የጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ አባት አረፉ
የሕይወት ታሪካቸውን ይዘናል (ተጨማሪ ዘገባ)
Ethiopia Zare (ኀሙስ ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. June 26, 2008)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ዜናዊ አስረስ ትናንት ረቡዕ ሰኔ 18 ቀን 2000 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ማረፋቸውን የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምንጮች ገለጹ።
የሕይወት ታሪካቸውን ይዘናል (ተጨማሪ ዘገባ)
Ethiopia Zare (ኀሙስ ሰኔ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. June 26, 2008)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወላጅ አባት የሆኑት አቶ ዜናዊ አስረስ ትናንት ረቡዕ ሰኔ 18 ቀን 2000 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ማረፋቸውን የአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምንጮች ገለጹ።
መሥራቾቹ ኢዲኃሕ፣ ኦፌዲን፣ ሶዲኃቅ፣ ዓረና፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና አቶ ስዬ አብርሃ ናቸው
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 17 ቀን 2000 ዓ.ም. June 24, 2008)፦ በዛሬው ዕለት በሀገር ውስጥ የሚገኙት የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረት (ኢዲኃሕ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዲን)፣ የሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ሶዲኃቅ)፣ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉዓላዊነት (ዓረና) የተሰኙት በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ፓርቲዎች ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር በመሆን “መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ” (መዲምኢ) በሚል ስያሜ አብረው ለመሥራት መስማማታቸውን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አቶ አባይነህ ወ/ት ብርቱካን የተሸለመችውን መኪና እንደሚያስመልሱ ገለጹ

Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. June 22, 2008)፦ በኢንጂንየር ኃይሉ ሻውል የሚመራው ቅንጅት/መኢአድ ለጉባዔተኛውና ለጋዜጠኞች በቅንጅት ስም ጉባዔውን ጠርቶ፤ ለአዲስ አባባ መስተዳድር ለስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደግሞ በመኢአድ (በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) ስም የስብሰባ ፈቃድ ጠይቆ፤ ዛሬ እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን በፕሬዝዳንትነት መረጠ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2000 ዓ.ም. June 21, 2008)፦ ዛሬ ረፋዱ ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም፣ ልዩ ስሙ ኦሽታ በተሰኘ ክፍለ ከተማ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ከህዝብ ጋር የሚያደርገውን ውይይት ከሰዓት በኋላ 14፡25 ሰዓት (ስምንት ሰዓት ከሃያ አምስት) ላይ ጀምሯል። በዚህ ህዝባዊ ውይይት ላይ የንቅናቄው መሥራቾች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ቸኮል ጌታሁን ተገኝተዋል።
ልዩ ጥንቅር - በአንድነት ፓርቲ ምስረታ ላይ
የመሪዎቹን አጭር ታሪክ/Profile ይዘናል

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. June 20, 2008)፦ ሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. በኢምፔሪያል ሆቴል ጠቅላላ ጉባዔ በማድረግ አመራር ለመምረጥ በዝግጅት ላይ የነበረው አንድነት ፖርቲ በዕለቱ ባይሳካለትም ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. በተለምዶ ሪቼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በድንኳን ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ተደርጓል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ በዛሬው ዕለት የተመረጡት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ከፍተኛ አመራሮች በፎቶግራፉ ላይ ከኋላ (ከግራ ወደ ቀኝ) አቶ ተመስገን ዘውዴ (ምክትል ሊቀመንበር እና የፋይናንስና የአስተዳደር)፣ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ (ምክትል ሊቀመንበር እና የህዝብ ግንኙነት)፣ አቶ አስራት ጣሴ (ዋና ፀሐፊ)፤ ከፊት (ከግራ ወደ ቀኝ) ኢንጂንየር ግዛቸው ሽፈራው (ምክትል ሊቀመንበር እና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ)፣ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ (ሊቀመንበር)፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም (ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ) ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወ/ት ብርቱካን የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆና ተመረጠች
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መሾሙ ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከፍተኛውን ድምፅ ያገኘችው ወ/ት ብርቱካን ነች
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 11 ቀን 2000 ዓ.ም. June 18 2008)፦ ዛሬ የተሰበሰበው የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ ስድሳ የላዕላይ ም/ቤት አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ በከፍተኛ ድምፅ በአንደኛ ደረጃ ስትመረጥ ኢንጂንየር ግዛቸው በሁለተኛ ደረጃ መመረጣቸው ታወቀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕ/ር ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል
ጉባዔው ነገ ረቡዕ 2፡30 ሰዓት ላይ ይጀመራል
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. June 17 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የመሥራች ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያስችለውን የስብሰባ ፈቃድ አገኘ። የሸምጋዮቹ ቡድን መሪ የሆኑት ፕ/ሮ ኤፍሬም ይስኃቅ ለፈቃዱ መገኘት ሚና ተጫውተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከሳሻቸው አቶ አየለ ጫሚሶ ነው
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. June 17 2008)፦ ዶ/ር ያቆብ ኃይለማርያም “አውራምባ ታይምስ” ከተሰኘው በሀገር ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ተንተርሶ በአቶ አየለ ጫሚሶ በተመሰረተባቸው ክስ ትናንት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርተው ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ በዋስ ተለቅቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...