በጀርመን፣ ፍራንክፈርት የተደረገው ሰላማዊ ስልፍ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ

ዮሐንስ ደሳለኝ - (ጀርመን)

Ethiopia Zare ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2007 ዓም January 17, 2015:- ባሳለፍንው ሰኞ በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዩጽያዊያን በአሁኑ ሰዓት በአገራቸው የሚደረገውን የመብት ጥሰት ለተለያዬ ተቁማት ለማሳወቅ ሁለት ሰዓት የፈጀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። መነሻውን ከዋናው የባቡር ጣቢያ አንድ ጣቢያ (station)አልፉ በሚገኘው ታውንስላገን አካባቢ ከዋናው ደች ባንክ አጠገብ ያደረገው ሰልፍ፣ ረፈዱ 11፡00am ላይ ተጀምሮ የእንግሊዝ ኤምባሲን አካሎ ምሳ ሰዓት ላይ (1፡00pm) ፍራንክፈርት የሚገኘው ኢትዬጽያ ቆንጽላ ጽ|ቤት በመገኘት በተለመደው ኢትዬጵያዊ ጨዋነት ተጠናቁል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በበርሊን ከተማ ደማቅ የተቃውሞ ስልፍ ተደረገ

ዮሃንስ ደሳለኝ (በርሊን -ጀርመኒ)

Ethiopia Zare ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2007 ዓም December 4, 2014  ከደች ባንክ ብድር ለመጠየቅ ረቡዕ ለታ ከጀርመኗ ቻንስለር መርከል ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በቦታው በመገኘት ተቃውሟቸውን ማስማታቸው ታወቀ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ

Hailu Gebreyohannes Gemoraw ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) "... እንደ ኪሩብ ሁሉ - ክንፍ አካል ቢኖረኝ፣
መች እጠበስ ነበር - በዚህ ዓለም በቃኝ፣
ስላጣሁ ብቻ ነው - መሸሻ መድረሻ፣
በዚች በሽት ዓለም - የኖርኩ እንደውሻ ...፣"
"... በሥጋዬ ብቻ ውጪ - ሀገር እስካለሁ፣
እወቁልኝ በርግጥ - አልኖርኩም ሞቻለሁ! ...
ኃይሉ (ገሞራው)
Ethiopia Zare (ረቡዕ ኅዳር 3 ቀን 2007 ዓ.ም. November 12, 2014):- በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታዋቂ የነበረው ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) ባለፈው እሁድ ጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. (ኖቨምበር 9፣ 2014) በስደት በሚኖርባት ስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በ71 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ተለየ። ሥርዓተ ቀብሩ በስዊድን እንደሚፈፀም ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድነት ፕሬዘዳንት የተመራ የልዑካ ቡድን የፖለቲካ እስረኞችን ጠየቀ

ፍኖተ ነፃነት

በዛሬው ዕለት ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩትን የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ስፍራው በማምራት አቶ ሀብታሙ አያሌውን፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺንና ሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችን ማነጋገራቸውን ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሲድኒ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ልዩ ክብር ሰጡ

ደማቅ ውይይትም አድርገዋል

አቢይ አፈወርቅ
Prof. Mesfin Woldemariam in Sydney, 26 October 2014

ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስራ አንድ ጋዜጠኞች ተሰደዱ

የገዥው ፓርቲ ቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ
(ከላይ ከግራ ወደቀኝ) ቶማስ አያሌው፣ ዳንኤል ድርሻ እና ግዛው ታዬ፣ (ከታች) ሰናይ አባተ እና አስናቀ ልባዊ (Top, left to right) Thomas Ayalew, Daniel Dirsha and Gizawe Taye. (Bottom, left to right) Senay Abate and Asnake Lebawi

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. August 23, 2014)፦ በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. "የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል" በሚል በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የደብረ ታቦር በዓል ተከበረ

በስዊድን፣ ስቶክሆልም የደብረ ታቦር በዓል ተከበረ በመድኃኒዓም ቤተክርስቲያን ሲከበር፣ ማክሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2006 ዓ.ም. Demera in Stockholm, Sweden

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. August 20, 2014)፡- በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሚገኘው የደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የደብረታቦር በዓል በደማቅ ሁኔታ በትናንትናው ዕለት ተከበረ። ጸሎትና ትምህርቱ በኃይማኖት አባቶች ለምዕመናኑ ከተሰጠ በኋላ፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት (19፡00 ሰዓት) ላይ የበዓሉ መገለጫ የሆነው ችቦ በርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ የተመሰረተባቸው ክስ ደረሳቸው

የዐቃቤ ሕግ የመሰረተውን ሙሉ ክስ ይዘናል
የዋስትና መብት ተከልክለው ወደቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ፣ ለሐምሌ 28 ተቀጠሩ
የታሰሩት ስድስት ጦማርያንና ሦስት ጋዜጠኞች The jailed 6 bloggers and 3 journalists

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. July 17, 2014)፡- ዛሬ ጠዋት በ84 ቀናቸው በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰየመ ችሎት ስድስቱ ጦማርያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ እና ሦስቱ ጋዜጠኞች አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ዐቃቤ ሕግ የመሰረተባቸው የክስ ፋይል ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሷቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ