የዜናዊ ምስጢሮች

ተስፋዬ ገብረአብ

... ጄነራል ሃየሎም አርአያ በጀሚል ተገደለ … ጄኔራል በርሄ በሚስቱ ተገደለ … የፀጥታው ሹም ክንፈ ገብረመድህን በሻለቃ ፀሃዬ ተገደለ … የፕሮፓጋንዳው ባለሙያ ገብረመስቀል ሃይሉ ታሞ ሞተ … አርቲስት እያሱ በርሄ በድንገት ሞተ …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሁዋላ የበቀለ ቀንድ ጆሮን ይቀድማል (መንግስቴ ደፋር)

ከአቶ/ሮ አዜብ ጌታቸው በጋ . . .  "ኢሕአፓዎች ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አትሁኑ" በሚል ርዕስ የተፃፈውን ጽሁፍ ተመለከትኩት። ከጽሁፍ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፣ ወደ ደጀሰላም ዝክር በአክብሮት የተጠራ ሰው፣ የሚገባውን ያህል ከተቋደሰ በሁዋላ፣ ሂሳብ ለማወራረድ እንደሚታገል ጀብራሬ የተወላገደ የነጠላ ዜማ ቅኝት መሆኑን ብቻ ነው። ብዕርዎ የገዛ ምስልዎን የሚቀርጹበት መሮ መሆኑን ደግሞ አይዘንጉት። “ አንድ አለብህ ይላል ያገር ቤት ዘፋኝ”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሞኙ ጠቅላይ ምኒስትራችን (በገብረ ክርስቶስ ዓባይ)

የጥንቱን የአስተዳደር ሁኔታ፤ የመሪነት ብቃትና ችሎታ ለጊዜው ወድጎን እንተወውና የዘመናዊውን አስተዳደርና የመሪነት ችሎታና ብቃት አሁን ባለንበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆነን ስንመለከተውና የእኛን አገር መሪ ከቀሪው የዓለም መሪዎች ጋር በንጽጽር ስናጤን ጠቅላይ ምኒስትራችን ሞኝ እንደሆኑ ለመረደት እንችላለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሐረር አሁንም ውሃ እንደተጠማች ነው (ጽዮን ግርማ)

ዐፄ  ምኒልክ የመጀመሪያውን የስልክ ጥሪ የደወሉት ወደዚች ከተማ ነው፡፡ የመጀ መሪያው ባንክ የተቋቋመውም በዚች ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያው    የቴምብር ፖስታ የተላከውም ወደዚች ከተማ ነው፡፡የመጀመሪያው ማተሚያ ቤት    የተቋቋመው በዚች ታሪካዋበዚች ታሪካዊ ከተማ ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ አካባቢ ዙሪያዋ በግንብ የታጠረላት ብቸኛ ከተማም ነበረች፡፡ ከተማዋ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነችባቸውን ክዋኔዎች በሙሉ መዘርዘር የዚህ ጽሑፍ ዓላማ አይደለም፡፡ ይሁንና በአጠቃላይ ከተማዋ ካላት የዘመን ቅድምና እና ታሪካዊነት የተነሳ በዩኔስኮ ስምንተኛ ቅርስ ሆና ተመዝግባለች፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኃየሎም አርአያ አሟሟት እውነተኛ ታሪክ እና የጀሚል ያሲን መጨረሻ

(ዳዊት ከበደ ወየሳ - ከአትላንታ)

አንዳንድ ጊዜ የኃየሎም አርአያ ጉዳይ ሲነሳ እንባ የሚተናነቃቸው ሰዎች አጋጥሞኛል። እንባ እየተናነቃቸው ሻዕቢያ ያስገደለው መሆኑን ይናገራሉ። “የለም ኃየሎምን ጀሚል እንጂ ሻዕቢያ አለረገደለውም።” በሚል ንዴት ሊያፈጡባችሁ የሚችሉ ሰዎች አሉ። እኔ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል። እውነተኛውን ታሪክ ስነግራቸው ግን እሳት የሚተፉ አይኖቻቸው እንባ ያዝላሉ።አሁንም ይህንኑ ቃል ብደግመው የሚናደዱ ሰዎች ይኖራሉ። የማውቀውን እውነት እንድናገር ግን ፍቀዱልኝ… ከዚያ የራሳችሁን ፍርድ ስጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓትርያርክ መርቆሬዎስ የት ነሁ? ብጹእ መልከ-ጼዴቅስ?

ካምፓላም ታመመ፡ ታመሰ እኮ !!

ተክለሚካኤል፡ አበበ  (ቶሮንቶ)

የዛሬ አስር ወር አካባቢ ለግል ጉዳይ ወደ ዩጋንዳ ተጉዤ ነበር። አንድ የፌብሩዋሪ 2011 የመጀመሪያ ሰንበት ጠዋት ወካምፓላ መካነሰላም መድሀኔዓለም ቤተክርስቲያን አመራሁ። ባጋጣሚ ከአገልግሎት በኋላ ምርጫ ነበርና አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ሲያደርግ፡ ሪፖርት ሲቀርብና የሰዎች ስም ዝርዝር ቀርቦ፡ ሰዎቹ በቤቱ ሲጸድቁ ታዝቤያለሁ። በሰዓቱ፡ በገንዘብ ሪፖረት እንዲሁም በቀጣይ አመት በጀት ላይ ከተነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች በስተቀር፡ ምርጫውን ተቃውሞ ምንም አይነት የሚያነታርክ ነገር ተነስቶ ሀሳብ ሲሰጥ ወይንም ሲከራከሩ አልተመለከትኩም። እነሆ ጉዳዬን ጨርሼ ወደሰሜን አሜሪካ ከተመለስኩ በኋላ ግን፡ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ብጥብጥ እንደተጀመረና፡ ሰዉ በሁለት ተቧድኖ እየተነታረከ እንደሆነ ሰማሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ