ያለ ጨረታ! ለነ ሌንጮ ለታ?

እንግዳ - ከኦስሎ

መቸም! ተስፋዬ ገብረአብ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም። ”ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም” ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ - በአብዛኛው በአማራና - ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ - የአበሻን - ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል። ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ? ደራሲ ተስፋዬ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከግንቦት እስከ ግንቦት

ተመስገን ደሳለኝ

የካቲት 11/1967 ደደቢት በረሃ

‹‹የትግራይ ህዝብ በብሔራዊ ጭቆና ውስጥ ነው። እናም የግድ ከዚህ ብሔራዊ ጭቆና እና ብዝበዛ ነፃ የሚያወጣው ብሔራዊ ድርጅት ያስፈልገዋል›› (ይህንን መልዕክት የምናገኘው ህወሓት 1967. የካቲት 11 ቀን ወደ በረሃ ለትግል ሲወጣ የአወጣው ማኔፌስቶን በግርድፉ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ነው) ሙሉውን አስነብበኝ ...

መለስ አለምላስ! ”ነጻነትን” ብሎ የጮህው ወገን

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

በሜይ 18 2012 መለስ ዜናዊ በማይዋጥለትና ጨርሶ እስከመቃብሩ ድረስ ሊረሳው የማይችለውን ትምህርት ቀሰመ። በነጻው ሃገር፤ ሃሳብን ያለምንም ገደም መግለጽ በሚቻልበት ነጻ ምድር፤ መለስ አፉ ተለጎመ። ያ ያለገደብ ባሻው መልኩ ስድብና ነቀፌታ፤ ፌዝና ሽሙጥ፤ ተራ ክብረ ነክ ቃላት ሲተፋ የነበረው አንደበቱ ታሰረ። በዋሺንግቶን ከተማ የሚኖረው ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ አበበ ገላው፤ በጂ8 ስብሰባ መሃል ስለ አፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ በተካሄደው ውይይት መሃል ብድግ ብሎ አዳራሹን ባናወጠው ድምጽ ሲናገር መለስ ዜናዊ አይኑ ፈጦ ቀረ። የአበበ ገላው ሃያል ድምጽ አስተጋባ:-

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጨዋታ ወፖለቲካ፡- ‘አንተ’ታ እና ‘አንቱ’ታ!

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. (ከአ.አ.)

ይሄንንስ መቼም እነግራችኋለሁ። “ወሰድ ያደርግሃል እንዴ?” አይለኝ መሰላችሁ። መድኃኔዓለም ይውሰደውና። … አርባ-አራቱ ታቦት ይውሰዱትና! ምናባቱንስና ደግሞ እሱ ብሎ ባለ ዲግሪ! ... እኔማ ልክልኩን ነገርኩት። “አሁን አንተ የማስተማር ዲግሪ ምናምን አለኝ እንዴት ትላለህ?” አልኩት። ልብ-ልቡን አሳጣሁት። “እኔ በግሌ ዲግሪህን ነጥቄሃለሁ!” አልኩና ቁርጡን ነገርኩት። አሃሃሃሃ …!!! ጭራ ሲያበቅል አየሁት። “… ስማ መልስልኝ፣ ምናምን እንዳትለኝ። ስማ! እኔ በግሌ ነው - ነጠቅኩህ - ያልኩህ፤” አልኩት። ይሄንንም መቼውንም እነግራችኋለሁ። …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍርሃት አዶ ከበሬ (አስቻለው ከበደ)

አስቻለው ከበደ

ደርግ ወደ ስልጣን መውጫው ጊዜ ላይ ድሮ ልጅ ሳለሁ አንድ የማይረሳ ትዝታ አለኝ። የጥምቀት በዓል ለማክበር ሄጄ አንድ ነገር ተመለከትኩ። አንዲት እናት የትግሬ ሽሩባ የተቆነደሉ በእጃቸው ረዘም ያለ ዘንግ ይዘው ከታቦቱ ፊት ጥቂት ሰዎች አጅበዋቸው ይሄዳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሥራት አንለይ ትዝታዬና መጽሐፉ

አሥራት አንለይወለላዬ (ከስዊድን) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

... እራሱን የሚገል እራሱን የሚያድን

እራሱን የሚያስጠላ፤ እራሱን የሚሆን።

እኮ በሉ ጎበዝ! ይኸን ሰው እወቁት፤

ሲፈልግ የሚኖር፤ ሲፈልግ የሚሞት፤ ...

አሥራት ለአሥራት

ትምህርት ቤት ለሁለት ወራት ሲዘጋ ለደብተር መግዣ የሚሆነኝ ገንዘብ የማገኝበት ስራ የሚያስቀጥሩኝ ዘመዶች ነበሩኝ። ሁለት ወይም ሦስት ክረምቶች ሰርቻለሁ። በኋላ እንደተረዳሁት ስራው በክረምቱ ወራት እንዳልወሰልት መቆጣጠሪያ ጭምር እንደነበር ልረዳ ችያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊቷን የገደሉ ሶስት የመናዊያን ፍ/ቤት በነፃ ለቀቃቸው … አል-ወሳይቂያ ጋዜጣ

ሀበሻ በየመን

ሀረድ ካምፕ ውስጥ ያሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተላላፊ በሽታ ተጠቅተዋል … የመን ታይምስ ጋዜጣ

ልጄን ማዳን እፈልጋለሁ እርዱኝ … ልጇ የታመመባት እናት

በየመን 14,000 ኢትዮጵያዊያን ችግር ውስጥ ገብተዋል … የየመን ሬድዮ

ግሩም ተ/ኃይማኖት

ሰሞኑን የታተመ አንድ ”አል-ወሳይቂያ” የተባለ ጋዜጣ በአንዲት ኢትዮጵያዊት ላይ የተደረገ ግድያን ምስጢር አጋልጧል። ”እስከሞት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን በሰነዓ” የሚል ርዕስ ሰጥቶ ምንጩ የየመን ሁማን ራይት ሚኒስቴር እንደሆነ ጠቅሶ ዘገባውን ለንባብ ያበቃውን ጋዜጣ ትርጉም እነሆ፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አበበ ገላው እና ሊባክኑ የማይገቡ አጋጣሚዎች (ዳዊት ንዳ)

ዳዊት ንዳ

ባለፋው ዓመት ወጣቱ ቱኒዚያዊ ሞሃመድ ቦዚዝ ራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ሲያቃጥል የቤን አሊ ሥርዓት ያደርስበት የነበረውን ጭቆና በመቃውም እንጂ ሓውልት ሊያስቆም የሚችል ተግባር ለመፈጸም አልነበርም። የርሱ ራስን ማቃጠል የነጋዳፊ መጨረሻ መጀመሪያ ይሆናል ብሎም አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ