ፕሬዝዳንቱም፣ ጠቅላይ ምኒስትሩም፣ ሕገ መንግሥቱን አያውቁትም

ይገረም አለሙ

Pres. Dr. Mulatu Teshome and PM Hailemariam Desalegne

ፕሬዝዳንት ሙላቱ በዘንድሮው ፓርላማ መክፈቻ ንግግራቸው አንዳንድ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉ ገልጸዋል። የመንግሥቱን ሥልጣን በበላይነት የሚቆጣጠሩት ህወሓቶች የገጠማቸውን የሕዝብ ተቃውሞ ለማስተንፈስ ያስችለናል ያሉትን፤ ግን የማይፈጽሙትን የማሻሻያ ርምጃ ጽፈው ሲሰጡዋቸው ከማንበባቸው በፊት ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ሊያገናዘቡ በተገባ ነበር። አንደኛው በአምናው የመክፈቻ ንግግራቸው ከተናገሩት ያልተፈጸሙት ይልቃሉና የማተገብሩትን ተናገር እያላችሁ ቃል አባይ ፕሬዝዳንት አታድርጉኝ ማለት፤ ሁለተኛው ደግሞ የተባሉት ማሻሻያዎች ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚነገሩ ሳይሆን በርግጥ ታምኖባቸው ተፈጻሚ እንዲሆኑ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ከሆነ፤ አንዳንዶቹ ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መንገድ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እናደርጋለን የሚል በንግግራቸው እንዲካተት ማድረግ ይገባቸው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እማማ አለብላቢት - የዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ነቀርሳ

Emama aleblabitሸንቁጥ አየለ

በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በአንድ ሰፈር ይኖሩ የነበሩ፣ እማማ አለብላቢት የሚባሉ ሴትዮ አጭር ታሪክ እና የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሥነልቦናን ትስስር ሁሌም ይገርመኛል። የሰፈሩ ልጅ ሁሉ እማማ አለብላቢት ብሎ ይጠራቸው ስለነበረ ታሪካቸውን በዚሁ ስማቸው እንተርከዋለን።

እማማ አለብላቢት በሰፈራቸው ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ነገር አይጥማቸውም። አንድ ሰው አዲስ ልብስ ለብሶ ቢወጣ "ኤዲያ" ብለው ያጣጥሉበታል። አንድ ሰው በሬ ቢገዛም ያጣጥላሉ። ሌላው ሚስት ቢያገባ ወይም ልጅ ቢወልድ ያጣጥሉበታል። ሠርግ እንኳን ተጠርተው እንዲበሉ እንዲጠጡ ተጋብዘው ሳለ የርሳቸው ዋና ሥራ ሠርጉን ማጣጣል ነው። "ኡ ኡ እቴ ...!" ብለው ጀምረው ሁሉንም አሉታዊ ቃላት ያዘንቧቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ ዳመነበት እንጅ አልመሸበትም

ፍትሕ ይንገሥ (የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ሁኔታ ከሚያሳስባቸው ዜጎች አንዱ)

ከሁሉ በፊት አንባቢያን ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ይህ ፅሁፍ ጥናት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን ነው። መነሻው በዋነኛነት የግል ትዝብት ሲሆን ከሌሎች የኢህአዴግ ደጋፊዎችና ገለልተኛ ሊባሉ ከሚችሉ ወገኖች ጋር የተደረጉ ውይይቶችም ውጤት ጭምር ነው። ለማንኛውም ግን ፅሁፉ ላይ የተነሱትን ችግሮች በተመለከተ ኢህአዴግ እንደተለመደው የተከላካይ (defensive) መንፈስ ይዞ ባያያቸው ይመረጣል። ይልቁንም የተነሱት ችግሮች አሉ ወይስ የሉም ብሎ በቅንነት ቢያያቸውና ራሱን ቢፈትሽ ያጠናክሩታል እንጅ ለጉዳት አይዳርጉትም። ይህን ለማድረግ ደግሞ የግድ የሮኬት ሳይንስ ማጥናት አያስፈልግም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በ40 ሚሊየን ብር ያለአግባብ ግዥ ሊጠየቁ የሚገባቸው ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነን ለሚኒትርነት ማዕረግ?

Prof. Yifru Berhaneከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሠራተኞች አንዷ

ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም.፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በድጋሚ ያቋቋሙትን ካቢኔ ከአንድ ዓመት ጊዜ ቆይታ በኋላ በማፍረስ እንደ አዲስ ያደራጁትን አዲስ ካቢኔ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ለሕዝብ አሳውቀዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካዋቀሩት ካቢኔ ውስጥ አብዛኞቹ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጡ መሆናቸው እስከ አሁን ካለው አወቃቀር ልዩ ያደርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እውነተኛ "አማራጭ ኃይል"

Young and old generationዮፍታሔ

ከሚነገረውና ከሚጻፈው በላይ የማይነገረውና የማይጻፈው እየበለጠ ነው።

በተቃዋሚዎች መካከል በውጭም ሆነ በአገር ቤት፣ በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ የሚካሄደው ሽኩቻና መገፋፋት በአረጋውያኑ እና በወጣቱ መካከል የሚካሄድ እየመሰለ ነው።

አረጋውያኑ ዘንድ ስም፣ ልምድና የውጭ ግንኙነት አለ። ወጣቶቹ ዘንድ አፍላ ኃይል፣ ቴክኖሎጂና የውስጥ ግንኙነት አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልዕክት፤ ለኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ መስራቾች

Ethiopian National Movement meetingይገረም አለሙ

የተቀዋሚዎች ብዛት የርስ በርስ ሽኩቻና የጎንዮሽ ትግል ለወያኔ ዕድሜ መርዘም ዋናው ምክንያት መሆኑ አሌ የማይባል ነው። የድርጅቶቹ ዓላማ ሳይሆን የመሪዎቹ ፍላጎት አይታረቄነት ተባብሮ ለመሥራት የማያስችል ሆኖ ውሾቹም ይጮኻሉ፣ ግመሉም ይሄዳል እየተባለ ሃያ አምስት ዓመት ዘልቀናል።

በተግባር እንዳየነው ለፓርቲዎቹ መብዛትም ሆነ ለመተባበር አለመቻል ዋናው ችግር የአደረጃጀትና የትግል ስልት ወይም የዓላማና ግብ ልዩነት ሳይሆን፤ የትግል ጽናትና ቁርጠኝነት አለመኖርና ከሚነገረው በስተጀርባ የተደበቀ የመሪዎች ፍላጎት መኖር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ"ጥልቅ ተሃድሶ" ድራማ ተጀምሯል!

Ethiopian parliamentክንፉ አሰፋ

በቤተ ሙስና፣ የ"ጥልቅ ተሃድሶ"ው ድራማ ተጀምሯል! የእርስ በርስ እና ራስን በራስ መተካካት ቧልት እና ፌዝ።

ከመጋረጃው ጀርባ ስብሃት ነጋ፣ አቦይ ጸሃይ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ደብረጽዮን እና በረከት ስምኦን የሚቆምሩትን ካርታ፤ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደቬጋስ አጫዋች ፊት እያመጣ ይዘረጋዋል። በዲዮጋን ያደረጉት አብዮታዊ እና ልማታዊ "ምሁራን" ፍለጋ ውጤት ነበረው። "የዶክተር ያለህ" ፍለጋ ጥቂት ታማኝ አገልጋዮችና፣ በርካታ ሮቦቶችን አስገኝቷል። "በዲሞክራሲ" በተመረጠው "የሕዝብ ምክር ቤት" የሚኒስትሮቹ ስም ይፋ በሆነ ግዜ፤ ለይስሙላ እንኳን ተቃውሞ፣ አልያም ድምጸ-ተአቅቦ ቢያደርግበት ድራማውን ያሳምረው ነበር። በሙሉ ድምጽ ጸደቀ ተባለ። የነዚህ ሮቦቶች ምርጫ የፍልፍሉን ቀልድ ያስታውሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የለውጥ ኃይሎች” ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል (ክፍል ሁለት)

Ermias Legesseኤርሚያስ ለገሰ

ጆቤ እንኳን ደህና አልመጣችሁ!!

ለህዝብ ውይይት መድረክ የተዘጋጀ (ሂውስተን/ቴክሳስ)

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ራዲዮ(ኢሳት)

ጥቅምት/2016

ማስታወሻ

ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም።

መግቢያ

“የለውጥ ኃይሎች ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል” በሚል አቢይ ርዕስ ተከታታይ መጣጥፍ እየቀረበ ነው። ከዚህ ቀደም “በክፍል አንድ” በተሰራጨው ጽሁፍ ሁለት ቁምነገሮችን ለመዳሰስ ተሞክሯል። የመጀመሪያው፦ ግልጽና ደፋር ውይይት የምናደርግባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለመዘርዘር ተሞክሯል። ዛሬ አገራችን ያለችበት ሁኔታ የሚያሳስበው ዜጋ ባለመኖሩና አገር አደጋ ላይ በወደቀችበት ሁኔታ በመተማመን ላይ የተመሰረተና የጋራ ድል (win- win) በሚያረጋግጥ መልኩ ምክክር መካሄድ እንዳለበት የተገለጠበት ነው። መጣጥፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ መምጣት አለበት በማለት የሚንቀሳቀሱት ሁሉም የለውጥ ኃይሎች የዛሬና የነገን ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ በሚወስኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ምን እንደሚያስቡ ለህዝቡ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚጠይቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተባበረችውን ኢትዮጵያን በጋራ እንገነባለን!

ገለታው ዘለቀ

We build ONE Ethiopia!

በቅርቡ በአንድ የኦሮሞ ወገኖች ስብሰባ ላይ አንድ ሰውየ፤ “ኦሮምያ ሰላም የምታገኘው ኢትዮጵያ ስትፈራርስ ነው፤ ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት” አለ ተብሎ ሲራገብ እያየን ነው። እኔ በግሌ የዚህን ሰው ተልዕኮ ለመረዳት ቅንጣት ጊዜ አልወሰደብኝም። ከራሱ ከወያኔ በቀጥታ መልዕክት እየተቀበለ የሚሠራ የወያኔ ተቀጣሪ ነው፤ ወይም እያጃጃሉ በስልት የሚጠቀሙበት ሰው ነው። አለቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“መፍራትና መጠንቀቅ ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው ሀገር የሚያፈርሱትን ነው”

Ethiopian flagይገረም አለሙ

ከአሥራ አምስት ዓመት በፊት ነው ኢዴፓ በቅሎ ቤት በሚገኘው ጽ/ቤቱ ዕለተ ግንቦት 20ን አስመልክቶ አንድ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ተገኝተናል። ከተናጋሪዎቹ አንዱ የነበሩት የወቅቱ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ባደረጉት ንግገር ውስጥ፤ “መፍራትና መጠንቅ ካለብን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው እኛኑ መስለውና ተመሳስለው ሀገር የሚያፈርሱትን በመካከላችን የሚገኙትን ነው” የሚለው አረፍተ ነገር በአእምሮየ ተቀርጾ አብሮኝ ይኖራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ