ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግሥት

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeይድነቃቸው ከበደ
ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግሥቱ የፀደቀበት ቀን ነው። ይህንንም ተከትሎ በመንግሥት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!!

ዳዊት ከበደ ወየሳ
ተጨማሪ ማስታወሻዎችና ከኢትዮጵያ የወሰዱት ሽጉጥ መጨረሻ
የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር - ዋናው ዜና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ሁለት

Ethiopian foodፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው። ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማንዴላ ለኢትዮጵያዊነት - ቤዛ ነበሩ!

ኔልሰን ማንዴላ Nelson Mandelaመራራ ስንብት - ከመብራታችን ጋር ...
ሥርጉተ ሥላሴ

በዘመነ ወያኔ የተከበሩ ማንዴላ የተስፋዬ ሀገር የሚሏትን ሀገርና ህዝብ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵውያንን ሳያዩ አረፉ። ስለ ምን? ለጥቁሮች የተፈሪነት ፍጹም ልዩ ዓርማ የሆነችውን የሀገራችንን ቀደምትነት፤ ያን የአፍሪካዊ የጥቁር ገድል፤ የቅኝ ግዛትን ቀንበር በምኞት ያስቀረ የፈካ ታሪክ በዕብሪትና በበቀል የጣሰው የወያኔ ሓርነት ትግራይ ማንፌስቶ አልተመቻቸውም ነበርና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውይይት ከአቶ ደበበ ጉሉ፣ ዳንኤል ጥላሁንና ተክለሚካኤል አበበ ጋር

በሳውድ አረቢያ ይኖሩ በነበሩ እጅግ ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተደራራቢ እስራት፣ ወከባ፣ እንግልትና በኢትዮጵያዊያት ሴቶች እህቶቻ ላይ አስገድዶ መድፈርን ያስከተለ ስቃይ ሲደርስ ሰንብቷል። መቆሚያ ጊዜውም በውል አልታወቀም። የእነኝህን ኢትዮጵያዊያን ስቃይ በሚመለከት ቫንኩቨር ካናዳ በየሳምንቱ የሚተላለፈው መለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ ከአቶ ደበበ ጉሉ፣ ዳንኤል ጥላሁንና ተክለሚካኤል አበበ ጋር ውይይት ተደርጓል። የመንግስት ሚና፣ በውጭና ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎና ጥረት፤ ውጤትና ቀጣይነት ይዳሰሳሉ። ውይይቱ Dec 30, 2013 የቀረበ ነው

የኢሕአደግና የግንቦት ሰባት ድርድር

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ Dr. Berhanu Negaግርማ ካሳ

"የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ለግንቦት ሰባት የእንደራደር ጥያቄ አቀረበ" ሲል ኢሳት ሰበር ዜና አሰማን። ዶ/ር ብርሃኑ ነጋንም በማቅረብ በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡም አድርጓል። ምንም እንኳን የቀረበውን ዘገባ ከሌላ ምንጭ ማጣራት ባይቻልም፣ ዜናው እውነት ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ግን ይሰማኛል። አገዛዙ ከኦብነግ፣ ኦነግ ከመሳሰሉ ጋር ድርድር እየጀመረ፣ የማቋረጥ ልማድ እንዳለው ታሳቢ በማድረግ። የግንቦት ሰባት "እንደራደር" ጥያቄም ከዚያ የተለየ አይሆንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሳውዲ አረቢያው ቀውስ ለዲያስፖራ ፍቅርና አንድነት ሰጥቷልን?

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al Mariamፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ)
በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ልዩ የሆነ ትኩረት እንዲሰጡትና ለወገኖቻቸው የማያቋርጥ ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምስራቅ ኢትዮጵያ ፖለቲካ

 ተመስገን ደሳለኝ - ከአዲስ አበባ

…አውሮፕላኑ ቅዳሜ ጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ደርሶ ከተርሚናሉ ስወጣ፣ ተጠራጥሬ ሰዓቴን ተመለከትኩ፤ የድሬ የጠዋት ፀሐይ ከተለመደው ንዳዷ ጋር የአዲስ አበባን የቀትር መራራ ፀሀይን ታስከነዳለች፤ እናም አጥበርባሪ ጨረሯን ያለምህረት ስትለቅብኝ፣ ጓደኛዬ መኪና ይዞ እቦታው እስኪደርስ መጠበቁ በገዛ ፍቃድ መለብለብ ስለመሰለኝ፣ በቀጥታ ከተደረደሩት ታክሲዎች አንዱን ይዤ ወደ ከዚራ አመራሁ፤ ድሬ የሄድኩት በዋናነት ከማህበራዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት በመሆኑ ሊቀበለኝ የተዘጋጀውን ጓደኛዬን ደውዬ ከማውቃቸው የአንዱን ሆቴል ስም ጠቅሼ እዚያ እንድንገናኝ ነገርኩት፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር

ክንፉ አሰፋ
በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግልጽ ደብዳቤ ለሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/የሱስ

በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አስመልክቶ "ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ" ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር አድሃኖም ገብረየሱስ የጻፉትን ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ልከውልናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ