Prof. Fikre Tolossaፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ከአድራ ጋር ባደረጉት ክፍል ፪ ቃለምልልስ፤ ”ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኦሮሞዎች በጣም አርቀው የሚያስቡና፤ አገራቸው ኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነች የሚያውቁ ናቸው። እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው አሁንም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ተቻችለው፣ ተፋቅረው፣ በአንድነት የሚኖሩ ናቸው እንጂ፤ የሚለያዩ ወይንም የመገንጠል ሃሳብ ያላቸው አይደሉም” ሲሉ በኢትዮጵያ ስላሉ ኦሮሞች ይናገራሉ።

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ "የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ" በሚለው አዲሱ መጽሐፋቸው ዙሪያ ከአድራ ጋር በክፍል አንድ ያደረጉትን ጠለቅ ያለ ቃለምልልስ ባለፈው ማቅረባችን አይዘነጋም፤ (ክፍል አንዱን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ!)። በቃለምልልሱ በተለይ የኦሮሞና የአማራን ዘር ከስር ከመሰረት ምንጩን አብራርተዋል። እውነት አማራ የገዥ መደብ ነበርን? ለሚለው የብዙዎች ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ሙሉ ቃለምልልሱን ለማድመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!