ካየሁት ከማስታውሰው - ልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴ (ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ)

የልዑል ራስ እምሩ ሃይለ ሥላሴን “ካየሁት ከማስታውሰው” እያነበብኩ አስቀድሞ በተመሳሳይ ዘመን ታሪክ ዙሪያ ባጠነጠኑ ኦቶባዮግራፊዎች ላይ ያነበብኳቸውና አልፎ አልፎ ያልተብራሩልኝ አልያም የደበዘዙብኝ ግዙፍ የታሪክ ሁነቶችንና ደግሞም እማላውቃቸውን ክስተቶችን ራስ እምሩ እያፍታቱ፤ እያበራዩ፤ እየገላለጡ … ሲያወጉ ባገኛቸው ጊዜ፤ ነፍስያዬ ተመስጣ ጣቶቼም ገፅን በገፅ እያጣፉ ስፈተለክ፤ ስሜቴ ደግሞ አንዴም በአግራሞት፤ አንዴም በመቆዘም…ይናወጥብኝ ነበር። እንዴትና ለምን? ብሎ መጠየቅ መቼም አግባብ ነው። መልሱንም በሁለት ቃላት መቋጨት አይከብድም - መጥ ፉን ማንበብ - በሚል። ካየሁት ከማስታውሰው - (ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ)

ምክር ያልሰማ ንጉስ ፤ አሟሟቱን ሲያረክስ

ሉሉ ከበደ

ኖቬምበር 5 / 2006 ሳዳም ሁሴን በሞት እንዲቀጣ ሲፈረድበትና ዲሴምበር 30 / 2006 ሲሰቀል  ለስቅላቱ ፍርድ ዋና ወንጀል ሆኖ የቀረበው የክስ ጭብጥ፡ የሚቃወሙት የሺአት ሙስሊሞች በ1982 የመግደል ሙከራ ካደረጉበት በሗላ 148 ቱን ገድሏል ነው። ሚሊዮንም ሰው ይግደሉ፤ አምስት ሰው ይግደሉ፤ የሞት ፍርድ ለመቀበል ሁለትም አስርም በቂ ነው። እንደ አገዳደሉ አይነት። ምርጫ 97 ላይ የኛ ጌታ ንጉስ መለስ ጀግናው ከሁለት መቶ በላይ ግዳይ ጥሏል። ስምንት መቶውን አቁስሏል። ማንም ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም በሰላም ለተቃውሞ ሰልፍ ወጣ እንጂ። የሰረቃችሁት ድምጼን መልሱ ብሎ። ይህ ገዳይ ነፍሱ በእስር ላይ መሆንዋን ህሊናው ያለ እረፍት ይነግረዋል:: ይጮህበታል። የፍርዱ ቀን ገና አልታወቀም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አክሱማዊነትን ያልተረዳው አክሱማዊ - (በውቀቱ ስዩም)

አስተሳሰብህ የሰፈር
አጨዋወትህ ለማፈር
ሁኔታህ ሁሉ ባዳ ነው
አንተን ማስቀመጥ ዕዳ ነው።
ተመስገን ተካ 1990 ዓ.ም.

ሰሞኑን የጌቶቻችንን የትጥቅ ትግል ታሪክ የሚዘግቡ መፃሕፍት ታትመው እየወጡ ነው፡፡ በአብዛኛው ተመሳሳይ ናቸው። የተዋጋነው ዴሞክራሲ ለማስፈን፣ ጭቆናን ለማስወገድ፣ ብሄረሰቦችን እኩያ ለማድረግ ስንል ነው የሚል ይዘት አላቸው። ማንም አንጋፋ ታጋይ፣ ያማረኝን ለመብላት፣ ጄት የሆነ መኪና ለመንዳት፣ የእሥር ቤት ቁልፍ በእጄ ለማስገባት ስል ነው የተዋጋሁት ብሎ እንዲተርክልን አንጠብቀውም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወያኔዎች ተይዟል ከተባለው የኡጋንዳ ቤተ ክርስቲያን ጀርባ ያለው እውነታ

ዕለተ ሰንበት ነው፡፡ ቀኑ ጥቅምት 5 ቀን 2003 ዓ.ም (ኦክቶበር 16) ነው፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንደሚያደርጉት ሁሉ በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፖላ የሚገኙ አማኞችም ራሳቸው ወዳስገነቡት ቤተክርስቲያን በማለዳ መትመም ይዘዋል፡፡ አብዛኛው ምዕመን የተለመደውን የቅዳሴ አገልግሎት ከመካፈል ባሻገር በሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫ የመሳተፍ እቅድ ይዞ ነው ወደ ቤተክርስቲያን የሄደው፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ከምርጫው ዕለት አንድ ቀን ቀደም ብሎ በሞባይል አጭር የጽሁፍ መልዕክት (ኤስ.ኤም.ኤስ) በደረሳቸው መልዕክት ተደናግጠው እና ተቆጥተው ጉዳዩን ለማጣራት የመጡ ናቸው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ