የመለስ ... ጉዞ - "ሸውራራ ብትኳል ለትዝብት" (አረጋዊ በርሀ)
አረጋዊ በርሀ (ዘሔግ)
በቅርቡ “መለስ ዜናዊ እና የህወሓት የትግል ጉዞ” በሚል ርዕስ፣ ፀሐፊ ኢያሱ መንገሻ (ኮ/ል) ተብሎ፣ ባለ 313 ገፆች አንድ መጽሐፍ መጋቢት 2002 ዓ.ም. አዲስ አበባ ታትሞ ወጥቶ፤ ከጫፍ እስከ ጫፍ አነበብኩላቸው። መጽሐፉ አቶ መለስን ልዩ የታሪክ ካባ ለማልበስ ሲባል ብዙ የተደከመበት የፈጠራ ቅንብር መሆኑ ገና ከሽፋኑና ከመቅድሙ ያስታውቃል። ለዚሁም በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከባህል ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በሸራተን ሆቴል ደግሰው ነሐሴ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. መርቀውለታል። ፀሐፊው ኮ/ል ኢያሱ መንገሻ ይባል እንጂ፤ በዚህ የፈጠራ ቅንብር የአቶ መለስ እጅ በእጅጉ እንዳለበት ብዙ ጠቋሚ ነጥቦች በዚህ መጽሐፍ ይገኛሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...