20210302 adwa

እሸቱ ታደሰ

ዓይነ ደረቅ አልሽኝ፣ ከልብህ አታላይ

ዓይኔን ግንባር ያርገው፣ የምትል አስመሳይ?

ይሁና …

ከሁሉም ስትወስጂ እነሱም ሲነግሩሽ የረባ ያረባውን

እያሽሞነሞኑ በቀልድ እያዋዙ የመሰላቸውን

እውነት ነው እያልሽኝ አንድም ሳታስቀሪ

በአሽሙር አላውሰሽ ለኔ ስትነግሪ

እጅጉን ተገረምኩ ትዝ ቢለኝ ያኔ

ገና እንደመጣሁ ልበ ሙሉ ሆኜ

ባልዋልክበት ቦታ ባልሄድክበት መንደር

እሱማ መጥፎ ነው ሰውን አያከብር

ብለው ስለሚያሙህ ከቶም አትሸበር

ቁብም አትስጣቸው ብለሽኝ አልነበር?

ታዲያ ምን ተገኘ እዚያ … ካለሽበት

ድንገት ያስወሰነሽ እነሱን ለመስማት

ከኔ ለመደበቅ ዓይኔን ላለማየት


(እሸቱ ታደሰ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!