እንኳን ለ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. አደረስዎ!

Ethiopia Zare (ኀሙስ መስከረም ፩ (1) ቀን ፳፻፩ (ለ2001) ዓ.ም. September 11, 2008)፦ በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር መስከረም ፩ (1) ቀን ፪፻፩ (2001) ዓ.ም. ተጀምሯል። እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማትዮስ በሠላም አሸጋገርዎ! አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የደስታ፣ የብልጽግና፣ ... ከነቤተሰብዎ ይሁንልዎ! ... በአዲሱ ዓመት በኢትዮጵያችን ዲሞክራሲ፣ ሠላም፣ ፍትህ፣ ... ይሰፍን ዘንድ፤ የዜጎች ሰብዓዊ መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት፣ ... ይከበር ዘንድ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከችግር፣ ከችጋር፣ ከረሃብ፣ ከሰቆቃ፣ ከስደት፣ ከእስር፣ ከስቃይ፣ ከመንገላታት፣ ከድብደባ፣ ከግድያ፣ ... ይድን ዘንድ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምኞት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢቲቪ የሥርጭት ሰዓቱን ሊጨምር ነው

ክልሎች ፕሮግራማቸውን በየክልላቸው ያደርጋሉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2000 ዓ.ም. September 09, 2008)፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት ከመስከረም 1 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሥርጭቱን ሊያራዝም መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ። የትግሪኛ እና የኦሮምኛ ፕሮግራሞች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በየክልላቸው ይደረጋሉ መባሉ ተቃውሞ አስነስቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመናኸሪያው ፍንዳታ የስምንት ሰው ሕይወት ቀጠፈ

Hanna Gosaye, age 20, victim of the explosion, 20080903ከምርጫ 97 ወዲህ በተከሰቱ 13 ፍንዳታዎች 36 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 200 ሰዎች ቆስለዋል

(ሪፖርታዥ)

Ethiopia Zare (እሁድ ጳጉሜን 2 ቀን 2000 ዓ.ም. September 07, 2008)፦ በአዲስ አበባ በአውቶቡስ ተራ አካባቢ "መናኸሪያ" ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው በተከሰተው አሰቃቂ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቅጥር ስምንት የደረሰ ሲሆን፣ በሃያ አራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሷል። አሰቃቂውን ፍንዳታ በሚመለከት ዝርዝር ዘገባ እንደሚከተለው ተጠናቅሯል።

 

ለአራት ዓመታት ወደሠራችበት ፎቶ ቤት ስታመራ ከወትሮው የተለየ ችግር ይገጥመኛል ብላ ያላሰበችው የ20 ዓመቷ ወጣት ሃና ጎሣዬ (በፎቶግራፉ ላይ የምትታየው)፣ ከመኖሪያ ቤቷ አቅራቢያ ወደሚገኘውና ለሀገር አቀፍ መናኸሪያ (አውቶቡስ ተራ) የተጠጋውና መርካቶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሥራ ቦታዋ “ፎቶ ሻርፕ” የሄደችው በእግሯ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ጋዜጦች አደጋ ውስጥ ናቸው

የሕትመት ዋጋ 50% ጨመረ

ሁለት ጋዜጦች ከገበያ ውጭ ሆኑ

Ethiopia Zare (ኀሙስ ነኀሴ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. September 04, 2008)፦ ከመስከረም ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ ስለምናደርግ ተዘጋጁ ሲል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ባለፈው ሣምንት ለደንበኞቹ በጻፈው ደብዳቤ ያሳውቃል። በሁኔታው የተደናገጡ ጋዜጦችም ምን ያህል ጭማሪ ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ባደረጉት ጥረት 100% ሊሆን እንደሚችል ይነገራቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መናኸሪያ አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ አራት ሞቱ፣ 21 ቆሰሉ

 (ተጨማሪ ዘገባ የታከለበት)

ወደ ሆስፒታሎች የተወሰዱትና ክፉኛ የቆሰሉቱ ለሕይወታቸው ያሰጋቸዋል

DS tvEthiopia Zare (ረቡዕ ነኀሴ 28 ቀን 2000 ዓ.ም. September 03, 2008)፦ አውቶቡስ ተራ አካባቢ መናኸሪያ ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው የዲ.ኤስ. ቲቪ ኳስ ማሳያ ቤት ውስጥ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ (በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር) በተከሰተ ከፍተኛ ፍንዳታ እስካሁን አራት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ሃያ አንድ የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውና በተለያዩ ሆስፒታሎች መወሰዳቸውን በሆስፒታል አካባቢ ሁኔታውን የሚከታተል የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጭ ጠቆመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 7 ለእንቁጣጣሽ ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨውን ራዲዮ ይጀምራል

Ginbot 7Ethiopia Zare (ማክሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. September 02, 2008)፦ በቅርቡ የተቋቋመው ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የሚቀጥለው ሣምንት ኀሙስ መስከረም 1 ቀን 2001 ዓ.ም. (September 11, 2008) በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት (8 P.M. / 20:00) ላይ ስርጭቱን በአማርኛ ቋንቋ እንደሚጀምር የንቅናቄው የህዝብ ግንኙነትና ቅስቀሳ ዘርፍ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፊፋ ኢትዮጵያን ለስድስት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች ያግዳታል

ኢትዮጵያ ለ2010 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሞሮኮ ጋር የምታደርገውን የማጣሪያ ውድድር እንዳትካፈል ታገደች

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ አዲሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር በተደጋጋሚ ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ቢሰጡትም፣ የፊፋን ውሳኔ ሳያሟላና ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት ለ2010 እ.ኤ.አ. የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ የታገደች ሲሆን፣ ምናልባትም ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች ልትታገድ እንደምትችል ፊፋ አስጠንቅቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“መንግሥት ሀገሪቱን ማስተዳደር ተስኖታል” የምክክር መድረክ

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ ከ14 ሚሊየን ህዝብ በላይ በረሃብ እየተገረፈና በአንዳንድ የሀገሪቱ ክልሎችም በድንበርና በመሬት ይገባኛል ጉዳዮች፣ በርካታ ዜጎች ደም አፋሳሽ ግጭቶች ውስጥ መግባታቸው፣ የመንግሥትን ሀገር የማስተዳደር ብቃት ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባ መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሪፖርተር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከስድስት ቀን በኋላ በዋስ ተለቀቀ

ሰኞ ጎንደር ፍ/ቤት ይቀርባል

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ ባለፈው ሣምንት ዓርብ ነኀሴ 16 ከቢሮው በፖሊሶች ከአዲስ አበባ የሪፖርተር ጋዜጣ ቢሮ ወደ ጎንደር የተወሰደው ጋዜጣው ባለቤትና ዋና አዘጋጅ አማረ አረጋዊ ረቡዕ ነኀሴ 21 ቀን 2000 ዓ.ም. ምሽት ላይ በስድስተኛ ቀኑ ከእስር በዋስ ተለቅቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...