ጥሩነሽ ዲባባ ሁለተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

Ethiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. August 22, 2008)፦ ዛሬ በቤጂንግ ኦሎምፒክ በተደረገው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ርቀት ፍፃሜ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አንደኛ በመውጣት ለራስዋ ሁለተኛውን፣ ለኢትዮጵያ ደግሞ ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። አትሌት መሠረት ደፋር ደግሞ ሦስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የነኀስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

አትሌት ቀነኒሳ ያሸነፈው የባለቤቱ ስም በተጻፈበት ጫማ ነው 




