በደም የተገነባ ተቋም
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ
ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በኀዘን ሲመታ፣ ደመናው ሲጠለሽ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ፤ የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው ... የክፉው ቀን ጅማሮ፣ የውርደት ሃሌታ፣ የሀገር አልባነት ስሜትና የዜግነት ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ
ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በኀዘን ሲመታ፣ ደመናው ሲጠለሽ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ፤ የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው ... የክፉው ቀን ጅማሮ፣ የውርደት ሃሌታ፣ የሀገር አልባነት ስሜትና የዜግነት ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሄኖክ የሺጥላ
የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ከአዲስ አበባ 483 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉ-አባ-ቦራ (Eloo The father of Holstein Friesian) ኢልባቡር ከተማ በሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ስኩዌር ሜትር ይዞታ ላይ ሥራውን እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ1993 ማከናወን የጀመረ ትልቅ የቢራ ማምረቻ ድርጅት ነው። ኢሊባቡር መልካም ምድራዊ አቀማመጡም ሆነ ምድራዊ ልምላሜው፣ እንደ በቆሎ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ የቅባት እህሎች፣ ማር፣ ከነ ቦራ ደሞ ወተት፣ ቅቤ እና ወዘተ የሚዘራባት፤ የሚታጨድባት፤ የሚቆረጥባት፤ የሚታለብባት ሀገር እንድትሆን አድርጉዋታል።
ግርማ ካሳ
በሕዝብና በሀገር ላይ ጥቃት ሲሰነዘር የሀገሪቷ መሪ ህዝቡን የመምራትና የማረጋጋት ኃላፊነት አለባቸው። ሳዑዲዎች በኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግፍ በፈጸሙ ጊዜ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ከመምራት ይልቅ ዝምታን መርጠው፣ አንዴ በካታር፣ ሌላ ጊዜ በፖላንድ ሲሽከረከሩ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ነው። "ጠ/ሚኒስትሩ የት ነው ያሉት?" የሚል ጥያቄና ትችት እየጠነከረ በመጣ ጊዜ፣ ከሣምንታት በኋላ ብቅ አሉ። በኢቲቪ ቃለ መጠይቅም አደረጉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የሥልጠና ክፍል አምስት ግብ በዐፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት (1924 -1967)፣ በደርግ ዘመነ መንግሥት (ከ1967 - 1983)፣ እንዲሁም በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት (1983 - 2002) የተደረጉትን ምርጫዎች በአጭር በአጭሩ መጎብኘት እና መገምገም ነው። ምርጫ 97 ግን በርከት ያሉ ትምህርቶች በመለገሱ ሰፋ አድርገን እንጎበኘዋለን። (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚኽ ይጫኑ!)
በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት (አንድነት) በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ ክፍል አራት በአቶ ግርማ ሞገስ በስካይፕ የሚሰጠው ሥልጠና ተጠናቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከእየሩሳሌም አርአያ
ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር።
በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡-
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በአበራ ለማ (ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ባለቅኔ)
አንጋፋው የዲሞክራሲና የለውጥ አርበኛ አበራ የማነአብ የሰባ ሁለት ዓመት አዛውንት ናቸው። ከዚህ ዕድሜያቸው ውስጥ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥት ባፈላማ ይዟቸው ሃያ አምስቱን ዓመታት በዓለም በቃኝና ወህኒ ቤቶች ቀርጧቸዋል። ከዚህ ውስጥ ባመክሮ ጥቂት ዓመታት አራግፈው አስራ ስድስት ዓመት ከስምንት ወራት በህሊና እስረኝነት አሳልፈዋል።
ግርማ ካሳ
በፌስቡክ የሚጽፋቸውን እየሰበሰቡ አንዳንድ ድረ ገጾች ያስነብቡናል። በመቀሌ ነው የሚኖረው። ወጣት ነው። አብርሃ ደስታ ይባላል። የሚያምንበትን ከመናገርና ከመጻፍ ወደኋላ አይልም። በቅርቡ ከጻፋቸው አስተያየቶች አንዱ፣ ልቤን ማረከው። እኔም በዚያ ላይ ጨመር ለማድረግ ፈለኩ።
አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት ወደ ኋላ (ክፍል ሁለት)
ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያሰፈነ ስላለው የፍርሃት ባህል ቀደም ሲል ባሰራጨሁት የዚህ ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ባለሙያዎች በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ለፍርሃት ባህል መስፈን መንሰዔዎች ያሏቸውን ነጥቦች ዘርዝሬ ነበር።