አማረ አረጋዊ ጩቤ ጨበጠ!

አማረ አረጋዊ, Amare aregawiተስፋዬ ገብረአብ

አማረ አረጋዊ ከልብ የሚያደርሱ ቃላትን በመጠቀም ኢህአዴግን የሚገለባብጥበት ጊዜ አለው። የረቡእ ርዕሰ አንቀፅ የዚህ ምሳሌ ነው። ኢህአዴግን በሁለት ከፍሎ ያየዋል። ሙሰኛ ያልሆኑ፣ ለአገር አሳቢ የሚላቸው አሉት። እንዲህ ማለቱ ሚዛን ለመጠበቅ ይሆናል። ርግጥ ነው፣ እኔ ጨምቄ ያቀረብኩት የርእሰ አንቀፁን ቁንፅል አሳብ ነው። አማረ በርዕሰ አንቀፁ ኢህአዴግ በመጪው ጉባኤ ራሱን እንዲያፀዳ መክሮአል። የአማረ ምክሮችና የኢህአዴግ ጠንካራ ጎን ሆነው የቀረቡት አጃቢዎች ገለል ሲሉ የኢህአዴግን እውነተኛ ምስል የሚገልፀው ክፍል የሚከተለውን ይመስላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኦሮሞ ህዝብ  ጀርባ...

(ከተመስገን ደሳለኝ)

እንደ መግቢያ

1975 ዓ.ም.፡፡ በመሀል  ሀገር የነበረው የፖለቲካ ግለት ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ወደ ጠረፍ እና የገጠር ከተሞች አፈገፈገ፡፡ በ‹‹ምርጥ መኮንኖች›› የተመሰረተው መንግስትም አንፃራዊ ሰላም ያገኘ መሰለ፡፡ አስቀድሞ ‹‹ወታደራዊ ክንፍ›› አቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በ ገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ለማቀጣጠል ሞክሮት የነበረው አብዮት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎት ከሸፈ፡፡ ለክፉ ቀን ‹‹አማራጬ›› ያለው ወታደራዊ ክንፉም ቢሆን ለሶስት በመከፈሉ በእጅጉ ተዳከመ (ትግል በቃን ብለው ወደ ምዕራብ  ገራት ለመሰደድ በወሰኑ፣ ኢህአፓን ይዘን እስከመጨረሻው እንፋለማለን ባሉና ‹‹ኢህአፓ ዴሞክራት አይደለም›› በሚል ተገንጥለው ‹‹ኢህዴን›› የተባለ አዲስ ድርጅት በመሰረቱ) ከዚህ በተቃራኒው በመገንጠል እና በብሄር ጥያቄ ዙሪያ የተሰባሰቡት ሻዕቢያ፣ ህወሓት እና በሽብርተኝነት የተፈረ ው ኦነግ የተሻለ ድርጅታዊ አቅም መፍጠር ቻሉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሃይማኖት ነፃነትና መቻቻል

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም

‹‹ማንኛውም የሃይማኖት ነፃነት በሕገ መንግሥቱ የተከበረ ነው፤ አንቀጽ 27/1

ሰው የማሰብ፤ የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነት አለው፤ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ፣ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር፣ ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል።›› ብዙ ሰዎች ይህ አንቀጽ እንደገባቸው አድርገው ይናገራሉ፤ አንቀጹ ከሃይማኖት ነጻነት በተጨማሪ ብዙ ሌሎች መብቶችንም የያዘ ነው፤ የሕሊና ነጻነትና የሃይማኖት ነጻነት አንድ አይደለም፤ የሃይማኖት ነጻነትና እምነት አንድ አይደለም፤ እነዚህ የተጠቀሱት ሀሳቦች አንድ አይደሉም ብቻ ሳይሆን አንዳንዴ ይጋጫሉ ወይም ይቃረናሉ፤ ኅሊናና እምነት፣ ወይም ኅሊናና ሃይማኖት፣ ወይም እምነትና ሃይማኖት አንዳንድ ጊዜ አይስማሙም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ኃይለማርያም እና ኤርትራ – መልስ ለአቶ ግርማ ካሳ

አቡጊዳ ቀይሶ ከኮልፌ

ውድ አቶ ግርማ ካሳ "አቶ ኃይለማርም እና ኤርትራ" በሚል ፅሑፍ አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያለዎትን ሃሳብ ስላካፈሉን በቅድሚያ ያለኝን ምስጋናዬ ላቅርብ። በፅሑፎ ላይ ስለሰጡት የዘር መተንትን ከእርሶ ጋር የምጋራው ነጥብ ቢኖረኝ እንጂ የምቃወምዎት ሃሳብ የለኝም። ምክንያቱም ዘር የእድል ጉዳይ እንጂ የጥረት ውጤት አይደልምና። ማንኛውም ሰው መመዘን ካለበት በጥረቱ በሚሰራው ስራና በሚያመጣ ውጤት እንጂ በዘር መሆኑ በጣሙን የተሳሳተ አመለካከት በመሆኑ በዚህ ላይ ሰፊ ትንታኔ መስጠት ቢቻልም በግዜው ስለፃፉት ስለ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሳብ ላይ ያለኝን አስቴየት ለመሰንዘር ነው።  

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዘልቆ ሊያመን የሚገባው በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የሚደርሰው ግፍ (ነቢዩ ሲራክ)

ለዚህስ ማን ነው ተጠያቂው?

ነቢዩ ሲራክ

ይህ የምትመለከቱትን ፎት ያነሳሁት በጅዳው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች አንድ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው። ይህች የምታይዋት እህትም ምን እዚያ አመጣት እንዳትሉ! ከአንድ ወር ከሳምንት በፊት በኮንትራት ስራ ከሀገር ቤት የመጣች መሆኗን ሳውዲው የእድሜ ባለጸጋ አሰሪዋ ተነገረውኛል። እኔም ሆንኩ ይህንን ጉድ አብረውኝ የሚመከቱ እህቶቸ ሁላችንም ወደ ሃገር ቤት የሚሸኙ ዘመዶቻችንና ወዳጆቻችን አጅበን ነና የመጣነው የዚህች እህት ወደ አየር መንገዱ ለምን እንዳመጣች መጠየቅ አላስፈለገኝም። በሰውነቷ ላይ ባረፈውን እስራትና ድብደባ ከመገለ እጇና ገላዋ ላይ ሰንበር የመሰለ የጉዳት ምልክት ይታያል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐሙስን ከሚኒስትሩ ጋር! (ከተማው ገረመው - 6 ኪሎ ዩኒቨርስቲ)

ነፃ አስተያየት

 

ዕለቱ ሐሙስ ነው፡፡ ቀኑ ደግሞ ‘08’፡፡ ወርሃ ጥቅምት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢህአዴግ ግንባር ቀደሞች ተሰብስበናል፡፡ በታሪካዊው የ”FBE” አዳራሽ፡፡ ታሪካዊ ማለቴ ቆራጡ መንጌ የፖለቲከ ርዮት ያጠጣበት የነበረ አዳራሽ በመሆኑ ነው፡፡ ካለመናችሁ ወንበሮቹን እዩአቸው፡፡ መደገፊያዎቹ ላይ “ፖ/ት ይላሉ፡፡ ፖለቲካ ት/ቤት እንደማለት፡፡ በቀኝ እጃቸው ሴቷ ማጭድ ወንዱ መዶሻ ይዘው ግራ እጃቸውን “የሁሉም ሐገር ሠራተኞች ተባበሩ!” የሚል መፈከር ያነገቡ የሚመስል ቅርፅም መግቢያው ላይ አለ፡፡ እናስ ታሪካዊ አይደለም ትላላችሁ?! እኛም ግንባር ቀደሞቹ በዚህ ታሪካዊ አዳራሽ ታሪካዊ ስብሰባ እያደረግን ነው፡፡ ሰብሳቢዎቻችን ደግሞ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም እና የ ዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ ናቸው፡፡

 

ከጠዋቱ 3፡00 ከአራቱ የኢህአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች የተውጣጣን ግንባር ቀደሞች አዳራሹን ሞላነው፡፡ የመሰረታዊ አደረጃጀት አመራሮች በር ላይ ሆነው ግንባር ቀደም ያልሆነውን ግንባሩን አዙሮ እንዲሄድ ለማድረግ በጥንቃቄ እየለቀሙ ያስገባሉ፡፡ አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ፡፡ ስብሰባው ለታላቁ መሪያችን  ጸሎት በማድረግ ተጀመረ፡፡ ክቡር ሚንስትሩ አጀንዳውን አስተዋወቁ፡፡ ስለ ‘አክራሪነት’ ነው፡፡ አቶ አምባዬ የተባሉ ሰው (ይቅርታ ማዕረጋቸው ስላልተነገረን) ያዘጋጁትን ጽሑፍ “በፕሮጀክተር” ዘረገፉት፡፡ የቀረ የለም፡፡ ሁለም በአክራሪነት ተፈርጇል፡፡ አንዳንድ ዋሃቢያዎች… አንዳንድ ሰለፊዎች… አንዳንድ ካዋርጃዎች… አንዳንድ ማኅበረ ቅዱሳኖች… አንዳንድ…፡፡ አክራሪዎች ናቸው ተባለ፡፡ ከንጉሡ ጀምሮ እስከ አምባ ገነኑ ደርግ ድረስ የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዳልነበር አስተጋቡ ፤ የዛሬውንም መንግሥት ቸርነት ሰበኩ፡፡ አቶ አምባዬ ረጅሙን ትንተናቸውን ሲጨርሱ ክቡር ሚንስተሩ ተተኩ፡፡ ትንሽ ላጠናክረው ብለው አንዳንድ ነገሮችን አንስተው በአንዳንዶች ላይ ዙሩን አከረሩት፡፡ እኝህ ክቡር ሚኒስትር ንግግራቸው ጠንካራ ነው ፤ ልክ እንደ ጓዳችን፡፡ ትንሽ የሚለዩት በአማርኛቸው ነው፡፡ ያዝ! ያደርጋቸዋል፡፡ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 90/2/ን ተነተኑት፡፡ “ትምህርት ከፖለቲካ ፤ ከሃይማኖት እና ባህላዊ ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት” ይላል አሉ፡፡ በእርግጥ እሳቸው ከ‘ሃይማኖት’ የሚለው ላይ ነው ጠበቅ ያሉት፡፡ ይሄኔ ከጎኔ የተቀመጠው ግንባር ቀደም ጓደኛዬ “what about this” አለኝ፡፡ በዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ፖለቲካ እየሰበኩ እንዴት ነው አንቀጹ የሚነሳው ማለቱ ነው፡፡ የአይኖቼን ቅንድቦች ብቻ ከፍና ዝቅ በማድረግ “እኔም አልገባኝ!” አልኩት፡፡ ክቡር ምኒስትሩ ማጠናከሪያቸውን እስኪበቃው ድረስ እንደ ብረት ካጠነከሩት በኋላ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆነ፡፡

 

የመጀመሪያው ተናጋሪ ‘ማይኩን’ ተቀበለ፡፡ ወደፊት አካባቢ ስለነበር አካላዊ ገፅታው አይታየኝም፡፡ ድምፁ ግን ወፍራም ነው፡፡ “በእውነቱ ዛሬ የተወያየንበት ነገር በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እህ! (ድምፁ ይበልጥ እየወፈረ መጣ) ሥራ አጥነት አገብጋቢ ሆኖብን ፣ ተምረን መውደቂያ እያጣን እናንተ አክራሪነት ትላላችሁ!” ከባድ ጭብጨባ፡፡ ክቡር ሚንስትሩ ገላመጡን፡፡ “ስሙ! ይሄ ጭብጨባ እኮ የደርግ መገለጫ እንጂ የግንባር ቀደሞች አይደለም፡፡ ደርግ ነው በባዶ አዳራሽ የሚያስጨበጭብ፡፡” ሌላም ተግሳፅ አወረዱብንና ለሌላኛው እድል ሰጡ፡፡ ሁለተኛው ተናጋሪ ስሙንና ድርጅቱን ተናግሮ ቀጠለ “እኔም የምለው ነገር ስለ ሥራ ነው፡፡ ሥራ ስጡነ ስንል ‘ኮብልስቶን’ ስሩ ትሉናላችሁ፡፡ የተማረውም ያልተማረውም ‘ኮብልስቶን’ ከሰራ ልዩነቱ ምንድነው?” ደማቅ ጭብጨባ ፤ በጭብጨባው ታግዞ ንግግሩን አረዘመ፡፡ “እናንተ መብታችሁ ተከብሮ ትላላችሁ የትኛው መብታችን ነው የተከበረው? በቀደም ለታ እሁድ ቀን ኳስ ልናይ ከተሰለፍንበት ፌደራል ቀጠቀጠን፡፡ ስንቱን ሽባ አደረገው፡፡ ደሞ… ምን መብት አለነ፡፡” ሌላ ጭብጨባ… “ደሞ ሚዲያዎቻችን ውሸት ብቻ ነው ሥራቸው፡፡ ትናንት በቴሌቭዥን 40 ኩንታል ጤፍ በጭልጋ ተመረተ ሲል ነበር፡፡ እኔ ራሴ የጭልጋ ልጅ ነኝ፡፡ እንኳን 40 ኩንታል አንድ ገበሬ ሊያመርት 4 ኩንታልም የለ፡፡ ይህ ለምን ነው እሚዋሽ? እንዴ! ነውር አይደለም?” አዳራሹ በሁካታ ተሞላ፡፡ የ‘ህዋስ’ አመራሮች ዐይናቸውን ማፍጠጥ ጀመሩ፡፡ የአንዳንዶቹ ጉንጭ የበሰለ ቲማቲም ይመስል ጀምሯል፡፡ ክቡር ሚንስትሩ ድምፅ ማጉያውን አበሩ፡፡ “ጎበዝ! ይሄ እኮ የግንባር ቀደሞች ስብሰባ መስሎኝ ነበር (ትንሽ ፋታ ወስደው)… እና እንግባባ፡፡ አታጨብጭቡ ማለት አታጨብጭቡ ነው፡፡ በቃ!... እንስማማ እንጂ…”

 

ሦስተኛው ተናጋሪ ‘ማይኩን’ ያዘ፡፡ ጀንተል ያለ ነገር ነው፡፡ ነጭ ቦዲው ሰውነቱን አላንቀሳቅስ ብሎታል፡፡ “እኔ በዚህ ውይይት በጣም አዝኛለሁ፡፡ ስለ ‘ኮብልስቶን’ የተባለው እንዳለ ሆኖ የዱሮውን ታሪክ እየበረዝን ፣ እየከለስን የዛሬውን ለማግዘፍ ለምን እንደምንሯሯጥ አይገባኝም፡፡ ይሄ ነገር ድርጅታችን እንዳይንደው መጠንቀቅ ያሻል፡፡ ሌላው ፅንፈኛው ማን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ያን ለመንካት ሌሎችንም በጎን ማሰለፉ ‘አህያውን ፈርቶ ዳውላውን’ ያስመስላል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን በጣም የገረመኝ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ሚኒስትሩ ሲናገሩ ‘የከሰሩ ፖለቲከኞች’ ብለዋቸዋል:: በምርጫ ተወዳድሮ መሸነፍ መክሰር ነው እንዴ? እንግዲህ ኢህአዴግ ላለመክሰር እድሜልክ ይገዛል ማለት ነው? ይህ በጣም ያሳፍራል፡፡ ቃል ብንመርጥ አሪፍ ነው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡” ከእስካሁን የበለጠ ጭብጨባ አዳራሹን ናጠው፡፡ ክቡር ሚንስትሩ መላ መፈለግ ጀመሩ፡፡ እስካሁን የተናገሩት ወደ ስምንት የሚጠጉት (እኔ ሦስቱን ብፅፈውም) ከ‘ብአዴን’ ነው፡፡ ሁሉም ተቃውሞ በዛበት፡፡ “ከዚህ በኋላ ብአዴኖች በቃችሁ፡፡ ሌሎች ድርጅቶች ተናገሩ” አሉን፡፡

 

ሌላኛው ተናጋሪ ማይኩን ተቀበለው፡፡ ስሙን ተናገረ፡፡ ዲፓርትመንቱን አስተዋወቀ፡፡ ወደ ንግግሩ ሊገባ ሲል ክቡር ሚኒስትሩ “ከየትኛው ብሔራዊ ድርጅት ነህ?” አሉት፡፡ እሱም “ኢህአዴግ” አላቸው፡፡ በሳቅ አጀብነው፡፡ ደግመው ጠየቁት ፤ ያንኑ ደግሞ መለሰ ፤ ያንኑ ሳቃችንን ደግመን ሳቅን፡፡ “እሺ ቀጥል አሉት፡፡”… ቀጠለ፡፡ “መወያየት ያለብን ስለዩኒቨርስቲያችን ችግር እንጂ ስለ ፅንፈኛና አክራሪነት አልነበረም፡፡ ደግሞ ለምን እኛ ኢህአዴጎች ብቻ እንወያያለን ሌሎች ተማዎሪዎችስ?...

 

መነፅሩን ያደረገ ፤ የተረጋጋ ወጣት እድሉን አገኘ፡፡ ከ“ኦፒዲዮ” ነኝ አለ፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ተስፋ የጣሉበት ይመስላሉ፡፡ ግንባር ቀደም ቢሆን ብለው፡፡ እሱም እንዲህ ተናገረ፡፡ “እኔ እንደማምነው ርዕሱ በራሱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ብዙ ጊዜ ችግሮቹን ከመፍታት በላይ ችግሮቹን ማስተጋባት ፤ ቀዳዳዎችን ከመድፈን ይልቅ ማድመቅና ማደንቆር ይቀናዋል፡፡ ያምናውን አጀንዳ ነው ዘንድሮም የደገማችሁት፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡”

 

ለዚህ ጽሑፍ የመጨረሻው ተናጋሪ እጁን አወጣ፡፡ ፀጉሩን እንደ ገመድ ገምዶታል፡፡ አገጩ እንደ ቄስ ፂም ቁልቁል የወረደ ፤ አፍንጫው ሰልካካ የ‘ጆርናሊዝም’ ተማሪ ነው፡፡ “እኔ የመጣሁት ከ“ኦፒዲዮ” ነው፡፡ ባይገርማችሁ ምንድነህ? ስባል “ኦፒዲዮ” እላለሁ እንጂ መታወቂያ እንኳን የለኝም፡፡ ለምን እንደማይሰጡኝም አይባኝም፡፡ ሁለተኛ ምንም እንኳን ብኖርበትም የተማሪዎች መማክርት አመራረጥ ትክክል አይደለም፡፡ ፖለቲካና ብሔር ያጠላበት ነው፡፡ እንኳን የተማሪውን መብት ተከራክረው ሊያስከብሩ በራሳቸው መቆም የማይችሉ ናቸው፡፡ እና ኢህአዴግ ለምን በሁሉም ጣልቃ ይገባል? ስለ‘ኮብልስቶን’ የተባለው እኛ ስንመረቅ እሱም ያልቅና ተደራጁና ‘ኮብልስቶኑን’ ውሃ አጠጡ እንዳንባል፡፡” ሳቅና ሁካታ… ንግግሩን ቀጥሎ “ሦስተኛ እኔ የ‘ጆርናሊዝም’ ተማሪ እንደመሆኔ ቅድም ተገልፅዋል፡፡ ኢቲቪ ያሉ ጋዘጠኞች ‘ጆርናሊዝም’ ሳይሆን ‘ጆካይዝም’ ነው ያጠኑት፡፡” ሌላ ሳቅ… “የሚዲያ ኤቲክስ የላቸውም ፤ ሁልጊዜ ውሸት ነው፡፡ ኢቲቪ (1) ሲታረስ ነው የሚያሳየን ፣ ኢቲቪ (2) ሲዘራ ፣ ኢቲቪ (3) ሲከመር ፣ ኢቲቪ (4) ሲሸጥ…፡፡” የሳቁ ንጉስ በላቸው የገባበት ይመስል አዳራሹ በሳቅ ተናጋ፡፡ ከክቡር ሚኒስትሩና ከሴል አመራሮች በቀር ያልሳቀ የለም፡፡ ምናልባት ድርጅታዊ እርምጃ እንዳይወሰድባቸው በመፍራት ሳቃቸውን ያፈኑት ይመስላል፡፡

 

እንደ ምርቃት አንደበተ ርዕቱ ተናጋሪ በተናገረው ልሰናበታችሁ፡፡ “እኔ ለመድረኩ የምጠይቀው ከድሮ እስከ ዘንድሮ ፣ ከአምና እስከ አሁን ሪፖርት ሲቀርብ ‘አንዳንድ… አንዳንድ’ የሚባል ነገር አለ፡፡  እነዛ አንዳንድ እነማናቸው? እነዛንስ ለይቶ መቅጣት አይቻልም? እስከ መቼ አንዳንድ እየተባለ በጅምላ እየተወቀጠ ይኖራል፡፡ ሌላው… ‘ዋሃቢያ’ የሚባል ነገር አለ ወይ? ቢሮ አለው? አድራሻ አለው? ድርጅት ነው? ምንድነው? ግራ ገባኝ እኮ፡፡ እኔ ራሴ ምንድን ነኝ፡፡”

 

የምሳ ሰዓት ደርሷል፡፡ መውጫችን ነው፡፡ ክቡር ሚንስትሩ በጥያቄዎቻችን እንዳልተደሰቱ ያስታውቃሉ፡፡ ከምሳ መልስ መልሳቸውን እንደ‘ላውንቸር’ ሊያምዘገዝጉት እንደሆ ገምተናል፡፡ ከእሳቸው በላይ የህዋስ አመራሮች አምርረዋል፡፡ የስብሰባው መስመር ተስቶ እንደጠበቁት ሳይሆን እንዳልጠበቁት እየሄደ ግንባር ቀደምት የተባሉት ጭራ ቀደም ሆነው አረፉት፡፡ ይሄ ነገር ምን ይመስላችኋል? ተስፋ መቁረጥ ይሆን???

ቸር እንሰንብት

የሻዕቢያ መንገድ

Berket Simon, በረከት ስምኦንተስፋዬ ገብረአብ

 የኤርትራውያን የአረብኛ ፓልቶክ ክፍል በረከት ስምኦንን እንግዳ አድርጎ ጋብዞ ነበር። ጥያቄዎች ይቀርቡ የነበሩት በአረብኛ ቢሆንም፣ የትግርኛ ትርጉም ስለነበረው ሙሉውን ተከታትዬው ነበር። ውይይቱ ሲጨመቅ በሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ዙሪያ ያተኮረ ነበር ማለት ይቻላል።

የመጀመሪያው፣ “የኢትዮ - ኤርትራ ድንበር ለምን አይካለልም? ችግራችሁ ምንድነው?” የሚል ነበር። በረከት የተለመደውን ምላሽ ሰጥቶአል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‘ግንቦት-7ዲ’ን አላምነውም! ለምን?

Ginbot 7ግንቦት-7ያሬድ አይቼህ

የሰሞኑ የዲያስፓራ ፓለቲካዊ ወግ ትኩሳት ወደ ግንቦት-7 አዙሮዋል። ጉዳዩ እንዲህ ነው፦ ግንቦት-7 አባል ነበርን የሚሉ ነገር ግን አሁን ‘ግንቦት-7ዲ’ ሚባል ድርጅት አቋቋምን የሚሉ ሁለት ሰዎች በፓልቷክ የቃሌ ክፍል ዛሬ ቅዳሜ ቃለምልልስ ተደረገላቸው። አስተናጋጁ ኮሮጆ-ኢትዮጵያ ምራቁን የዋጠ መስተንግዶ አድርጓል - ምስጋና ለኮሮጆ-ኢትዮጵያ ይድረሰው። ወደ ጉዳዩ ልመለስ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኳሷ ኢሕአዴግ ሜዳ ላይ ነው ያለችው

አማኑዔል ዘሰላም

ልማት ለአንድ አገር በጣም አስፈላጊ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ሰለጠኑ ከሚባሉ አገራት ጋር ስትነጻጸር ብዙ የሚቀራት ናት። አገራችንን ከድህነት ነጻ ለማውጣት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥም ወደ መካከለኛ አገራ ውስጥ እንድትመደብ ለማድረግ፣ ኢሕአዴግ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይህ ኢሕአዴግ የጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ከመደገፍ ባሻገር፣ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ባላቸው አቅምና ጉልበት የድርሻቸውን ሊያበረክቱበት የሚገባ እንቅስቃሴ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ