ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን በ2012 ምርጫ መሳተፍ ይገባቸዋል

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም Professor Alemayehu G. Mariam ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ጉዳዩ የምርጫ ብቻ አይደለም እኮ!

ባለፈው ሴብቴምበር ስለ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጥ ድጋፌን ገልጬ ነበር። ለታዳሚዎቼ እንዳስነበብኩት በ2008 ምርጫ ተወዳዳሪ ባራክ ኦባማን ደግፌ እንደነበርና ከምርጫው በኋላ ግን በታየው በተለይም ኢትዮጵያንና አፍሪካን በተመለከተ ስለተካሄደው አስተዳደራዊ ፖሊሲ ግን በጣሙን ቅሬታ አድሮብኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ክፍል 2 - ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

አማኑኤል ዘሰላም

መግቢያ

አንባቢያን ሰፊ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ፣ የሙስሊም አክራሪነት እንዴትና ከየት እንደተጀመረ፣ በአሁኑ ወቅትም በአለማችን ምን አይነት ችግር እያስከተለ እንዳለ ለማሳየት ሞክሪያለሁ። በተለይም ሳውዲ አረቢያ፣ ካላት የነዳጅ ክምችት የተነሳ በምታገኘው ፔትሮ ዶላር፣ ምን ያህል፣ ለሰብዓዊነት ክብር የሌለውን አክራሪነት ለማስፋፋት የምትጫወተው አሉታዊና ሰይጣናዊ ሚና፣ የማያሻሙ መረጃዎች በማስቀመጥ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ ሞክሪያለሁ። በክፍል ሁለት ትኩረቴን በውጭ አገራት ካሉ የአክራሪነት እንቅስቃሴዎች አንስቼ በአገራችን እየታዩት ወዳሉት የሙስሊም እንቅስቃሴዎች እዞራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓርኪንግ

Parkingዳንኤል ክብረት

አሜሪካን ሀገር ወደሚኖሩ ወዳጆቼ ቤት ሄጄ ነበር። ከተጋቡ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል። ቤታቸው ስገባ የቤቱም ዕቃ የቤቱም ሰዎች ዝምታ ውጧቸዋል። አባ አጋቶን ቤት የገባሁ ነው የመሰለኝ። እርሱ ክፉ ላለመናገር ሰባት ዓመት ድንጋይ በአፉ ጎርሶ በአርምሞ ተቀምጧል። ነገር ዓለሙ አላምር ሲለኝ ‹ምነው ያለ ወትሯችሁ ዝምታ ዋጣችሁ› ብዬ ተነፈስኩ። እዚህ ቤት የነበረውን ሳቅና ጨዋታ ስለማውቀው። ‹ሳቅና ጨዋታ ዝና ካማራችሁ› ሲባል አልሰማችሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመከላከያ የጀኔራሎች ፍጥጫ

(እየሩሳሌም አርአያ)

በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሃይለማርያም ቃለመጠይቅ በሻዕቢያ የተዘጋጀ?

ተስፋዬ ገብረአብ

ሰሞኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ አንድ አስገራሚ ቃለመጠይቅ ሰጥቶ ነበር። አገር ውስጥ ለሚታተም መፅሄት በሰጠው በዚሁ ቃለመጠይቅ ላይ፣ “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” በማለቱ ከቤተሰቡ የደረሰበትን ተቃውሞ ገልፆአል። በርግጥም ሃይለማርያም ልጆቹንና ባለቤቱን ሰብስቦ፣ “ተሳስቼያለሁ።” ብሎ ይቅርታ ጠይቆአል። ይህን እንግዲህ ከመፅሄቱ ላይ ያነበብነው ነው። የሃይለማርያም ሴት ልጅም አባቷን በዚህ መልኩ በማረሟ ታዋቂ ሆና ሰንብታለች። በርግጥም ዘላለማዊ ክብር ለአምላክ እንጂ ለሰው የሚሰጥ አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብርሃንና ሰላም = ጽልመትና ሽብር

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊውን የፍትሕ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ አገደ፤” (www.fetehe.com እና በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ ሐምሌ 2004 ዓ.ም)

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ ሳምንታዊው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳይታተም ከለከለ።” (www.fnotenetsanet.com እና amharic.voanews.com October 02, 2012/ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም))

“ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ የሪፖርተር ጋዜጣን ገጽ ቁጥር ገደበ።” (ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም)

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በሁሉም ዜናዎች በበጎ ጎኑ አልተነሳም። “እንዳይሰራጭ አገደ!” “እንዳይታተም ከለከለ!” እና “ቁጥር ገደበ!” የሚሉት ሃረጎች የማተሚያ ቤቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ ናቸው። ይህ ማተሚያ ተቋም፣ የዛሬዎቹ ሹመኞችና ባለሥላጣናቱ አወቁትም - አላወቁትም ትልቅ ራዕይና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነበር። እነዚህን ተልዕኮዎቹን ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል መስዋዕት ማድረግ ግን ከተጠያቂነትና ከታሪክ-ሕሊና ተወቃሽነት አያድንም። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያዋ ርዕዮት ”የጥንካሬዬ ዋጋ”

ርዕዮት ዓለሙ Reyot Alemuፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም / ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ ብዙ ነገሮች የሉም። ለ31 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም። አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ”ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ” በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን ለአለም አስተላልፋለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ክፍል 1 - ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ

አማኑኤል ዘሰላም

መግቢያ

ከእስልምና ጉባዔ ምርጫ ዙሪያ፣ በወሎ ክፍለ ሃገር ፣ ሀገራ ከተማ በተነሳው ግጭት ሶስት ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው እንዳለፈ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ምርጫው ከተደረገ ከበርካታ ቀናት በኋላ፣ በምርጫ በተሳተፉትና በምርጫ ባልተሳተፉት መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ ፖሊስ ጣልቃ እንደገባ የዘገበው ሪፖርተር፣ ከሞቱት ሰዎች መካከል አንዱ የፖሊስ አባል እንደሆነም ጠቅሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለመሆኑ ኢሕአዴግ አለ እንዴ?

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ጤና ይስጥልኝ ክቡራትና ክቡራን አንባቢያን፤

በዚያኛው ሰሞን ስለብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ከእግዚአብሔር መንገድ መራቅና ስለሕዝበ ክርስቲያን የመንፈስና የልብ መሸፈት አንዳንድ ነጥቦችን ተናግሬ ነበር። አንድ ሦስት ያህል የነጻው ሚዲያ ድረገጾች አስተናግደውታል። እግዚአብሔር ይባርክልኝ፤ መንግሥተ ሰማይንም ያውርስልኝ። ሙከራየ ጥቂቶችን ከገቡበት አረንቋ እንዲወጡ - እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ - ለማሳሰብ እንጂ ኃይማኖተኝነትን ለመክሰስ ወይ ለመውቀስ አይደለም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ