ኢዴኃኅ መግለጫ አወጣ
ኢሕአፓ እና መድህን አልተገኙም
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. July 8, 2008)፦ መቀመጫውን በውጭ ሀገር ያደረገው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት (ዲዴኃኅ) በሜሪላንድ ከተማ በጠራው ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔ የድርጅቱን ቀጣይ ሂደት በሚመለከት ተወያይቶ መግለጫ አወጣ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ኢሕአፓ እና መድህን አልተገኙም
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2000 ዓ.ም. July 8, 2008)፦ መቀመጫውን በውጭ ሀገር ያደረገው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት (ዲዴኃኅ) በሜሪላንድ ከተማ በጠራው ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔ የድርጅቱን ቀጣይ ሂደት በሚመለከት ተወያይቶ መግለጫ አወጣ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. July 6, 2008)፦ በዋሽንግቶን ዲሲ ግንቦት 7 ንቅናቄ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ ከህዝብ ጋር ሰኔ 28 ቀን 2000 ዓ.ም. (ጁላይ 5 ቀን 2008) ባደረገው ውይይት ላይ አቶ ሙሉነህ እዩኤል "ኑ እንተባበር! ወቅቱ የሚጠይቀውን የትግል ስልት እንምረጥ፣ ሀገራችንንም ከጥፋት እንታደጋት" በሚል ርዕስ ንግግር አድርጓል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...15 ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Ethiopia Zare (እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. July 6, 2008)፦ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጓጓዙ መንገደኞች ከየሻንጣቸው ውስጥ ንብረቶቻቸው እንደሚጠፋባቸው ማማረር ከጀመሩ ቆየት ብሏል። ዝርፊያው ለስድስት ወር ያህል የዘለቀ ነበር። ብዙውን ጊዜ ንብረት ከጠፋባቸው መንገዶኞች መካከል ጠንከር ብሎ ጥያቄውን ያቀረበ ንብረቱ በገንዘብ እየተቀየረ ይከፈለዋል፤ የፈራና የጣልኩት ሌላ ቦታ ነው ብሎ የጠረጠረ ደግሞ እንደጠፋበት ይቀራል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የተጭበረበረ ሰነድ እንዲጣራ ለሣምንት ተቀጥሯል
ሁለት ጋዜጠኞች ታሰሩ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. July 4, 2008)፦ ዛሬ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን እንደሚፈታ በአዲስ አበባ ውስጥ ወሬ ሲናፈስ የሰነበተ ቢሆንም ብይኑ ለሣምንት ተቀጥሯል። በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ዶ/ር የተፈረመበት የሟች ደጉ ይበልጣል የሞት የምስክር ወረቀት ቴዲ ከተከሰሰበት ቀን ጋር ልዩነት በመፍጠሩ ዳኛው ዛሬ ብይን መስጠት ሲገባቸው እስኪጣራ ለሣምንት ቀጠሮ በመስጠት ችሎቱን መበተናቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።
አሳታሚዎቹ 300 ሺህ ብር መክፈል አለባቸው
"ግፊቱ ቢበዛብንም ሀገራችንን ለቀን አንወጣም" ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
"የሚመጣብንን ለመቀበል ዝግጁ ነን" ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና
Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. July 4, 2008)፦ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው ድርጅታቸው እንዲፈርስና በገደብ እንዲቀጡ የተወሰነባቸው አራት የጋዜጣ ድርጅቶች ውሳኔው ከተሰጠ ከ11 ወራት በኋላ በቅጣት የተወሰነባቸው ወደ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመንግሥት እንዲያስገቡ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ምንጮች ገለፁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ኀሙስ ሰኔ 26 ቀን 2000 ዓ.ም. July 3, 2008)፦ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ የመኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው የነበረው የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተለዋጭ ቤት በኪራይ መልክ ሊሰጣቸው እንደሆነ አስታወቁ።
ተጠርጣሪው ጓደኛው ነው
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሰኔ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. July 2, 2008)፦ ወጣት ደጉ ተስፋዬ ሰኔ 13 ቀን 2000 ዓ.ም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቅቆ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃውን ይዞ፣ ዕቃውን ሸክፎ መናኸሪያ ከደረሰ በኋላ፤ የሞባይል ስልኩ ጠፍቶበት ስለነበር ስልኩ መገኘቱን የሚገልጽ መልዕክት ደርሶት ወደ ግቢው ሲመለስ ነው ሦስት ቦታ በጩቤ ተወግቶ የተገደለው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...HAPI ከUNESCO እና ከUNOHCHR ጋር በመተባበር ነገ ጠዋት በረቂቅ አዋጁ ላይ ሴሚናር አዘጋጅቶ ነበር
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም. July 1, 2008)፦ ከአምስት ዓመት በፊት ኅዳር 25 1995 ዓ.ም. የተረቀቀውና፣ ጥር 5 ቀን 1995 ዓ.ም. (January 13, 2003) ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ተቃውሞ የቀረበበትና አፋኝ መሆኑ ሲነገርለት የነበረው አዲሱ የፕሬስ ሕግ ዛሬ በፓርላማው መጽደቁን ለኢትዮጵያ ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰው መረጃ ጠቆመ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
"ግንቦት 7 ንቅናቄን ሊቀላቀሉ ይችላሉ"
Ethiopia Zare (ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. June 30, 2008)፦ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የቀድሞ ፀሐፊ አቶ ሙሉነህ እዩኤል በትናንትናው ዕለት ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች አረጋገጡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አዲሱ/ተለጣፊው መምህራን ማኅበር የ12 ሚሊዮን ብር ሊወርስ ነው
Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. June 27, 2008)፦ ለሰላሳ ዘጠኝ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲንቀሳቀስና በአንድ ወቅት በዶ/ር ታዬ ወ/ሠማያት ይመራ የነበረው አንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ከ15 ዓመታት የፍርድ ቤት ሙግት በኋላ ለመጨረሻ ጊዜ በሰበር ችሎት እንዲዘጋ ተወሰነ። አዲሱ/ተለጣፊው የመምህራን ማኅበር ወደ 12 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወራሽ ሊሆን ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...