የሒላሪን እውነቶች፤ለኛ ውሸታሞች

ሉሉ ከበደ

ቀኑን በስራ የዛለ ሰውነቴን ላሳርፍ አልኩና፤ የሁለት ዓመት ህጻን ልጄ አልፋን ይዤ ወደ መኝታ ቤት ገባሁ። ደንገዝገዝ ያለ ውሀ ሰማያዊ ብርሀን የሚሰጠውን የመኝታ ሰዓት መብራት አበራሁና በጀርባዬ አልጋ ላይ ተንጋለልኩ። ልጄ አልፋን ከአዲሷ አሻንጉሊቷ ጋር ደረቴ ላይ አድርጌያት፤ እሷም ከደረቴ ወደ አልጋው፤ ካልጋው ወደ ደረቴ እየተመላለሰች ባሻንጉሊቷ ስትጫወት፤ ቀኝ እጄን ግንባሬ ላይ አሳረፍኩ። ትራሴን ከፍ አድርጌ፤ አራት ባራት በሆነችው መኝታ ቤት ውስጥ ከፊት ለፊቴ ግርግዳ ላይ የተሰቀሉ ስዕሎችን እመለከት ጀመር። ከሁሉ ጎልቶ የሚታየው በሀገሬ ባንዲራ ከፈፍ ዙሪያውን ተሰግጦ ያማረው ትልቁ የኢትዮጵያ ካርታ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳውሮ ዋካ ህዝብ ከእንባ ወደ አመፅ

Yenesew Gebre መምህር የኔሰው ገብሬዳውሮ- ከከፋ ክ/ሀገር እስከ ሰሜን ኦሞ

ዋካ (ከስዊድን) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ክፍል አንድ

መግቢያ

ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማና አካባቢው ህዝብ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ አሁንም እንዳለ ነው። አሁንም ዋካ በወያኔ የመከላከያ ሠራዊት ጊዚያዊ ቁጥጥር ሥር ናት። ይሁን እንጂ ውጥረቱ አንድ አዲስ ክስተት አስከተለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይህን ያለው ማነው?

“ትግሬን ወደ መቀሌ!ንብረቱን ወደ ቀበሌ!”

ደረጀ ሀብተወልድ -ሆላንድ

ይህን ጥያቄ፤ ለአንድ ጤነኛ ሰው ቢያቀርቡለት፤”እንደዚህ የሚሉት(ያሉት)፤ለትግሬዎች ጥላቻ ያላቸው  ናቸው”ሊል እንደሚችል ግልፅ ነው።ይህ አያከራክረንም።አከራካሪ የሚሆነው፤እነዛ፤ ለትግሬዎች ጥላቻ ያላቸው፤ እነማን ናቸው?” የሚለው ተከታይ ጥያቄ ነው። ግን.. ይህን ያለው ማን ይመስላችሁዋል? ቅንጅት? የቅንጅት ደጋፊዎች?ህብረት? የግል ጋዜጦች? ወይስ ሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች? “ትግሬን ወደ መቀሌ፤ንብረቱን ወደ ቀበሌ” ብሎ በአደባባይ ያወጀው፤ ህወሀት ቢሆንስ  ምን ይሰማችሁዋል?ምንስ ትላላችሁ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኃየሎም አርአያ አሟሟት… እና በጀሚል ያሲን ላይ የተሰጠ የሞት ብይን (ክፍል 2)

በዳዊት ከበደ ወየሳ - አትላንታ

አንዳንድ ወዳጆቻችን ባለፈው ሰሞን ባወጣሁት የኃየሎም ግድያ ዙሪያ ቅሬታቸውን ገልጸውልኛል። ሆኖም በኔ ውስጥ ያለውና እነሱ የሚሉት እውነት አይገናኝም። ለነገሩ ብዙዎቹ ዘገባዎች ሀገር ቤት እያለሁ ያወጣኋቸው ናቸው። ይሄንን ጽሁፍ ለየት የሚያደርገው ዝርዝር ትንታኔ ውስጥ በመግባቴ ነው። አሄንም ቢሆን በእኔ እምነት ነገሮችን በመሸፋፈን የምንሄድበት መንገድ ሌሎች እውነቶችን እንዳንመለከት ያደርገናል። ምንም እንኳን ጀሚል ያሲን ግድያውን ቢፈጽምም፤ የተደረገበትን ኢሰብአዊ ተግባር አልደግፍም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ ጌታ ነው!

አቤ ቶክቻው

ከዚህ በፊት የሆነ ቀን በዚችው ፍትሕ ጋዜጣ ላይ “ኢህአዴግ ጌታ ነው” የሚል ርእስ ሰጥቼ እና በቃል አጋኖ አጅቤ አንድ ጨዋታ አጫውቼዎ ነበር። አሁንም እላለሁ! ኢህአዴግ ጌታ ነው! ምክንያቱም የምኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ኢህአዴግን እንደ ግል አዳኙ ያልተቀበለ እርሱ የተረገመ ነው። መከራም በላዩ ላይ ይብዛ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ሰማይ ምን አርገዟል? (ተሻለ መንግሥቱ)

አጭር መልእክት መጻፍ አሰኘኝ – ደካክሞኝ ልተኛ ስል። ከበፊትም የነሱና የኛ ታሪኮች መመሳሰል በጣሙን ያስደንቀኝ ነበር። የነሱና የኛ ችግር ተቀራራቢ እንደሆነ በተለይ ካለፉት ስምንትና ዘጠኝ ወራት ወዲህ እነሱ እየደረሰባቸው በሚገኘው የጭፍጨፋና የግድያ የሰቆቃ ኑሮ  መገንዘብ ችያለሁ – የሁለታችንም አሳዳሪ ጌቶች ክፉኛ ጨካኞች ናቸው – ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው። እነሱ እንደሕዝብ በጣም ጠንካሮች ናቸው። እኛ ግን የነሱን የብቃት ደረጃ ለማግኘት ገና በውል ያልተገለጠልኝ  የጊዜ ርዝማኔ የሚያስፈልገን ይመስለኛል። እነሱ የማይቀርላቸውን የታሪክ ዕዳ እየተወጡ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ እና በጨለማ መተኮስ (በሳ.ግ.)

ሰሞኑን በአንድ የአፍሪካ አገር በሚታተምና በዋናነት አፍሪካ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በሚያተኩር www.Africareview.com የተባለ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዜና ርዕስ ስቦኝ ከፍቼ ውስጡን አነበብኩት። ርዕሱ እንዲህ ይላል፦ “Is Ethiopian strongman Meles Zenawi shooting in the dark?”. [i]ማለፊያ ርዕስ ነው። አይነ ግቡ ነው፤ የጽሁፉንም የመከፈት እና የመነበብ ዕድል ከፍ እንደሚያደርገው ግልፅ ነው። ርዕሱ በአቀራረብ ለዛው ጠያቂ ቢሆንም ከምንም ነገር በላይ ግን በጣም ገላጭ እና እውነትነት ያለው ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ።  አዎን አቶ መለስ ዜናዊ አሁን፣ አሁን ወደር በሌለው ጋጠወጥነት(hubris)ከፊት እየመሩ ራሳቸውንም፣ የሚመሩትንም ቡድን ሆነ አገሪቱን የከተቱበት የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ አዘቅት ሊወጡት የሚችሉት እንዳልሆነ  ዛሬ፣ ዛሬ ፍንትው እያለላቸው የመጣ ይመስላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ