ሲኖዶሱ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተፈጸመው ጥቃት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠር ነው ሲል መግለጫ አወጣ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መግለጫውን በሰጠበት ወቅት

የፖለቲካ ፓርቲዎች ርዕዮተ ዓለማዊ ጥቃት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እያደረሱባት እንደኾነ ተገለጸ

ኢዛ (ረቡዕ ነኀሴ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 26, 2020)፦ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸመው ጥቃት ዋናው ዒላማ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን እንደነበሩ በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥታለች። በፖለቲካ ፓርቲዎች ርዕዮተ ዓለማዊ ጥቃት እየደረሰባት እንዳለ ያስታወቀችው ቤተ ክርስቲያኒቱ፤ ከ67 በላይ ምእመናን በግፍ እና በአሠቃቂ ኹኔታ መገደላቸውን ከዐቢይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት መረዳትዋን አስታውቃለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የህዳሴ ግድብን በመጎብኘት የመጀመሪያዊ መሪ ሊኾኑ ነው

PM Abiy Ahmed (L) and PM Abdalla Hamdok (R)

ጉብኝቱ ሱዳን ከኢትዮጵያ ወገን ስለመቆምዋ የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል

ኢዛ (ረቡዕ ነኀሴ ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 26, 2020)፦ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ለመጎብኘት የመጀመሪያው የተፋሰሱ አገር መሪ ሊኾኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋናና ምክትል ሥራ አስፈጻሞዎቹ ከሥራ ተሰናበቱ

አቶ በቀለ ሙለታ (በግራ)፣ አቶ አድማሱ ዳምጠው (በቀኝ)

በምትካቸው አዲስ ተሿሚዎች ተተክተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 25, 2020)፦ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ለአንድ ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩት አቶ በቀለ ሙለታና ምክትላቸው አቶ ብሩክ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነስተው በአዲስ ተተክተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲሷ ከንቲባ አዲስ አበባን የሚመጥን የጸጥታ መዋቅር እንደሚገነቡ አስታወቁ

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የጸጥታ ምክር ቤት ለማቋቋም መክረዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 25, 2020)፦ አዲሷ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን የጸጥታ መዋቅር እንደሚገነቡ አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዳዲስ የፖሊስ ዘርፎች ወደ ሥራ ሊገቡ ነው

Endeshaw Tassew

የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ ሊቀየር ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 25, 2020)፦ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብሱን ሊቀይር መኾኑንና አዳዲስ የፖሊስ ዘርፎችን ወደ ሥራ ሊያስገባ መኾኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አስታወቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 50ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 50th, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሃምሳኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከነኀሴ 11 - 17 ቀን 2012 ዓ.ም.) ካሳለፍነው ሳምንት ቀዳሚ ዜናዎች ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለ10 የሥራ ኃላፊዎች ሹመት መስጠታቸው ነው። በተለይ የምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ስንብት ያልተጠበቀ ሲሆን፣ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ 32ኛዋ ከንቲባ ኾነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብልጽግና ለአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤቱ አዲስ ኃላፊ ሰየመ

አቶ መለስ ዓለሙ፣ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እና ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ (ከግራ ወደ ቀኝ)

አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ወደ ዋናው ጽ/ቤት ተሹመው ሔዱ
ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በዋናው ፓርቲ ጽ/ቤት የዓለም አቀፍና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኾነዋል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፲፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 24, 2020)፦ አቶ መለስ ዓለሙ የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ ተስፋዬ በልጅጌን በምተካት የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኾነው ሲሾሙ፤ አቶ ተስፋዬ በሚኒስትር ማዕረግ ወደ ዋናው የብልጽግና ጽ/ቤት ተዛውረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ቀን ምርመራ 1,778 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

Total coronavirus cases in Ethiopia, August 20, 2020

በቫይረሱ ተጠቅተው የሞቱት 620 ደርሰዋል

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 20, 2020)፦ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ በሚባል ደረጃ እየጨመረ በመምጣት፤ በአንድ ቀን 1,778 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ዛሬ ተደረገ። ከዚህ ቀደም ከፍተኛውና በአንድ ቀን ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የተመዘገበው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን፤ ቁጥሩም 1,652 ነበር። በአምስት ቀን ውስጥ በዛሬው ዕለት ያ አኀዝ በ126 ጭማሪ አሳይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ