”ሕገመንግሥታዊነት፣ ዲሞክራሲና የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስር” ስየ አብርሃ
የወ/ት ብርቱካንን እስር ምክንያት በማድረግ ዕሁድ መጋቢት 20 ቀን 2001 ዓ.ም. (ማርች 29 ቀን 2009) በአዲስ አበባ ኢምፔሪያል ሆቴል ”ቃሌ” በሚል ስያሜ በተካሄደው ሲምፖዚየምና የሻማ ማብራት ዝግጅት ላይ አቶ ስየ አብርሃ ”ሕገመንግሥታዊነት፣ ዲሞክራሲና የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስር” በሚል ርዕስ ጽሑፍ አቅርበዋል።
በዚህ ሲምፖዚየምና የሻማ ማብራት ዝግጅት ላይ የተለያዩ ወገኖች ጽሑፎችን አቅርበው ነበር። ከእነዚህም ውስጥ ዶ/ር መራራ ጉዲና፣ የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘነበ አሰፋ እንዲሁም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ይገኙበታል።
አቶ ስየ አብርሃ ”ሕገመንግሥታዊነት፣ ዲሞክራሲና የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ እስር” በሚል ርዕስ ያቀረቡትን ጽሑፍ አስነብበኝ።