የአቶ ሀብታሙ አያሌው የእስር ቤት ታሪኮች
የቀድሞው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጋር የእስር ቤት ታሪካቸውን አስመልክቶ ከጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። "አንድ እስረኛ ተመርምሮ ሲመለስ መጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም?" የሚል ነው - ከእስር የተለቀቁት አቶ ሀብታሙ አያሌው።
ቃለምልልሱ በሁለት ክፍል የቀረበ ሲሆን፣ ሁለቱንም ክፍሎች በዚህ ገጽ መጨረሻ ላይ ያገኙዋቸዋል።
የቀድሞው የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ቃል አቀባይ በሽብር ወንጀል ተከሰው እሥር ቤት በቆዩባቸው ሁለት ዓመታት በምርመራ ሳቢያ ደረሰብኝ ያሉት ከባድ ስቃይ አሁን ለሚገኙበት የጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ይናገራሉ።
ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ጭካኔ የተሞላባቸው ልዩ ልዩ የምርመራ ዓይነቶች በአብዛኞቹ እሥረኞች ላይ ሕልፈትን ጨምሮ ለተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንደሚዳርጉም አቶ ሀብታሙ ያስረዳሉ።
አቶ ሀብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት እንመክራለን። ለማዳመጥ የማጫወቃ ቁልፉን ይጫኑ!
ክፍል ፩
ክፍል ፪