የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ሀገር ወዳድና ... ኢህአዴግ ከዚህ ወዴት? (ክ.12 - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ ሁለት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ፣፬፦ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረት (ኢተፖድሕ)፣ ፓሪስ ሁለት ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው ደርግ ሲወገድ የህዝባችን ምኞትና ጥባቆ ለዝንታለም ቀስፈው የያዙት የአመረባገነን ስርአቶች አዙሪት እንዲያከትምና መሰረታዊ የሆኑና ስር የሰደዱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የወል ችግሮቻችን በሰከነ ሀገራዊ የእርቅና ሰላም ሂደት የሚፈቱበት መንገድ ይመቻች ይሆናል የሚል ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የከዘራው ትንቢት አልተፈፀመም እንዴ?

ይሄይስ አዕምሮ

ትናንት ማታ የድረ ገጽ ዜናዎችን ሳነብ ያየሁት አስገራሚ ዜና በሌላ ጉዳይ ላይ ልጽፍ ተነሳስቼ የነበርኩትን ሰውዬ ወዲያውኑ አስለወጠኝ። ብቻየን በሳቅ ስንከረከር የራሴው የሳቅ ማሚቶ እንደገና እያሳቀኝ በቶሎ ላቆም አልቻልኩም - አስመሸኝ። የወያኔ ገልቱ ሥርዓት እንዴቱን ያህል የወዳጆቹን ብቻ ሳይሆን የጠላቶቹን ጭምር አንጀት በሚበላ አሳዛኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ስገነዘብ እኔ ራሴም ሆዴን ባር ባር አለው፣ ክፉኛ ተንቦጫቦጨለት፣ ሲያልቅ አያምር አሉ። የምሬን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ብሩንም ገደሉት (ነፃነት ዘገዬ)

ነፃነት ዘገዬ

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ዶ/ር እሌኒ ስለምትባል ወጣት ኢትዮጵያዊ ምሁር ሲያቀብጠኝ በእንግሊዝ አፍ ጽፌ በላክሁት ጦማር ሳቢያ በደረሰብኝ የሞራል ውድቀት ላለፉት ብዙ ጊዜያት አንገቴን ደፍቼ ምንም ሳልል ቆይቻለሁ። አሁን ግን ”እስከመቼ ኩርፊያ?” ብዬ ተደፋፈርኩና ብዕሬን አነሳሁ። የሚገርመው የት ጠፋ ብሎ አንድም ሰው አልጠየቀኝም። እንዴህ ነን እንዴ ለካ? ትዝብት ነው ትርፉ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ አለንጋ እጅ ባሜሪካ

ይነጋል በላቸው

በ”ሠላም ለሁላችሁም!” ጀመርኩ ይህችን አጭር አስተያየት። የአቶ ዘውገ ፋንታን ሐተታ (በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ስለ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሣ የክብር እንግዳነት ምርጫ የወሰደው ፖለቲካዊ አቋም) አነበብኩ። ሀገራችን የገጠማትን ዘርፈ ብዙ ችግር እያሰላሰልኩም ብዙ ተከዝኩ። የወያኔም እጅ ምን ያህል ረዥም እንደሆነ ታሰበኝ። ለነገሩ በብሂሉ ”አለንጋ ጣት” ነበር የሚባለው፤ ግን ነገርን እንዳደረጉት ነውና ”አለንጋ እጅ” አልኩና ተነሳሁ። ዳሩ ዛሬ ዛሬ ምን ባለበት ቆሞ ያለ ነገር አለና ልጨነቅ? ሁሉም ነገር ሊያውም በአሉታዊ መልኩ እየተለወጠ አይደል ያለ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የስደቱ “የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ”

ስለ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሣ የክብር እንግዳነት ምርጫ የወሰደው ፖለቲካዊ አቋም

ዘውገ ፋንታ (የፌደሬሽኑ የቀድሞ ቦርድ አባል)

መግቢያ

በውጭ ያለው ማንኛውም የኢትዮጵያኖች ማህበራዊ ድርጅት፣ በሀገር ውስጥ እንዳለው ድርጅት ሁሉ በተዘዋዋሪ ወይም በቀጥታ በወያኔው መንግሥት ቁጥጥር ስር ካልሆነ በስተቀር ለመቀጠል እንዳይችል ውዝግብ እየተፈጠረ ስለሆነ ሕብረተሰቡ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን መረዳት ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱት ጋዜጦች እንዲሁም ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፉት የዜና ማሰራጫ መስመሮች መንግሥታዊ ድርጅት የሆነው የአሜሪካ ድምፅ ሳይቀር አምባገነኑ መሪ በአሜሪካ ምድር ቆሞ በድፍረትና በንቀት ያገዳቸው መሆኑን ለአሜሪካ ሕዝብ አሰምቷል። ኢትዮጵያኖች በየትኛውም ሀገርና ምድር የሕብረተሰብ ጉዳያቸውን ያለሁከትና ብጥብጥ ለማካሄድ ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል። የኢትዮጵያ ሀብት ለወገኖቿ ጥፋት ስራ በየሀገሩ እየተረጨ መሆኑ ግልጽ ነው። ወያኔ መጨቆኛ ሴራ-ድሩን ለማስፋፋት ሲል የኢትዮጵያ ወገኖችን ለሌላ ጨቋኝ ዘረኞች አሳልፎ እየሰጠ መሆኑንም መረዳት ያስፈልጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መድረኩ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ከጥቂት ሣምንታት በፊት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ አምስት ገጾች የያዘ መግለጫ አውጥቷል። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አደገኛ ሁኔታ ላይ እየወደቀ እንደሆነ የገለጸው መድረክ፣ ኢትዮጵያ ወደ አንድ ግለሰብ አምባገነንነት እያመራች እንደሆነም በመግለጫው ያትታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

... ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? (ክ.11 - አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስራ አንድ

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ) አመራር፦ ቀደም ሲል እንዳየነውና ወደፊትም እንደምንመለከተው ለማንኛውም የተናጠልም ሆነ የጋራ ትግል መሳካት ወይም ውድቀት አመራር ቁልፍ የሆነ ሚና አለው። በመሠረቱ የትግል ድርጅት አመራር ሰጭ መሆን ከፍተኛ ኃላፊነት ስለሆነ በኅሊና ተገዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት እንጂ የግል ጥቅም የሚገኝበትም ሆነ አጉል ዝና የሚፈለግበት ሹመት ተደርጎ መታዬት አይኖርበትም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብአዴን ለአማራው የመጣለት ወይስ የመጣበት

ቻሌ ተሾመ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የአማራውን ክልል በመምራት ላይ የሚገኘው ብአዴን የተባለ የህወሓት ጥላ ድርጅት የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት በተመለከተ በዋሽንግተን ዲሲ በሞቀበት የሚዘፍኑ ሚዲያዎች ማስተጋባትን ይዘዋል። በተለይ በዚሁ ድርጅት ቀድሞ ታጋይ የነበርን የሚሉ የትግል ውሉና ጉዞው የጠፋባቸው ተጋባዦች የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ አቶ ተድላ አስፋው ”Ethiopian Movement Vs Amahara national” በሚለው የእንግሊዝኛ መጣጥፋቸው በመዳሰስ ከኢትዮጵያዊ ስም ወደ ክልላዊ ስያሜ የተቀየረበትን ምክንያት በትክክል አስቀምጠውታል ብዬ አስባለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በብርቱካን ስም መወጋገዝና መለያየት ይቁም!

ግርማ ካሣ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

”ከፌዴሬሽኑ ጀርባ ልንሰለፍ ይገባል” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ጽሁፍ፣ እጅግ በጣም በርካታ ምላሾች በኢሜል ደረሱኝ። ኢሜሎቹ በሙሉ የተቃውሞ ኢሜሎች ናቸው። አንዳንዶቹ ከመቃወም አልፈው ስድብና ዛቻም አዝለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወ/ት ብርቱካን፣ ፌዴሬሽኑና ደንቡ

ክንፉ አሰፋ (ከአምስተርዳም)

“በዋሽንግተን ዲ.ሲ. እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽ በዓል ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። እኔ እዚህ አለሁ፣ ተጫዋቾቹም እዚሁ አሉ፣ ግን ህዝቡ የት እንደገባ ለማወቅ ጓጉቻለሁ።” ስትል ነበር አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አሊሻ ፔተርሰን የ2008ቱን የዋሽንግተን ዲ.ሲ. የፌዴሬሽኑን ውድቀት የዘገበችው። ፔተርሰን “ሰው ሁሉ የት ገባ?” ብላ ለጠየቀችው ጥያቄ ምላሽም በዘገባዋ አካትታለች። በዓሉ ከኢህአዴግ መንግሥት ጋር ቁርኝት ባለው በሼክ አላሙዲ ስለተደጎመ በህዝቡ “ቦይኮት” እንደተደረገ በቪዲዮ የተደገፈ ምስል ጋር ቀርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...