አጋዚና ሰይጣን (Read on PDF)

ከወለላዬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አጋዚና ሰይጣን ተገናኝተው መንገድ

ሽቅብ ቁልቁለቱን በመውጣት በመውረድ

ሲሄዱ አመሹና አንድ ላይ በመጓዝ

ጨለማው ጠንክሮ ዓይናቸውን ሲይዝ

ፈልገው ለማደር በእግዜር እንግዳነት

ፈቃድ ለመጠየቅ ተጠጉ ካንድ ቤት

 

እነዛን እንግዶች ባለቤቱም አይቶ

ከጋብዘ ወዲያ እቤት አስገብቶ

ማሳደር የምችል አንዱን ነው በማለት

ማንነታችውን ጠየቀ እንዲነግሩት

አጋዚው ተነስቶ የመለስ አዲስ ጦር

እንደሆነ ገልጾ አብራርቶ ሲናገር

ሰይጣንም ገለጸ እራሱን ሳይስወር

ይሄኔ ሰውየው ፈገግታ አሳይቶ

እንዲአድር ፈቀደ ሰይጣን እቤት ገብቶ

አጋዚው እራሱን እየነቀነቀ

እንዴት እሱን መረጥክ በማለት ጠየቀ

ሰይጣንስ ይሄዳል በመስቀል በጠበል

አንተ አልወጣም ካልከኝ ምን ማደረግ ይቻላል

ስለዚህ መላህን ያንተን ስለማላውቅ

አላሳድረህም ሌላ ቦታ ጠይቅ

በማለት ተናግሮ ዘግቶ ገባ በሩን

አጋዚን አባሮ አስተኛው ሰይጣንን


 

ከወለላዬ ሰኔ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. ስዊድን

June 23, 2008 Sweden

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ