የትግራይ ክልል አካሒደዋለሁ ያለው ምርጫ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው ተባለ

The House of Federation of the Federal Democratic Republic of Ethiopia

ምርጫው ቢደረግ፤ የማይጸና መኾኑንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወሰነ

ኢዛ (ቅዳሜ ነኀሴ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 5, 2020)፦ የትግራይ ክልል አካሒደዋለሁ ያለው ምርጫ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ መኾኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ክልል በነገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አልሳተፍም አለ

ሕወሓት እና የፌዴራሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አጀንዳው ቀድሞ ሊደርሰኝ ይገባ ነበርም ብሏል

ኢዛ (ዓርብ ነኀሴ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 4, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነገ የጠራው አስቸኳይ ስበሰባ አጀንዳ ቀድሞ ካልደረሰው፤ ክልሉን የሚወክሉ አባላት በስብሰባው ላይ እንደማይሳተፉ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የኢዜማ መግለጫ ሐሰተኛና የተጋነነ ነው” ታከለ ኡማ

Eng. Takele Uma

የኢዜማን መግለጫ ኮንነው፤ ለአርሶ አደሮች የሰጠነው 20 ሺህ ቤት ነው ብለዋል
የመሬት ወረራ ላይ እርምጃ ስንወስድ ነበር

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 1, 2020)፦ ትናንት ረፋድ ላይ ጀምሮ የብዙዎችን ዓይንና ጆሮ የያዘው በአዲስ አበባ ተፈጸመ ስለተባለው ሕገወጥ የመሬት ወረራና ያልተገባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን ለተመለከተው የኢዜማ መረጃ በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ተብለው የሚታመኑት የቀድሞው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂንየር ታከለ ኡማ፤ የኢዜማን መግለጫ በመኮነን ድምፃቸውን አሰሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጄኔራሉ ብልጽግና ፓርቲን ተቀላቀሉ

B.Gen. Kemal Gelchu

ከኦነግና ከኦፌኮ ጋር ተፋትተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. September 1, 2020)፦ የቀድሞው የጦር መኮንንና የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ መሥራችና ሊቀመንበር ብርጋዲየር ጄኔራል ከማል ገልቹ ፓርቲያቸውን አክስመው የብልጽግና ፓርቲን ተቀላቀሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖሊስ በአቶ ልደቱ ላይ ክስ ለመመሥረት የጠየቀው ተጨማሪ ቀን በፍርድ ቤቱ ውድቅ ኾነ

Lidetu Ayalew (Photo: Addis Fortune)

አቶ ልደቱ የዋስትና ጥያቄያቸውን በሌላ መዝገብ ማቅረብ ይችላሉ ተባለ

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 31, 2020)፦ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ክስ እስኪመሠረት ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው የጠየቀው መርማሪ ፖሊስ፤ ጥያቄውን ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ፤ አቶ ልደቱ በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ተሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ በአዲስ አበባ መሬት ወረራና የኮንዶሚኒየም እደላ ዙሪያ አጀብ ያሰኘውን መረጃ ይፋ አደረገ

Prof. Berhanu Nega and Takele Uma

213,000 ካሬ ሜትር መሬት በሕገወጥ መንገድ ታድሏል
95 ሺሕ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ላልቆጠቡ ሰዎች ተሰጥቷል
የዚህ ወንጀል ተባባሪዎች ለፍርድ ይቅረቡ ብሏል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 31, 2020)፦ ኢዜማ በአዲስ አበባ ከ213,000 ካሬ ሜትር በላይ መሬት በሕገወጥ መንገድ መታደሉንና 95 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሕገወጥ መንገድ ለማይመለከታቸውና ለጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላልቆጠቡ ሰዎች መተላለፉን የሚያመለክተውን በጥናት ላይ የተደገፈ ሪፖርቱን ዛሬ ሰኞ ነኀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል። ጥናቱ የተጠናው በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት አሥር ክፍለ ከተሞች ውስጥ በአምስቱ ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 25 ቦታዎች ላይ ብቻ ነው። በዚህ ወንጀል እጃቸው ያለበት ባለሥልጣናት ለፍርድ ይቅረቡ ብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 51ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 51st, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሃምሳ አንደኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከነኀሴ 18 - 24 ቀን 2012 ዓ.ም.) ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ አነጋጋሪ ከነበሩ ዜናዎች መካከል ኢዜማ ከመሬት ወረራና ከኮንዶሚኒየም አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ መከልከሉ ነው። አዲሷ ምክትል ከንቲባ ሳምንቱን በተለያዩ ክንውኖች የዜና ሽፋን የተሰጣቸው ሲሆን፤ ጐልቶ የሚጠቀስላቸው ደግሞ የከተማዋን የሰላም ምክር ቤት በይፋ ማቋቋማቸው ነው። ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ግድያ ለመፈጸም ቦምብ በመወርወር ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት አምስት ተከሳሾች፤ ጥፋተኛ መባላቸው የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር። ፍርዳቸው ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢዜማ ጋዜጣዊ መግለጫ በፖሊስ ታገደ

ኢዜማ

በአዲስ አበባ ከተማ መሬት ወረራና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሐዊ ዕደላ ጋር ተያይዞ ፓርቲው ዛሬ መግለጫ ሊሰጥ ነበር

ኢዛ (ዓርብ ነኀሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 28, 2020)፦ ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የመሬት ወረራና የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ኢፍትሐዊ ዕደላን በተመለከተ ሲያዘጋጀው የነበረው ጥናት ላይ የቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ ታከለ ኡማ ጽሕፈት ቤት፤ የመሬት ልማት ቢሮና የቤቶች ኤጀንሲን ምላሽ ለማካተት ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ ቢያጣም፤ በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ላይ ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በፖሊስ ታገደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወላይታ ዞን አዲስ ዋና አስተዳዳሪ ተሾመለት

Endrias Geta (PHD)

የዞኑ ምክር ቤት ለዶ/ር እንድሪያስ ጌታ ሹመቱን የሰጠው ዛሬ ባካሔደው ስብሰባ ነው

ኢዛ (ዓርብ ነኀሴ ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 28, 2020)፦ በቅርቡ ከወላይታ ዞን አስተዳዳሪነታቸው በተነሱት በአቶ ዳጋቶ ኩምቤ ምትክ፤ ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ እንደተሾሙ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ