በታክሲ ፍንዳታው የሞቱት ስድስት ናቸው

• የአራተኛው አስከሬን በማግሥቱ በሼህ አላሙዲን መናፈሻ ውስጥ ተለቅሞ ተገኘ

• 5ኛውና 6ኛው አካላቸው ተቆራርጦ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ አርፈዋል

• አንዱ በትውልድ እስራኤላዊ በዜግነቱ አሜሪካዊ ነው

Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም. May 22, 2008)፦ ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ወደ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ በአዲስ አበባ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጎን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች ድርጅት በር ላይ በሚኒባስ ታክሲ ላይ በደረሰው ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ስድስት መሆኑን የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሸምጋዮቹ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 13 ቀን 2000 ዓ.ም. May 21, 2008)፦ ምርጫ 97ን ተከትሎ በርካቶች ወደ እስር ከተወረወሩ በኋላ፣ በተለይም የቅንጅትን ከፍተኛ አመራሮችና ከምርጫው ጋር በተያያዘ የታሰሩትን ሰዎች ያስፈቱት የሀገር ሽማግሌዎች ወደ አሜሪካ በያዝነው ሣምንት እንደሚሄዱ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአ.አ. ውጭ ጉዳይ መ/ቤት አካባቢ በደረሰ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ሞቱ

ሁለት ቆሰሉ፣ አምስት ተረፉ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. May 20, 2008)፦ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አካባቢ ሚኒባስ ውስጥ በተከሰተ ፍንዳታ የሰው ሕይወት ማለፉን ከአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ጥቆማ አስረዳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ

Ato Kuma DemeksaEthiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም. May 20, 2008)፦ ኢህአዴግ ባለፈው ሚያዝያ 5 እና 12 ቀን 2000 ዓ.ም. በተካሄዱት ምርጫዎች ብቻውን ተወዳድሮ ካሸነፈ በኋላ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ምክር ቤት መስራች ጉባዔውን አካሂዶ ከንቲባውንና ቀሪዎቹን ባለሥልጣናት መምረጡን ከአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድነት ግንቦት 23 ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሂዳል

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 11 ቀን 2000 ዓ.ም. May 19, 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ትናንት ባካሄደው የላዕላይ ምክር ቤት ስብሰባው ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔውን ለመጥራት መወሰኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የላዕላይ ም/ቤት ነገ ይሰበሰባል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2000 ዓ.ም. May 17, 2008)፦ በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ፣ የአሁኑ የ”አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ” በነገው ዕለት የላዕላይ ም/ቤቱ ተሰብስቦ ፓርቲው ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት ያስችለው ዘንድ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎች ላይ እንደሚደርስ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የመያድ” ረቂቅ ዐዋጅ የሞት ቅጣት ነው ተባለ

መያዶች ለፍትህ ሚኒስቴር አቤቱታ አቀርበዋል

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 8 ቀን 2000 ዓ.ም. May 16, 2008)፦ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) “የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ረቂቅ ዐዋጅ” በሚል የቀረበው ረቂቅ በመያዶች ላይ የተሰነዘረ የሞት ቅጣት ነው በሚል በባለድርሻዎቹ ተተቸ። ረቂቁ ለፓርላማ ከመመራቱ በፊት፣ ሰፊ ውይይት ሊደረግበት እንደሚገባም በመግለጽ ለፍትህ ሚኒስቴር አቤቱታ አቅርቧል ሲል ‘እንቢልታ’ የተሰኘው በሀገር ውስጥ የሚታተም ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ ዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት ሰባት የተጠራው ሰልፍ በስቶክሆልም ተካሄደ

በማትያስ ከተማ

Ginbot 7 Rally  - Stockholm, Sweden

Ethiopia Zare (ኀሙስ ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም. May 15, 2008)፦ ግንቦት ሰባት ቀን 1997 ዓ.ም. የተደረገውን የዲሞክራሲ ትግል ለማስታወስና በወቅቱ የተሰዉትን ሰማዕታት ለመዘከር በዛሬው ዕለት ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም. (ሜይ 15 ቀን 2008) ሊደረግ ታቅዶ የነበረው ሰልፍ በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ተደረገ። በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አዘጋጆቹ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ገለጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነዶ/ር ብርሃኑ ነጋ "ግንቦት 7" ንቅናቄን በይፋ አሳወቁ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 6 ቀን 2000 ዓ.ም. May 14, 2008)ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ አምስት የቀድሞ የቅንጅት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ስላቋቋሙት "ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ" በተሰኘው አዲስ የፖለቲካ ፓርቲን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ኔትዎርክ (ኢ.ቲ.ኤን.) መግለጫ ሰጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኀሙሱ ዓለም አቀፍ ሠላማዊ ሰልፍ በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይካፈላሉ

Reported by Matias Ketema

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. May 13, 2008)፦ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል መሪ አነሳሽነት የፊታችን ኀሙስ ተነገወዲያ ሜይ 15 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. (ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.) በመላው ዓለም የሚደረገው ሰልፍ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልምም እንደሚደረግ አስተባባሪው ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...