በጎሣ ትግል ወያኔ አይወድቅም፤ ቢወድቅም ውጤቱ አያምርም

መሳፍንት ዘፈረንሳይ ለጋሲዮን

Stop shouting

በኦሮሚያ ተቀጣጥሎ ወደተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለተዛመተው ሰላማዊ የፍትሕ ይገባኛል ጥያቄ፤ የግድያና የእስራት ምላሽ እየሰጠ ያለውና በቅርቡም ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የእምነት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኀንና ዲፕሎማቶች ሳይቀሩ የመብት እንጥፍጣፊ እንዳይኖራቸው “በባርነት አዋጁ” የደነገገው የወያኔ ሥርዓት፤ ለሩብ ምዕተ ዓመት ሲሠራ የቆያውንና አሁንም እየሠራ ያለውን ሁሉ ያስተዋለ በሀገራችን የተከሰተውን ስር የሰደደ የፖለቲካ ቀውስ መረዳት አያዳግተውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሰመጉ ከየት ወዴት?

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

አምስት ዓረፍተ ነገሮች

ኢሰመጉ መንፈሳዊ ተልዕኮ ያለው መንፈሳዊ ድርጅት ነው፤ ዓላማው በሰው ልጆች መሀከል የሚከተሉትን ተልዕኮዎች መዝራት ነው፡–

1.1. እኩልነትንና ነጻነትን
1.2. ፍቅርንና ስምምነትን
1.3. ፍትሕንና ሕጋዊነትን
1.4. ሰላምንና ማኅበረሰባዊ እድገትን
1.5. የእውነትንና የእውቀትን ብርሃን ማስፋፋትን

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድ ጉድ ልንገራችሁ!

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

አንድ ጉድ ልንገራችሁ!

ያለፈው እኁድ የዱሮው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ኢሰመጉ (ዛሬ በግድ ስምን ለውጦ ሰመጉ የተባለው) የሃያ አምስተኛ ዓመት በዓሉን ለማክበርና በዚያው እርዳታ ለመሰብሰብ በደሳለኝ ሆቴል የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ነበር፤ ኢትዮጵያውያንም የውጭ ሀገር ሰዎችም ነበሩ፤ ፕሮግራሙ ሲካሄድ ቆይቶ አንድ ሰዓት ያህል ሲቀረው ፖሊሶች መጥተው ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ አዘዙ፤ ተቋረጠና ወደየቤታችን ሄድን! ስብሰባው የተደረገው አስፈላጊው ፈቃድ ሁሉ በጽሑፍ ከተገኘ በኋላ ነበር፤ ምናልባት ፈቃጆቹና ከልካዮቹ አይተዋወቁም ይሆናል!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ዓይናችን እያየ አትፈርስም!

Jawar Mohammedአቤ ቶኩቻው

ይቺ ሚጢጢ የአቋም መግለጫ ናት ብላችሁ አስቡ ... አንዳንድ ዕድሜ የተጫጫናቸው ስደት እና አሰልቺ ትግል የሀገራቸውን እና የህዝባቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ያስረሳቸው ... ግለሰቦች እና ድርጅቶች ኢትዮጵያን አፍርሰን እኛ እንቆማለን ሲሉ እየሰማን ነው ... (እስቲ ማሉልን! ... በሳቅ ነው የምታፈርሷት!? ወይስ በመረጃ ልትቆፍሯት ነው!? ... !?)

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፀጉረ ልውጦች በፍራንክፈርት

በልጅግ ዓሊ

እህ ዛዲያማ
በአንድ ጎጆ
እህ!
አንድ ቁርንጮ ይነጠፍና
እህ!
አዋጅ በይፋ ይታወጅና
እህ!
ኃይል ያደራጃል ደግሞ እንደገና
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ትለኛለህ?
ከየመንገዱ ሰብሰቦ ሲያስርህ
አይደለም እንዴ ገድሎ ሊጥልህ።
. . .
ወለላዬ

እነሆ ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አለወትሮዋ በፀጉረ ልውጦች ከተሞላች ሰንበትበት አለች። ሀገራችን ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ ያስፈራቸው የወያኔ ጀሌዎችና ደጋፊዎች የተነሳውን እሳት ለመሸሽ በመዘየድ ወደ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ በተራቸው መፍለስ መጀመራቸው መሆኑ ነው። ይህ ትዕይንት የወያኔ ዘመን ሊያከትም መዳረሱን ጠቋሚ ክስተት ነው። ዛሬ በመካከላችን የምንሰማው ዱካ፣ በዓይናችን የምንቃኘው ወዛም ገጽታ፣ በየሱቁ የምናስተውለው ግርግር፣ የባለሥልጣን፣ የቱጃር ሚስቶችና ልጆች፣ እንዲሁም ዘመዶችና ቁባቶች መሆናቸውን አንዳች የሚያሳብቅ ነገር አለው። እንደው በጥቅል አነጋገር በከተማው ውስጥ በሰፊው የሚታዩት እነሱ ስለመሆናቸው ብዙ ዋቢ ማቅረብ የሚያስፈልግ ከቶ አይመስለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በተለይ ለኦሮሞ ልሂቃን የተላከ ማስታወሻ

Oromo protestነፃነት ዘለቀ

መድኃኒት ከምን እንደሚሠራ አለማወቃችን በጄ እንጂ፤ ብዙ ፈዋሽ መድኃኒቶች የሚቀመሙት ከመርዝና ብዙም ከማንወዳቸው ነገሮች ነው። ግን መዳን ስላለብን ሐኪምና ዐዋቂ እንድንወስዳቸው የሚመክሩንን የሚቀቡም ሆኑ የሚዋጡ መድኃኒቶች አለማመንታት እንወስዳቸዋለን። በቤታችንስ ስንቶቻችን ነን የገዛ ሽንታችንን የምንጠጣ? አዎ! መድኃኒት ነው ከተባለ የጅብ ጉበትም ይበላል፤ የአህያ ወተትም ይጠጣል። ዋናው ከሚያሰቃየን ደዌ መፈወሱ ነው። “ምንም ቢያስቀዝን ጮማ” ብሎ ነገር በጭንቅ ወቅት አይሠራም። አሁን ያለንበት ሀገራዊ ድባብም እንዲሁ በጣም አስጨናቂና አሳሳቢ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ

ዩሱፍ ያሲን

Gonder protest

1. ኢትዮጵያ በለውጥ ዋዜማ

በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ቀጣይነት ሊኖረው የሚችል ሁኔታ አይደለም (Unsustainable) ሲባል ሰንበትበት ብሏል። አንድ ሐሙስ ቀረው እየተባለ መነገር የጀመረው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። የሥርዓቱ ዕድሜ ካንድ ሐሙስ ይልቅ ከላይ ወደ ዜሮ በሚደረግ የኋሊት መቁጠር የሚዳዳቸው ታዛቢዎቹም አሉ። በፈረንጅኛው Count Down የሚሉት ስሌት መሆኑ ነው። እንደ ተለመደው ኢትዮጵያ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ ቆማለች፣ በመንታ መንገድ ላይ ናት መባሉ እንደገና እየተዘወተረ መጥቷል። ሁሉም ግን ኢትዮጵያ ወዴት? የሚለውን ጥያቄ እያስጨነቀው ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ መቆሟ አያነጋግርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማኅበራዊና የሕብረተሰብዓዊ ጥያቄ ወይም የብሔር/ብሔረሰብ ጥያቄ?

”እባብ ወተት ጠጥታ መርዝ ትተፋለች፣ ቅዱስ ግን መርዝ ጠጥቶ ወተት ይተፋል!“ Azmuto

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

The question of nationality

መግቢያ

አሁን ያለንበት ዘመን 21ኛው ክፍለ-ዘመን ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ ብዙ የምዕራብ አውሮፓ ሀገሮችና አሜሪካንንም ጨምሮ፣ እንዲሁም ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ፣ ዛሬ ደግሞ ቻይና በሳይንስ አማካይነት የቴክኖሎጂ ምጥቀትን በማግኘት አነሰም በዛም የተረጋጋ ሕብረተሰብ ለመገንባት ችለዋል። በተለይም ባለፉት 40 ዓመታት የተፈጠሩትና ገበያ ላይ የዋሉት ቴክኖሎጂዎች ቀደም ብለው ከነበሩት ቴክኖሎጂዎች ጋር ሲወዳደሩ በጥራትም ሆነ በምቾት እጀግ ተሽለው የሚገኙ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቦይ ዘባረቁ? ሰምሃልስ?

እንግዳ ታደሰ ከኖርዌይ

Aboyi Sibhat

ያንን ገለባ ልጅ ከደጅ የወደቀው
አድራሻህ ወዴት ነው ብለህ አትጠይቀው
የነገው ነፋስ ነው መንገዱን የሚያውቀው።
በዕውቀቱ ስዩም

ጥቅምት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. የሸራተን አዲስ የላሊበላ አዳራሽ ቲያትር ቤት መጋረጃ ለተደራሾች ተገለጠ። ሁለት መቶ ሃምሳ ታዳሚዎችን ባጨናነቀ ሁኔታ የትያትር ቤቱ አዳራሽ ሞልቶ ነበር። ”በዲሞክራሲያዊ ግንባታ ችግሮች ላይ የተሰነዘሩ ምልከታዎች” በሚል መርሃ ቃል በአቶ በረከት ሰምዖን መርሃኤ ተውኔት አዘጋጅነት፣ በልደቱ ተዋኝነት የተካሄደ ስብሰባ። አዳራሹን ያለስሙ ቲያትር ቤት ያልኩት ጠፍቶኝ አይደለም። ከወሎዋ ላሊበላ ምድር፣ እስከ ሸራተኑ የላሊበላ አዳራሽ ድረስ እነኝህ ሁለት ሰዎች እንዴት እየተደጋገፉ እንደሚያቄሉን ስለገረመኝ ነው ቲያትር ቤት ያልኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ በተዘጋጀ መድረክ ተቀዋሚዎች ምን ይሠራሉ?

ይገረም አለሙ

Lidetu Ayalew (M) and Bereket Simon (L)

የፖለቲካ ድርጅት የመገናኛ ብዙኃን ባለቤት እንዳይሆን የሚከለክለውን ሕግ በመተላለፍ ወያኔ ያቋቋመው ፋና ሰሞኑን አንድ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። ውይይቱን በቀጥታ ስርጭት ሳይሆን ለእኛ ይገባቸዋል ብለው የመጠኑልንን አቀናብረው አስተላልፈውልን ተመልክተነዋል። ጽሁፍ አቅራቢዎቹ ተወክለው ይሁን ወክለው ባይታወቅም ከምሁራን ከባለሀብት ከተቀዋሚና ከኢህአዴግ ተብለው ነው የቀረቡት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ