የትነበርክ ታደለ

TV Ads For Alcohol: Do They Increase The Risk For Teenage Drinking Problems?

እናመስግን ይሆን?! ስንቶቻችን በየቤታችን የተንገበገብንበትና በሶሻል ሚዲያ የተንጫጫንበት ቅጥ የለሽና ልክ የለሽ የአልኮል መጠጦች የማስታወቂያ ጋጋታ እንዲገደብ የሚያዝ አዋጅ ሊወጣ ነው እና እናመስግን?

ግን ምኑን አምነን እናመሰግን? እንኳን ገና ሊወጣ ነው የሚባል ሕግ ይቅርና፤ ወጣ የተባለው 'ሲጋራ በሕዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች እንዳይጨስ' የሚያዘው ሕግ መቼ ተግባራዊ ሲሆን አየንና ነው? ቀድሞ ማመስገን ኋላ ለመውቀስ ያስቸግራል ይላሉ አባቶች።

ኢትዮጵያ ውስጥ 100 ሺህ ህጻናትና 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን አዋቂዎች ትምባሆ ያጨሳሉ። ምን እሱ ብቻ? በየዓመቱ 9,600 ኢትዮጵያውያን ሲጋራ በማጨስ ሰበብ ለሞት ይዳረጋሉ።

እና ይህንን ሁኔታ እያየና እየተገነዘበ ህጻናትን ከዚህ አስከፊ ችግር ለመጠበቅና አዋቂዎችንም ለማቀብ የሚያስችለውን ሕግ ተፈጻሚ ለማድረግ እግር ያጠረው መንግሥት፤ አሁን ደግሞ የአልኮል መጠጥ አምራቾች የሕዝብ በዓላትን ስፖንሰር እንዳያደርጉ የሚደነግግ ሕግ አወጣለሁ ቢለን፤ "እውን ይሆን ይሆን?" በሚል ጥርጣሬ ከማየት በዘለለ ለምስጋና አፋችንን ለመክፈት እንቸገራለን።

በተለይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከሙያ ሥነምግባር ባፈነገጠ መልኩ አንድን በዓል አስታኮ በሚያዘጋጃቸው ዝግጅቶች በሙሉ በሚሰነቅራቸው የቢራ ማስታወቂያዎች ጊዜና ሰዓት ባልመረጠ መልኩ ህጻናት ቁጭ ብለው እየተመለከቱት በማዝናናት ሰበብ፤ የቢራን ፍቅር እየሰበከ፣ ገንዘብ ሲቃርም ስንት ዘመን ተቆጠረ?

ቢራ ለፍቅር፣ ቢራ ለኩራት፣ ቢራ ለቤተሰብ ደስታ፣ ቢራ ለበዓል ድምቀት ... ኧረ ስንቱን ስንቱን ነገር ቢራ እንደሚሠራልን እየሰበኩን በዓላችንን፣ ያውም የኃይማኖት በዓላትን ሳይቀር እየነጀሱ አዋሉን ...?

ይህ ሕዝብ ሰልችቶት የተወው ሕገ ወጥ ተግባር፣ ዛሬ መንግሥት ኮንስሮት ሕግ ሲያወጣበት ሳይሆን፤ በሚያወጣው ሕግ ላይ ለተፈጻሚነት ወገቡን ታጥቆ ለሕዝብ በተለይም ለነገው ትውልድ መልካም አስተዳደግ መቆሙን ሲያሳየን ... ያኔ እናመሰግናለን!! እስከዚያው ግን እየታዘብን እንቆያለን!!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!