ዓ.ም. July 17, 2009)፦ እ.ኤ.አ. የ2009ኙ ጎልደን ሊግ አራተኛ ውድድር በፓሪስ ፈረንሣይ እየተካሄደ ሲሆን፣ ይህ ዜና ከመጠናከሩ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ3000 ሜትሩን ውድድር በ7 ደቂቃ ከ28፡64 ሰከንድ በመጨረስ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቅቋል። ከዚህ በኋላ የሚደረጉትን ሁለት ውድድሮች በአሸናፊነት ካጠናቀቀ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ጃክ ፖት ተቋዳሽ ይሆናል።

 

ከአትሌት ቀነኒሳ በተጨማሪ በፉክክሩ እስካሁን ሳይበገሩ የተገኙት ሦስት ሴት አትሌቶች ናቸው። በምሩክዝ ዝላይ ሩሲያዊቷ ይሌና ኢሲንባዬቫ፣ በ100 ሜትር ሴቶች ጃማይካዊቷ ኬሮን ስትዋርት እና በ400 ሜትር ሴቶች ሳኒያ ሪቻርድስ ከቀነኒሳ ጋር ለአንድ ሚሊዮን ዶላሩ እየተፎካከሩ ያሉ አትሌቶች ሲሆኑ፤ በዛሬውም ውድድር ሦስቱም ሴት አትሌቶች አራተኛ ድላቸውን ተቀዳጅተዋል።

 

ቀሪዎቹ ውድድሮች በስዊዘርላንድ ዙሪክ ላይ አርብ ኦገስት 28 (ነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም.) እንዲሁም የመጨረሻው ውድድር ቤልጅየም በረስልስ ላይ አርብ ሴፕቴምበር 4 (ነሐሴ 29 ቀን 2009 ዓ.ም.) ይካሄዳሉ።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ