ብልጽግና ምርጫውን ሲገመግም፤ ኢዜማ በምርጫው ሒደት ላይ መግለጫው ይጠበቃል

ምርጫ 2013

ኢዜማ ድምፅ መስጠቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርጫ ሒደቱን በተመለከተ የመጀመሪያውን መግለጫ የሚሰጥ ፓርቲ ይኾናል

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 23, 2021)፦ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስድስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ሒደት የተመለከተ ግምገማ ማድረጉን ሲያሳውቅ፤ ኢዜማ አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለወራት ተቋርጦ የነበረው የአስመራ በረራ ዳግም ተጀመረ

Ethiopian Airlines

በረራውን አቋርጦ የነበረው በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ጦርነት ጋር የተያያዘ እንደኾነ ይታመናል

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 23, 2021)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለወራት አቋርጦት የነበረውን የአስመራ በረራ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ከፈረንሳይና ከጣሊያን ጋር በመከላከያ ዙሪያ ለመሥራት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተላከ

98ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የመለስ አካዳሚ ስያሜ እንዲቀየር የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 22, 2021)፦ ኢትዮጵያ ከጣሊያን እና ከፈረንሳይ ጋር በመከላከያ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ያደረገቻቸውን የሁለትዮሽ ስምምነቶች ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው የሚያደርገውን የማጸደቂያ ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተላከ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ውጤቱን ወደ አዲስ አበባ ለማስመጣት ምርጫ ቦርድ ትብብር ጠየቀ

Ballot box, Ethiopian Election 2021

ለጸጥታ ኃይሎችና ለሹፌሮች ቦርዱ አበል ይከፍላል

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 22, 2021)፦ ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ትናንት በሰላም መጠናቀቁ ከተገለጸ ወዲህ፤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤቶችን ከክልል ወደ አዲስ አበባ በልዩ ጥበቃ እንዲገቡ የክልል መንግሥታትን ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ አጋጠሙ ያላቸውን ችግሮች ገለጸ

Birhanu Nega (Prof.)

ዘግይተው ምርጫ የተጀመረባቸው ቦታዎች ሰዓት እንዲጨመር ጠይቋል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ በዛሬው ምርጫ 2013 ላይ ጥሩ ነገሮች እንደታዩ ሁሉ፤ የተለያዩ ችግሮችንም መመልከቱን ኢዜማ አስታወቀ። ዘግይተው ምርጫ የተጀመረባቸው ቦታዎች ሰዓት እንዲጨመር ጠይቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠዋት ቅኝትና የቀትር በኋላ ድምፅ መስጠት

PM Abiy Ahmed

2070 የሚዲያ ባለሙያዎች በ100 ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን በቀጥታ እያስተላለፉ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ የአንድ ዳቦ ፋብሪካን ግንባታ ጨምሮ፤ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን የሥራ ሒደት ከጎበኙ በኋላ፤ ወደ ትውልድ ቀያቸው በመሔድ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ በምርጫው ቀን ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው

Ethiopian Citizens for Social Justice

በቀሩት ሰዓታት መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ ብሏል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በ2013 ምርጫ ቀን ላይ ያጋጠሙ እና በተቀሩት ሰዓታት መፍትሔ ይገባቸዋል ባላቸው ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወይዘሪት ብርቱካን በአማራና በደቡብ ክልሎች ሕገወጥ ተግባሮች ታይተዋል አሉ

Birtukan Mideksa

- በደቡብ የምርጫ መገልገያ የያዘ ሳጥን በመሰረቁ፣ የምርጫ ጣቢያው አልተከፈተም
- ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ 2013 አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ሕገወጥ ተግባራት መታየታቸውን አመለከቱ። በደቡብ ክልል “ኡባ ደብረፀሐይ” በተሰኘ የምርጫ ጣቢያ፤ ለጣቢያው የሚያገለግል ሰማያዊ ሳጥን ተሰርቋል መሰረቁን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ