መፍትሄው አንድ ብቻ ነው

አንዷለም አራጌ

በዚህ በሠለጠነው ዘመን በኢኮኖሚ፣ በፍትሕና በዴሞክራሲ ከፍተኛ እመርታ በአስመዘገቡ አያሌ የዓለማችን አገሮች መሀከል በርካታ የአፍሪካ አገሮች ሕዝብ በጥቂት አፄዎች የጭቆና ቀንበር ሥር እየማቀቀ ይገኛል። ጭቆናው በጥቂቶቹ ላይ ደግሞ እጅግ የከፋ ነው። ከጥቂት እጅግ የከፋ አፈና ከተንሰራፋባቸው አገሮች መካከል ደግሞ ግንባር ቀደሟ አዛውንቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀዳሚተ ሰንበት ከዳዊት ከበደ ጋር (ከሲያትል)

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን በዝና አውቀነው ቆይተን ነበር። ወደዚህች ምድር በነጻ ፈቃዳችን እንኖር ዘንድ የላከን እግዚያብሔር ፈቅዶ ይሄው በአሲምባ ሬስቶራንት ተገናኘን። አሲምባ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የአንድ ትልቅ ተራራ ስም ነው። በዚህ ተራራ ስር ሀገራቸውን ነጻ ለምውጣት ሲሉ የቀደሙ ወንድሞችና እህቶች የመሸጉበት ታሪካዊ ስፍራ እንደሆነ ሰምተናል። ይህ ታሪካዊ አምባ ተረስቶ አልቀረም ይሄው በፈረንጆቹ ሀገር የአንድ ግሩም ሬስቶራንት መጠሪያ ሆኗል። በዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን አግኝተን በብዙ ጥያቄ ጠየቅነው። ከእሱም ጋር በላን ጠጣን ደስም አለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ... ከዚኽ ወዴት? ክ.15 (አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አምስት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በአዘጋጅ ኮሚቴው በኩል ከታሰቡባቸው መሰረታዊጉዳዮች አንዱ ድኢርጅቶች ወደዚህ ጉባኤ እንዲመጡና በመሪዎቻቸው አማካኝነት እንዲወከሉ ሲጠየቁ እነሱ በተናጠል ተገኝተው የመሰላቸውን መልእክት አስተላልፈው የሚለዩበት ወይንም 'ይሄንን ለመወሰን ውክልና አልተሰጠኝም፣ አማክሬ ልምጣ፣ ወ.ዘ.ተ' በሚል መንገዋለልና ጊዜ ማባከን እንዳይኖር ከወዲሁ የየድርጅቱ አባላት በጉዳዩ ላይ የመምከር እድል እንዲኖራቸውናእንዲያገኙ በማድረረግ ላይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ... ከዚኽ ወዴት? (ክ.14 አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አራት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በዚኽም መሠረት ምንም እንኳን ድርጅቶች በተናጠል የሚያደርጉት ትግል በተባበረና በተቀናጀ መልክ መሆን ይችል ዘንድ የጋራ ብሔራዊ ግንባር (ትብብር) እንዲመሠረቱ በብዙ ቅን-አሣቢ፣ ዴሞክራትና አገር-ወዳድ ወገኖች በኩል ሙከራዎች ያልተቋረጡ ቢሆንም በተለይ ኢአጉ ከተመሠረተበት ከሰማንያ ዘጠኝ ዓ.ም. ጀምሮ ድርጅቶች የትግል ግንባር እንዲፈጥሩ የእንቅስቃሴው ዋና ነጥብ (አጀንዳ) አድርጎ መያዙና ያላሰለሰ ጥረት የእንቅስቃሴአቸው አካል አድርገው ማየትን አላቆሙም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አረ ጎበዝ…! ኢትዮጵያ ከጃችን ማምለጧ ይሆን?!!

አትክልት አሰፋ (ከቫንኩቨር-ካናዳ)

ያሁኖቹ ቱጃሮችማ በቅጡ ይታወቃሉ። ብዙ ህዝብ መሀል ጣል ጣል ያሉ ስለሆኑ በደንብ ይታያሉ፤ አዲስ አበባም ሆነ ዋና ዋና የክ/ሀገር ከተሞች፤ ገጠርም ብትገቡ የማን ንብረት ምን እንደሆነ፤ የማን መኪና ታርጋ ቁጥር ለማን እንደተሰጠ፣ የማን ቤት በምን አይነት እምነበረድ እንደተሰራ፣ ዝርዝር አድርገው የሚነግሯችሁ አሉ። ህዝቡ ሁሉን ዘርዝሮ አውቃል። ያሁኖቹ ጉዶች ደግሞ ይሉኝታ እንኳን የላቸውም፣ የጄኔራል ማዕረጉን የደረደረ ወታደር መሀል አዲስ አበባ ላይ ቆሞ ቤት ሲያሰራ ታያላችሁ፤ ሚኒስተሩ ትላልቅ ካሚዮን የሚገዛው ከአብራኩ በወጣች ልጁ ስም ነው፤ ሌላም አለ… ቀዳማዊ እመቤቲቱም አስር ቦታ የምታስጀምራቸው ቤቶች ጠሀይ ሞቆታል። ወሎ ሰፈር አካባቢ ታስገነባለች በሚባለው ህንጻ የጦር ሰራዊት የጭነት መኪና የሚገለብጠው አሸዋና ሲሚንቶ… ከሰው አይን ሽፋሽፍት የራቀ አይደለም። ልቀጥል ነው …።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

... ኢህአዴግ ከዚህ ወዴት? (ክ.13 - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ ሦስት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

አደረጃጀትና አወቃቀርን ከመሳሰሉ መሰረታዊ ችግሮች በተጨማሪ፣ በአንድ በኩል በተለይ በውጭ ሀገር በሚገኙ ኢተፖድኀ አባል ድርጅቶች መኻል የሻቢያ እብሪታዊ ወረራ ተከትሎ በተከሰተው ልዩነት፣ በሌላ በኩል በኢተፖድኅና በተገር ውስጥ በሚንቀሳቀሰው በደቡብ ህብረት አመራር መኻል በተፈጠረው እየተካረረ የሄደ አለመግባባት ምክንያት ኢተፖድህ በተመሰረተበት መንፈስና ባቀደው የትግል መስመር እድገቱን ጠብቆና የቆመበትን መርህ ተከትሎ መጓዝ አልቻለም። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

በየመን ዩኤንኤችሲአር ያስገነጥላል፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያጨበጭባል

አምላክሥራ ግሩም

ለአንዳንድ ጉዳይ ወደ UNHCR ቢሮ ጎራ ስል ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ የቢሮው ብልሹ አሠራር ያናድደናል - ለኢትዮጵያዊያን። ሰሞኑን እንኳ የስደተኛነት ማረጋገጫ ማንዴቴ ላይ ስሜ ሲጻፍ የቃላት ግድፈት አስተካክሉልኝ ብዬ አንድ የዘለሉዋትን ፊደል ለማስተካከል 10 ቀን ነው ያመላለሱኝ። ሙሉ ስሜን ቢሆን ስንት ወር ያመላልሱኝ ይሆን? ይህ ታዲያ ለኢትዮጵያዊያን ነው። ኢራቂ ከሆኑ መስተንግዶው ፈጣን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓትና ፒራና

ግርማ በላይ

በትግርኛ ”ጠዓመኒ ድግመኒ” የሚባል አነጋገር እንዳለ አውቃለሁ። በአማርኛም ”ጣመኝ ድገመኝ” የሚል አይኖርም ብዬ አላስብም። ባለፈው ከኢትዮሚዲያ የአንድ ሰው ጽሑፍ ተነስቼ ስለወያኔ ዛፍ የሞነጫጨርኩዋት ወረቀት በሰደድኩዋት አብዛኛው ቦታ ስላየሁዋት ብርታት ሰጠችኝና አሁንም ኪቦርዴን አነሳሁ - ’ብዕር’ እየቀረ አይደል?! ስንት ዘመን ለፍቶ ሲያበቃ ኪስ ማሞቂያ ሆኖ መቅረቱ ግን ትንሽ ቅር ማሰኘቱ አይቀርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቁጩ አማሮችና የ30ኛው ዓመት በአላቸው (ወንድሙ መኮንን)

ወንድሙ መኮንን - ከለንደን

ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ኑዋሪውን ወገናችንን ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠረ ገምቶ እብሪት ቢሰማውም፣ ህዝኢባችን በወያኔ አስተዳዳር ላይ ያለውን ምሬት ያከፍርሀት ከመግለጽ ወደኋላ አላለም። ታዲያ ይሄ ህዝብ የናቀ የማፍያ መንጋ ውጭ ሀገር የምንኖረውንም ለመቆጣጠር ባለው ህልሙ መሰረት፣ በሚኒስተር/ካውንስለር ወይም ያ በሌለበት ሀገር በአንደኛ ጸሀፊ የበላይነት ወያኔ ኢምባሲ መሰረቱ/ቤዝ ያደረገ በሺ የሚቆጠሩ ለሆዳቸው ያደሩ የሰላዮች ቡድን በየዋና ከተማው አስገብቶ ያሰማራና ሊያጠምደን እንደተዘጋጀ ከአሁን በፊት በአማአርኛ "ዘመነ ወያኔ ዘመነ ጨለማ" ርእስ ጽፌ በኢትዩሚድያ፣ በኢትዮጵያ.ኦርግ፣በኢኤምኤፍ፣ አዲስ ቮይስ ድረ ገጾች መበተኔ ይታወሳል። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያዊያን መከራ (ክፍል-5 በነብዩ ሲራክ)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ሐጅ ወቅት ላይ ሆኖ ስለ ሮመዳንን ማውራት ሊከብድ ይችል ይሆናል። በዚህ ቀጣይ መጣጥፍ ቅኝቴ በኢትዮጵያዊያን የሳውዲ ዐረቢያ የኑሮ ታሪክ አስከፊ የነበረውን አጋጣሚ ማዘከር ነው። ለዚህም ለሆነው ሁሉ የቅርብ ምስክር ነበርኩና ከማስታወሻ ያሰፈርኩትን የተደበቁ እውነቶችን ወጋወግ ጊዜና ወቅት ሳይገድበው እያነሳሁ ብጥለው አትፍረዱብኝ! ቀኑ ሳይታሰብ መሽቶ ይነጋል። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)