የአንድነት ፀሎት ጥሪ ለቴዲ አፍሮ
Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) አብሮ አደግ የሆኑትና የቤተልሔም ት/ቤት ተማሪዎች በየእምነታቸው በጾምና በፀሎት ሊያስቡት ማቀዳቸውን ገልጸው፣ በጾምና በፀሎቱ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች፣ ዘመድና ወዳጆች በያሉበት በመሆን ዘር፣ ፖለቲካ፣ ኃይማኖት ወደማይለየው ፈጣሪያቸው ይማፀኑ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።






