አሸባሪነትን” ማን ያገኛታል... ስለ ህዝቡ በፅናት የታገለ አይደለምን?

አቤ ቶኪቻው

ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ? ሁሉ ሰላም ሁሉ መልካም ይሆን ዘንድ አጥብቄ እመኝልዎታለሁ። “አጥብቆ የተመኘ ከሰጠ እኩል ነው” የሚለውን አባባልም እመርቅልዎታለሁ። አንተስ እንዴት ነህ? ካሉኝ፤ የእኔ ነገር እንግዲህ ገና ሚናው ያለየለት ስደተኛ አይደለሁ? አንዴም ሲጨንቀኝ፣ አንዴም ሲጨምቀኝ ብቻ አለሁ እንደምንም፤ እግዜር የሰጠውን ሰው አልችል አይልም! እልዎታለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማን እያሸነፈ ነው? “ቅንጅት” ወይንስ "ሕወሃት/ኢሕአዴግ"? ግርማ ካሣ

የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔው፣ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ይህን አስመልክቶ አጭር አስተያየት የሰጠው አፍቃሪ ኢሕአዴጉ አይጋ ፎረም፣ የቅንጅት ነገር እንዳበቃለት ይናገራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለመሆኑ የከሰረው ማነው?

ዳዊት ከበደ

ሀገሬን ከለቀቅኩ ድፍን አንድ ወር ሞላኝ። በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳትታይ የተፈረደባት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣም ህትመቷ ከቆመ እነሆ አራት ቅዳሜዎች አለፉ። በሽመልስ ከማል የቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመራው አዲስ ዘመን ግን ስድቡን አላቆመም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐበሻ በየመን - ክፍል 5 (ግሩም ተ/ኃይማኖት)

ክፍል 5

ግሩም ተ/ኃይማኖት

Sedet

ማንም የዳስሰው አይመስለኝም። የቀይ ባህር እና ህንድ ውቅያኖስ መጋጠሚያ Gulf of aden አሰቃቂ ጉዞ እና የሱማሊያውያኑን ኢሰብአዊ ድርጊት፣ የእኛም በጉዞ ላይ የዘቀጠ ማንነት.የሚካተትበት ትረካ ነው። መሳፈሪያው ቦታ እስክንደርስ እና ለመሳፈር ባህሩ ጋር ስላለው ነገር ያለውን እንዝለለው። አሁን ምናቦትን አውሱኝ እና የትራንስፖርት ሳይከፍሉ እንጓዝ … ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2011 የፓልቶክ ፖለቲካ ክፍሎች ግምገማ

ያሬድ አይቼህ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

እ.ኤ.አ. በ2011 ፓልቶክ ብቅ ስል ያዘወትርኳቸውን የፖለቲካ ክፍሎች ግምገማዎዬን ይዤላችሁ ስቀርብ በታላቅ ደስታ ነው። ግምገማው የኔ እይታ ነው፤ መቀበልም መስማማትም የለባችሁም፤ ግን አንብቡኝ። አላማዬ በፓልቶክ የመወያያ መድረኮች የሚደረጉትን ገንቢ የውይይት ተሞክሮዎች ለመጠቆምና ለማበረታታት፣ በተጨማሪም ሊሻሻሉ ይገባል ብዬ የማስባቸውን የፓልቶክ የውይይት ገጽታዎች ላይ ገንቢ ትችት ለማቅረብ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐበሻ በየመን - ክፍል 4 (ግሩም ተ/ኃይማኖት)

ክፍል 4

ግሩም ተ/ኃይማኖት

ሰናይት ካቀረቀረችበት ቀና ማለት አሳፈራት ... ልጁ ደግሞ ደግሞ ቢያናግራትም … ቀስ ብዬ አቀፍኳት እና ”... ይህ የህይወት ሂደት ነው መውደቅ መነሳት አለ። ግን ለምን ሰኒ ልጅሽስ? ባልሽስ? እነሱን ጥለሽ ይህ አይነት ህይወት ይሻላል? ለምን ወደ ሀገር አትመለሽም? ...” ብዙ ብዙ ነገር አልኳት። ልጁ አየኝ እና ”እ … ቢዝነስ አግኝተሻል? በቃ አልማዝ ስሪ ...” አለ። ሰናይት ባህሩን ለመሻገሪያ ብቻ አማራጭ አጥታ እንደምትሰራ ነገረችኝ። ”ሳዑዲ ናት የተባለወውስ?። አልኳት። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር

ክንፉ አሰፋ

"እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል... ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።" እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣  የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም ይመስላል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አገሩማ የእኔ ነው… (ከተመስገን ደሳለኝ)

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለመፃፍ ያሰብኩት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ..ጓደኞቼን መልሱልኝ… ብዬ በፃፍኩ በሳምንቱ ማለቴ ነው። ሆኖም በዛ ሳምንት በይደር የማይታለፍ አፋጣኝ መልስ የሚያስፈልገው ጉዳይ አጋጠመኝ። የ..አኬልዳማ.. ፊልም። ስለዚህ ይህን ርዕስ በይደር አልፌው የዛኛውን ሳምንት ለአኬልዳማ ሰዋሁት። እናም ጠቢቡ... ቦ ጊዜ ለኩሉ… እንዳለው ሁሉ እነሆም ጊዜው ሆነና የተዘለለው ርዕስ ተነሳ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አኬልዳማ፤ የደደቢት ደደቦች ድራማ!

ሉሉ ከበደ

ዛሬ በዚህ ጽሁፌ የማነሳው ጉዳይ ወያኔ ሰሞኑን አኬልዳማ  በሚል ርእስ የነዛውን የውሸት ድራማ በተመለከት አንድ ነገር ለማለት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ዛሬ የአለም ህዝብ ወያኔ ማለት ውሸት፤ ሌብነት፤ ክህደት ማለት መሆኑን በመረዳቱ፤ ይህ እየተነዛ ያለው ፕሮፓጋንዳ ማንንም የኢትዮጵያን ህዝብ ያሳምናል ብየ አላምንም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች (ሊያነቡት የሚገባ)

በአቢይ አፈወርቅ

ክፍል ሁለት

የወቅቱ ገናና ቃል ‘ሽብር’ ሆኗል። ሹማምንቱ ሳይጠሩት አያድሩም። ህዝቡም ሲያስበው ውሎ ያድራል… ያልተሸበረ ማን አለ?” ያሰኛል። እውነት ነው ህዝቡ ተሸብሯል። እንግዳውን ቤቱ ለማሳረፍ ተሳቋል። መኪናውን ለሰው ማዋስ የማይታሰብ ነገር ሆኗል።… በዚህ ዘመን ‘ሪፖርት አላደረክም’ በሚል በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቅ የማይችል ነገር ያለ አይመስልም። እድሜ ለ’ጸረ ሽብር’ አዋጁ!... ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ