ለምን ተውኸኝ? ላማ ሰበቅታኒ (በነጋ አባተ)

እውነት ሲሸጥ፤ እውነት ሲሰቀል፤ እውነት ሲደማ የተጮኸ ጩኸት ነበር። ይህ የሰቆቃና የጭንቅ ጩኸትም በአኬልዳማ ተደመደመ። በወቅቱ እውነት እንዲሰቀል ምክኒያት የሆኑ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን የሃይማኖትን ልብስ ለብሰው በማስመሰል ከመቆም ውጭ ከዕውነት ጋር የተቃረኑ፤ ኑሮአቸውና ማንነታቸው በውሸት የተሞላ ነበር። ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጣና እንዲህ አላቸው “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ……እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም ሃሰተኛ የሃሰት አባት ነውና..”እንግዲህ የተውኔቱ ግጭት(conflict) የጀመረው እዚህ ላይ ነው። በዕውነትና በሃሰት መካከል የተከፈተ ጦርነት!። ተውኔቱ ይጻፍ ጀመረ። ጸሃፊዎቹ በጊዜው ወንበሩን በተቆናጠጡትና በሃሰት ጎራ የተሰለፉት የፈሪሳውያን ቡድን አባላት ነበሩ። ሃሰት በዕውነት ላይ ዘመተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግል በአስመራ በኩል፣ ክፍል ሁለት ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ

ግርማ ካሣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. 

መግቢያ

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከግንቦት ሰባቱ መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል የኤርትራ ጉዳይ ይገኝበታል። ኤርትራን በተመለከተ ዶ/ር ብርሃኑ ከተናገሩት የምጋራቸው በርካታ ነጥቦች አሉ። በተለይም የኤርትራ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ትልቅና ስር የሰደደ ታሪካዊ ትስስር እንዳለው፣ በርግጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ የተመረጠ ለሕዝብ ፈቃድ ተገዢ የሆነ መንግስት ቢኖር፣ ከኤርትራ ጋር ያለውንም ሆነ ሌሎች ችግሮችን ለመፍታት በጣም እንደሚቀል በመግልጽ የሰጡትን አስተያየት፣ ምናልባት ከአምባገነኖቹ በስተቀር የማይጋራው ሰው አለ ብዬ አላስብም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ በረከት ምን ነካቸው? ለካስ ጉድ ሳይሰማ የፈረንጆች ገናም አይመጣም!

አቤ ቶኪቻው

የፈረንጆች ገና መጣ። እንንኳን መጣ! የእኛም በቅርቡ ይመጣል። እስከዛው ግን እንኳን ለፈረንጆቹ ገና አደረሰን እንባባል። ያው እንደሚታወቀው አነዚህ ፈረንጆች ገናቸውን ባከበሩ በሳምንቱ አዲስ አመታቸውን ደግሞ ያክብራሉ። ታድያ ይሄኔ እነርሱ አመት ባል ባመትባል ሲደራርቡ እና እረፍት በእረፍት ሲብነሸነሹ ፈረንጅ የያዘው ዶሴ ተሸፈፍኖ መተኛቱ ነውና፤ ከፈረንጅ ጉዳይ ያለው ሰው ቻል ማድረግ ይገባዋል ማለት ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍትህ ጋዜጣ በጫና እና በማስፈራሪያ የሚዝሉ ክንዶች፤ የሚሰደዱ እግሮች የሏትም!

አሁን አደገኛ ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ፍትህን ወደ መቃብር ለመክተት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ የሚሴረው ሴራ እና የሚሸረበው ተንኮል ስጋና ደም ለብሶ እነሆ ከበር ቆሟል። ከረቡዕ (11/04/2004) ጀምሮ በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ፤ እንዲሁም በአዘጋጆቹ ሙሉነህ አያሌው እና ኃይለመስቀል በሸዋምየለህ ላይ መፈናፈኛ የሚያሳጣ ክትትል እየተደረገ ሲሆን፣ ይሄ ርዕሰ አንቀጽ እየተዘጋጀም (13/04/2004) የጋዜጣው ቢሮ በክትትል ቀለበት ውስጥ እንደሆነ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች

(ሊያነቡት የሚገባ!) - ክፍል 3

አቢይ አፈወርቅ

መሐመድ አል-አሙዲ (ሼህ)

የዛሬው ምጥን ፍተሻችን ትኩረት መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ናቸው። እኝህ ሰው ባለፉት 20 ዓመታት ምናልባትም እጅግ አወዛጋቢ ሆነው ከቆዩ ሚና ያላቸው ጥቂት ሰዎች መሀል በአይነታነት መጠቀስ የሚችሉ ሰው ናቸው። በኢንቨስትመንቱ መስክ ወደፊት ከምንፈትሸው በትግራይ ህዝብ ስም በጥቂት የወያኔ ሹማምንት ከሚሽከረከረው ከኢፈርት ጋር ገዝፈው መውጣታቸው ይታወቃል። ከገዥዎቻችን ጋር ባላቸው የጠበቀ ትስስርም በተለያዩ ጊዜያት ስለፈጸሟቸው አጠያያቂ ተግባራት በህዝቡ መሀል በስፋት መነጋገሪያ ነበሩ። በፖለቲካው፣ በሰብአዊ መብቱና በኢንቫይሮመንት ዙሪያም እጃቸውን ምን ያህል እንዳስገቡ እነሆ መረጃዎች እየወጡ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐበሻ በየመን - ክፍል 6 (ግሩም ተ/ኃይማኖት)

ግሩም ተ/ኃይማኖት

ሐበሻ በየመን

ይህን ጽሑፍ በመጽሐፍ መልክ ካዘጋጀሁት ላይ ቦጨቅ ድርጌ ለማስነበብ የወደድኩት ወድጄን አይደለም። አቅሙ ኖሮኝ መጽሐፉን እስከ አሳትመው ድረስ በስደት ከሚያልቁ ወገኖቼ አንድም ሁለትም ከሞት ማዳን ከቻልኩ ብዬ ነው። በሶማሊያ እና በጅቡቲ አድርገው ወደ የመን ሲሻገሩ ባህር ላይ በአመት የሚያልቁትን ከ2000 በላይ ወገን ቁጥር በአንድም ቢሆን መቀነስ ያስደስታል። ያ-ነውና አላማዬ እባክዎትን ስደት ... በተለይ ወደ የመን፣ ሳዑዲ ... በባህር ለመጓዝ ላሰቡ ሰዎች ከመንገር አልፈው ቪዲዮውን ያሳዩልኝ። አንድ ወገን ለማትረፍ እንረባረብ የዛሬ መልዕክቴ ነው። አሁን ወደ ቀጣዩ ጽሑፍ እናምራ …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዲሞክራሲን ያያችሁ? (ክፍል 1)

ሉሉ ከበደ

‘’ንስሀዬ’’ በሚለው ያለፈ ጽሁፌ መለስ ዜናዊ ስልጣኑን ለሽግግር መንግስት እንደሚያስረክብ ቃል ገብቶልናል። ምኞት አይከለከልም፤ የቢሆን ተስፋም ተዘግኖ አያልቅም። ቀጥሎ እንደግዲህ የኛ ተግባር የሚሆነው ከመለስ በሗላ መልሶ እዚያው ጭቃ ውስጥ ይዞን የሚሰጥም ወፈፌ ቡድን መልሰን ስልጣን ላይ እንዳናወጣ፤ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ነው። እንዴት?.. በሽግግሩ መንግስት በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ራሳቸውን አጠናክረውና አደራጅተው፤ ለምርጫ እንዲወዳደሩ የሚፈቀድላቸው ህብረብሄር ፓርቲዎች መጀመሪያ በራሳቸው ውስጥ ዲሞክራሲያዊ አሰራር አለ ወይ? መደማመጥ መቻቻል አለ ወይ? ብለን መመርመር መጠየቅ ይጠበቅብናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በኢሳት ላደረጉት ቃለ-ምልልስ መልስ

ግርማ ካሣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

”... እነ መለስ ናቸው ሕግ። መለስ የፈለገውን ነገር ሕገ ወጥ ነው ካለ ሕገ ወጥ ነው። ይህን አውቀህ ምኑን ነው ታገል የምትለው? ምኑን ነው በሰላማዊ መንገድ ለውጥ አመጣለሁ የምትለው? እርሱ እኔ በፍጹም ትርጉም ያለው እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው ብዬ አላምንም … ጊዜ ማጥፋትና እራስን መሸንገል ካልሆነ በቀር ...” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያልተዘመረላቸው ጀግኖች

የኔሰው ጓንጉል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

”ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ከሰጪው የተለየ ሀሳብ ላለው ካልተሰጠ መብቱ እርባና ቢስ ነው።”

ሮዛ ሉክዘምበርግ ለሌኒን ከጻፈችው ደብዳቤ

ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ እያለሁ ከጠዋቶች ሁሉ የሚናፍቀኝ የቅዳሜው ነበር። የእረፍት ቀን ስለሆነ ወይም አርፍዶ ለመነሳት አልነበረም። ቅዳሜ ጠዋት መኪናዬ ውስጥ ቁጭ ብዬ የ”ካልዲ”ን ማኪያቶ እየተጎነጨሁ፤ ለስላሳዋ ጸሀይ እየዳበሰችኝ፤ ደስ የሚል ሙቀት እየፈጠረችብኝ ”አዲስ ነገር”ን ጋዜጣ ለማንበብ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ