የቴዲ ነገር (ከጌታቸው አበራ)
(ለህሊና እስረኛው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ)
ከጌታቸው አበራ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )
የገዘፈውን ጨለማ - ብርሃን ቢፈነጥቅበት፣
የተዳከመውን ኢትዮጵያዊነት - እስትንፋስ ቢዘራበት፣
ፍቅር፣ ሠላም፣ … እርቅን - ዘምሮ ቢያስዘምረን፣
ለትውልዱ ራዕይ ኪዳን - ድምፁ ተስፋ ቢሆነን፣
ዘረኝነት የተጠናወታቸው - ለጥፋት ያደገደጉ፣
በእኩይ ምግባር ታንጸው - ህሊና አልባ ያደጉ
በክፋት፣ በቂም፣ … በተንኮል - የታጀሉ ጨለምተኞች፣
ጥበብን አሰሩት አሉ - የድንቁራና ”ሊቆች”።
ባገር ፍቅር ክትባት - ተኮትኩቶ ያደገ፣



