በሲያትል ዶ/ር ብርሃኑ ከህዝብ ጋር ያደረጉት ውይይት

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2000 ዓ.ም. May 12, 2008)፦ ትናንት በአሜሪካን ሀገር ሲያትል ከተማ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በከተማይቱና በአቅራቢያዋ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያኖች ጋር ህዝባዊ ውይይት ባደረጉበት ወቅት "ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረግ ትግል የግድ የሚለው የትብብር ጥያቄ" በሚል ርዕስ ረዘም ያለ ንግግር አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስደተኛውን ፓትርያርክ ዘገባ በተመለከተ አቋማችን፣ ዓላማችን እና መልሳችን

“የምናውቀውን እንናገራለን፣ ያየነውንም እንመሰክራለን”  ዮሐንስ ም. 3፥11

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም. May 10, 2008)፦ “የማይገለጥ የተከደነ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም” ይላል በስደት የሚገኘው ህጋዊ ሲኖዶስ ዜናችንን አስተባብሎ ባወጣው መግለጫ። ሚያዚያ 24 ቀን በኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ “ስደተኛው ፓትርያርክ ለእርቅ ወደ ኢትዮጵያ ሊሄዱ ነው” በሚል ርዕስ መዘገቡ አይዘነጋም። በጉዳዩ ላይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች በተለያዩ ድረ-ገጾች እና ራዲዮኖች የበኩላቸውን አስተያየት በመስጠት ዘገባው “ሐሰት ነው” ሲሉ አስተባብለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ብርሃኑ በቫንኩቨር የተሳካ ውይይት አካሄዱ

(ውይይቱን በድምፅ አቅርበነዋል)

'በሞኖፖል የተያዘውን የኢትዮጵያ ሚድያ ከውጭ ሃገር ሆኖ መስበር ይቻላል'  ዶ/ር ብርሃኑ

Dr. Berhanu, Vancouver public meeting 080510

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም. May 11, 2008)፦ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ትናንት ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2000 ዓ.ም. ከቫንኩቨር ነዋሪዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት የተሳካና ግልጽ ውይይት አካሄዱ። ውይይቱ የተጀመረው በቀድሞ የአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፕሬዝዳንት የነበረው ተማሪ ተክለሚካኤል አበበ የዶ/ሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመምህርነት ተግባርና ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር የነበራቸውን ቅርርብ፣ በማስተማርና በመማር ሂደት ላይ ያላቸውን ችሎታ በማውሳትና ምስክርነት በመስጠት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት አቋቋሙ

ስያሜው ግንቦት ሰባት ተብሏል

በቅርቡ ራዲዮና ድረ-ገጻቸው ይፋ ይሆናል

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2000 ዓ.ም. May 09, 2008)፦ በቅርቡ ከቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲም ሆነ አሁን እንደአዲስ ከተቋቋመው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ራሳቸውን ያገለሉት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አጋሮቻቸው ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በሚል ስያሜ አዲስ የፖለቲካ ድርጅት አቋቁመው በመጭው ሳምንት ግንቦት 6 ቀን 2000 ዓ.ም. ለህዝብ ይፋ ሊያደርጉ መሆኑን ታማኝ ምንጮቻችን ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዕንቁ መጽሔት ጋዜጠኞች በዋስትና ተለቀቁ

መጽሔታቸው ግን እንደታሰረ ነው

Ethiopia Zare (ኀሙስ ሚያዝያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. May 08, 2008)፦ ባለፈው ቅዳሜ የዓለም የፕሬስ ቀን ተከብሮ በዋለበት ዕለት ፖሊስ አስሯቸው የነበሩት አራት የዕንቁ መጽሔት ጋዜጠኞች እና ባልደረቦች ትናንት ከሰዓት ረፋዱ ላይ በዋስ መለቀቃቸውን ሪፖርተራችን ከአዲስ አበባ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጎርፍ ካጠቃው መኪና አራት ሲሞቱ አንድ ተረፈች

የሥራ ባልደረባውን አድኖ እራሱን ጎርፍ ወሰደው

ሦስቱ የሕክምና ባለሙያዎች ናቸው

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. May 5, 2008)፦ ከድሬዳዋ ድልጮራ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ወደ ገጠር ቀበሌዎች ተጉዞ የነበረ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ይጓዙበት የነበረው መኪና በጎርፍ ተወስዶ አራቱ እንደሞቱ ሲገመት አንዲት ነርስ መትረፏን የኢትዮጵያ ዛሬ የድሬዳዋ ሪፖርተር ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አ.አ. ውስጥ አንበሣ አውቶቡስ 2 ሰዎችን ገድሎ 10 አቆሰለ

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን 2000 ዓ.ም. May 5, 2008)፦ትናንት ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ አንበሣ አውቶቡስ ፍሬን ተበጥሶበት ከገጫቸው ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ሲሞቱ አስሩ በከባድ ሁኔታ መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለሱዳን ተቆርሶ ተሰጠ በተባለው መሬት ላይ የአቤቱታ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. May 3, 2008)፦ "የሱዳን መንግሥት ባለሥልጣናት የኢህአዴግ መንግሥት ከኢትዮጵያ መሬት ቆርሶ እንደሰጣቸው ለመገናኛ ብዙኃኖቻቸው ገለፁ" ከተባለ ወዲህ ጉዳዩ በተለይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ እንደቀሰቀሰ ይታወቃል። ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ 35 ኢትዮጵያውያን "በትክክል የኢትዮጵያ የነበረ መሬት፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መቆየት አለበት" በሚል ርዕስ የአቤቱታ ፊርማ (ፔቲሽን) በኢንተርኔት ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለኢትዮጵያ ዛሬ ከደረሰው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...