ከኬኒያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ምን እንማራለን?

ታምሩ ገዳ

ህዝባዊ ምርጫዎች በመጡ ቁጥር ስልጣኑን እነማን ይርከባሉ? ምርጫው ምን አዲስ ነገር ይፈጥርልን ይሆን? ምርጫው ሰላም ወይም አለመረጋጋት ... ወዘተ ይቀሰቀስ ይሆን? የሚሉ መሰል ጥያቄዎች በበርካታ መራጮች አይምሮ ውስጥ መመላለሱ የተለመደ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአባይ ግድብ ዙሪያ

ግርማ ካሳ

ቋጠሮ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ አንድ ቪዲዮ አየሁ። በሪያድ ሳውዲ አረቢያ፣ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢትዮጵያውያንን ጠርተው፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ ባነጋገሩበት ወቅት፣ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው። «መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም»፣ «የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 27 ይከበር» የሚሉ መፈክሮች የተጻፉባቸው ነጭ ወረቀቶች ሲውለበለቡ ይታያሉ። ስብሰባው በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ፣ ለአባይ ግንባታም በቂ ገንዘብ የተሰበሰበ አይመስልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህወሓት ፍጥጫ ቀጥሏል

"አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው" እነ ስብሃት
"የህወሓት ወራሾች እኛ ነን" እነ አባይና አዜብ

ኢየሩሳሌም አርኣያ
ሁለት ቦታ የተከፈለው የህወሓት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም "መለስ ህወሓትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ህወሓት ቆዳ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ስም ማጥፋት

በዲሴምበር 2011 "ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር" በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር። በዚያን ወቅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔና እምነት

ቸሩ ላቀው

በመንግሥት አመራር ላይ የተቀመጡ ቡድኖችና በኃይማኖት አመራር ላይም የተቀመጡ የኃይማኖት መሪዎች በየፊናቸው የሕዝብን አደራ በኃላፊነት ተቀብለው በሀገሪቱ ባለው ሕገ መንግሥትና በኃይማኖቱ ሕግ መሠረት በሐቅና ለሕቅ ብለው ምለውና ተገዝተው ሕዝብን ለማገልገል የተቀመጡ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቡዳዎቹ ሠፈር የትኛው ነው?

ወልደማርም ዘገዬ

የቀድሞው ኢትዮጵያዊ የአሁኑ ኤርትራዊ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኃኔ "ኤርትራ እንደ እናት አገር፤ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም" በሚል ርዕስ በአውሮጳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ጥር ወር 2013 የጻፉትን ጥናታዊ ዘገባ በፍላሼ አሰንብቼ ዛሬ ጧት ቁርሴን አወራረድኩበት። ኤርትራ ለእርሳቸው የምታስጨንቀውን ያህል ኢትዮጵያም - ባለቤት ያጣችዋ ከርታታዋ ኢትዮጵያም ለእኔ እንደእናት ሀገር ታስጨንቀኛለችና የተሰማኝን ልናገር ብዕሬን አነሳሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚሳናቸው የለም

ቸሩ ላቀው 
ሿሚ፣ ሻሪ፣ ሀገር መከፋፈልና መገነጣጠል የነርሱ ተግባር ሆኗል። መለስን ሾሙብን፣ ሀገርን ገንጥለው ኢሳያስ አፈወርቂን ኤርትራን ይዘህ ራስህን ቻል አሉት። ከመለስ ሹመት ጋር ኢትዮጵያን በጎሣ ከፋፍለው እያወደሟትና እያደቀቋት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወላጆችና መሪዎች

ቸሩ ላቀው
ለዚህ የተቀደሰ ተግባርና ከባድ ኃላፊነትን ለሚጠይቅ ሥልጣን መታጨት ያለባቸው የሀገር መሪዎች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች በርካቶች ቢሆኑም በኔ እይታ አንዳንዶቹን ከወላጆች ጋር እያስተያየሁ ለመጠቃቀስ እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድንቄም ምርጫ!

ይኸነው አንተሁነኝ
ላንዲት ሀገር መሰረታዊ የእድገት ኃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው። የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብቃት ለመገንባት ደግሞ ካሏት የትምህርት ተቋማትና የትምህርቱ ሥርዓት በተጨማሪ በሕዝቦቿ መካከል ያለው የባህል፣ የኃይማኖትና የአኗኗር መስተጋብር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦና በዚሁ ሳቢያም የሚገኘው ቀጥተኛ ያልሆነ የእውቀትና የልምድ አቅምና ዝውውሩ የሚናቅ አይሆንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህወሓት ጉዞ የርስ በርስ መበላላት ታሪክ ነው

ትዕዝብት አድማሱ
የትግራይ መሳፍንት እርስ በራሳቸው ሲናቁሩና ሲገዳደሉ ያየች አንዲት የጎጃም አዝማሪ ስታንጎራጉር "ጎጃሜ ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ፣ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ" በማለት ትልቁ የታሪክ ጠባሳ በአንዲት ዓረፍተ ነገር አጠቃለለች ይባላል። ይህ የትናንት ታሪክ ነው። ዛሬስ ምን እየተደረገ ነው ያለው?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ