የጠፋው ትውልድ እና የታህሪር ናፍቆት-፪

ተመስገን ደሳለኝ (ፍትህ ጋዜጣ - አዲስ አበባ)

ማን ይፈራል ሞት
ማን ይፈራል
ለእናት ሀገር ሲባል

(ይህንን መዝሙር ያደመጥኩት በዘንድሮ አመት የግንቦት ሃያ ዋዜማ ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ1985 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተደርጎ የነበረ የተቃውሞ ሠልፍ ብሎ እንድንመለከተው ከጋበዘን ፕሮግራም ላይ ነው ። የኢቲቪ ዓላማ ‹‹ኢህአዴግ ያሸነፈው ደርግን ብቻ ሳይሆን ስልጣን ከያዘ በኋላ ይነሱ የነበሩ ተቃውሞዎችንም ነው›› የሚል መልዕክት ማስተላለፍ ነው)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትዝታ -  ሀዲስ አለማየሁ ቅኝት -

መስፍን ማሞ ተሰማ

 ሀዲስ አለማየሁየኢትዮጵያ መንግስት በፈረሰ ጊዜ ከራስ እምሩ ጋር ሆኖ ስለነፃነቱ በሚጋደልበት ጊዜ ቆሞም ተቀምጦም ተኝቶም የሚያቃጥለው ያገር ፍቅር ልቡን እየቀቀለው፤ እንፋሎቱ እየገነፈለ አይኑን እንባ እየሞላ ስላስቸገረው በናቱ ስም የኢትዮጵያ ልቅሶ ብሎ ሀዘኑን ለወንድሞቹ ለኢትዮጵያውያን ለማካፈል ሲል በንባው የፃፈልንን የሚከተሉትን ቃላት ለሃሳባችሁ መሰረትና መሪ ይሆኑዋችሁዋል ስንል ተካፋይነታችንን እያረጋገጥንላችሁ ሀዘኑን በጎደለ ሞልተን ፅፈንላችሁዋል ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዋልድባን ከቅርብ ርቀት (ሊያነቡት የሚገባ)

 

(ልዩ ጥንቅር ከአዲስ አበባ)

መንግስት በልማት ስም ቅዱስና ታሪካዊ የሆነውን የዋልድባን ገዳም ተጠግቶ የስኳር ፋብሪካ እገነባለሁ ካለ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ ከአገር አልፎ በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በስፋት ሲያነጋግር ሰንብቷል። ዋልድባ ለክፍለ ዘመናት ታፍሮና ተከብሮ "በጥብቅ" ሀይማኖታዊ ስርዓት የቆየ፣ ፍጹም ልዩ የሆነ መንፈሳዊና ታሪካዊ ዋጋ ያለው ስፍራ እንደመሆኑ በስፋት እየቀረበ ያለው ተቃውሞም በከፍተኛ ስሜት እና ቁጣ የታጀበ ሊሆን ችሏል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠፋው ትውልድ እና የታህሪር ናፍቆት (ሊያነቡት የሚገባ)

ተመስገን ደሳለኝ

(ከርዕሰ ጉዳያችን በፊት ጥቂት ‹‹ስለ ጥቁር ሰው››)
ኢትዮጵያ ሀገሬ የአፍሪካ መገኛ ናት
የነፃነት አርማ የሉአላዊነት
ያናብስቶች ምድር የአርበኞች ተራራ
በአለም አደባባይ ግርማሽ የተፈራ
የጥበብ ምልክት የፍቅር ማደሪያ
ኑሪ ለዘላለም ቅድስት ኢትዮጵያ
ዳግማይ ምኒሊክ፣ ዳግማይ ምኒሊክ
ምኒሊክ፣ ምኒሊክ፣ ዳግማይ ምኒሊክ…

(እነዚህን ስንኞች ያገኘሁት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ጥቁር ሰው›› ለተሰኘው ሙዚቃው የሰራውን የቪዲዮ ክሊፕ (ስዕል ለበስ ሙዚቃ) ከሁለት ቀን በፊት በሂልተን ሆቴል ባስመረቀበት መድረክ ከበርካታ አጃቢዎች ጋር ለበአሉ ድምቀት ይሆን ዘንድ ከዘመረው አዲስ መዝሙር ነው) ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዝርዕትና የእንስሳትን የተፈጥሮ ዝርያ መለወጥ… (አስራደው ከፈረንሳይ)

የሰው ልጅ ቀደም ሲል በእጆቹ፤ ቀጥሎም በቢለዋ እየቆረጠ፤ በማንኪያ እየጨለፈ፤ በሹካ እየወጋ የሚመገባቸው ድንች፤ ቲማቲም፣ ሥጋ፣ አትክሌትና ፍራፍሬ፤ ነገና ተነገወዲያ በተራቸው፤ እራሱን የሰው ልጅ እጅና እግሩን በገመድ ጠፍረው፤ በሳህን ላይ አቅርበው፤ በቢለዋ እየቆረጡ፤ በሹካና በማንኪያ እየጠቀለሉ ሊመገቡት በጠረጴዛ ዙሪያ ቢሰየሙ ምን ይባላለል ? እስቲ ጥቂት ጊዜ ወስዳችሁ ምስሉን በአንክሮ ተመልከቱና እራሳችሁን ጠይቁ! (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

‘የቃሊቲው መንግስት’ – የመጽሀፍ ቅኝት (በሳምሶን አስፋው)

ከሁሉ አስቀድሜ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ይህን “የቃሊቲው መንግስት” የተሰኘውን መጽሃፍ ጽፈህ፡ የታሪክ ማጣቀሻ ሰነዶቻችን አቅም በማጎልበትህ እንሆ ምስጋናዬ ይድረስህ እላለሁ።


እንደ መንደርደሪያ ስለ መጽሃፉ ጠቅላላ ይዘት ፡

የመጽሃፉ የፊት ሽፋን ከፍ ካለ ቦታ ላይ በተደቀነ ካሜራ የተነሳ በ1997 ምርጫ ዋዜማ በአዲስ አበባ ከተማ ቅንጅትን ደግፎ የተሰለፈውን በሚሊዮን የሚገመት ህዝብ ያሳያል። በምስሉ ራስጌ በደመናማው የአዲስ አበባ ሰማይ ባንዲራችን ስትውለበለብ እናያለን። ከባንዲራዋ ዘንግ ስር “የቃሊቲው” መንግስት” የሚለው የመጽሃፉ ርዕስ በቀይ ቀለም ጎላ ብሎ ተጽፏል። በስተ ግርጌ ደግሞ ሰልፍ የወጣውን ህዝብ አንድ ግቢ ውስጥ ያለ ያስመሰለው ያዛገ ቆርቆሮ አጥር ይታያል። (ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ሰሞኑን አዲስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶግራፍ በብዛት በያለበት ይታይ ነበር፤ ያዘነ፣ የተከዘና አንገቱን የደፋ መለስ ዜናዊ! እኔን ቀልቤን የሳበው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አንገት ሊያስደፋ የቻለው ነገር አይደለም፤ ወይም አበበ ገላው የተናገረው ነገር አይደለም፤ አበበ ገላው የተናገረውን ለመናገር ሙሉ መብት አለው፤ በተባለው ነገር የማይስማማ ሰው በማስረጃም ሆነ ያለማስረጃ የተባለውን ለማስተባበል መሞከር መብቱ ነው፤ የአሜሪካኑን ፕሬዚዳንት፣ ወይም የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ ያለ ሁኔታ ቢያጋጥማቸው፣ ወይም በጆርጅ ቡሽ ላይ አንዱ ኢራቃዊ እንዳደረገው ጫማውን እያወለቀ ቢወረውርም ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይኖርም ሙሉውን አስነብበኝ ...