ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በእንግሊዝ

“የንቅናቄያችን የእንግሊዝ አገር ስብሰባ ስኬታማ ውጤቶች” ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

ባለፈው ሳምንት መጠናቀቂያ አካባቢ በእንግሊዝ አገር ሪዲንግ ከተማ በአገራችን ስላለው ”የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የመሬት ነጠቃ እና የፖለቲካ መብቶች ረገጣ” የንቅናቄያችን የእንግሊዝ ንዑስ (chapter) የሁለት ቀን ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በተለይ በስብሰባው መጠናቀቂያ ላይ ከዚህ በፊት ጎራ ለይተው እርስበርስ በዘር፣ በዓላማ፣ በአካሄድ፣ በፕሮግራም ወዘተ የነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ቡድኖች - የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ክርስቲያኖች፣ እስላሞች፣ የአንድነት ደጋፊዎች፣ የነጻ አውጪ ግንባሮች፣ የትጥቅ ትግል ደጋፊዎች፣ የሰላማዊ ትግል አራማጆች፣ ወዘተ - በአንድ ቦታ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በስብሰባው መጠናቀቂያ ወቅት ሲተቃቀፉ፣ እርስ በርስ በፈገግታ ሲነጋገሩ እንዲሁም የግል መረጃዎቻቸውን ሲለዋወጡ መመልከቱ ብቻ የስብሰባውን ስኬት በግልጽ የሚያሳይ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፈጣን ምላሽ የሚጠይቅ የኅብረት ጥሪ

የህወሓት/ኢህኣዴግ መንግሥት ሥልጣን ከጨበጠበት ከ፩ሺ፱፻፰፫ ዓ. ም. (1991 አ.አ.) ጀምሮ የኢትዮጵያን ሀገራዊ ሉዓላዊነት እየሸረሸረና የሕዝቡን መብት እየረገጠ ፈላጭ ቆራጭ ሥርዓት ሆኖ መውጣቱ ዛሬ ከምንም ጊዜ የበለጠ ግልጽ ሆኗል። ያለፉት 19 ዓመታት የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ኢትዮጵያ ድንበርዋ እንዲደፈር፤ ህዝቧ በዘር እንዲለያይና እርስበርስ እንዲጣላ፤ የኢትዮጵያ መሬት በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለህብቶች ተሸንሽኖ እንዲሸጥ በአንጻሩ ደግሞ በርሃብ የሚጠቃው የሚሰቃየውና የሚሞተው ሕዝብ ቁጥሩ እንዲያሻቅብ የሆነበት፤ ብልጭ ብሎ የነበረው የዴምክራሲ ጭላንጭል የጠፋበት፣ ፍትኅ ጠፍቶ ዜጎች ሲዋከቡ ሲታሰሩ ሲደበደቡ ሲገደሉ ሲሰደዱ ዘወትር የምናይበት፤ የሀገሪቱ ሃብት በጥቂቶች፣ በሥልጣን ኮርቻ ላይ በጉልበት በወጡ አምባገነኖች እየተዘረፈ መሆኑን በየዕለቱ የምናይበት ዘመን ነው። (… ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ለሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ጉዳየኞች (Stakeholders) በሙሉ

ከለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተላለፈ ጥሪ

ሁላችንም እንደተከታተልነው በኢትዮጵያ ተካሄደ በተባለው ”ምርጫ” የመለስ ቡድን የ99.6% አብላጫ ድምጽ በማግኘት ”አሸንፌያለሁ” ማለቱ እንኳንስ ተቃዋሚዎችን የራሱ ደጋፊዎች አፍ ያስያዘና መልስ ያሳጣ ሆኖ ሰንብቷል።ከዚህ አኳያ ባለፈው ነገር ላይ ብቻ እያተኮርን ”ምንድነው ስህተታችን?” እያልን ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ ለነጻነታችን እና ለዘመናት በሰቆቃ ለሚኖረው ህዝባችን ምን ልናደርግ እንችላለን የሚለውን በመጠየቅ በቀጣይነት በጋራ ልናደርግ በሚገባን ነገር ላይ ውሳኔ መድረሱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።ይህንን አብሮ የመሥራትን እና የአንድነትን ነገር ሁሉም በየፊናው እያነሳ የሚወያይበት ዕለታዊ አጀንዳ እንደሆነ ከየአካባቢው ይሰማል። ወቅታዊው ጥያቄም ”ከሁሉ በፊት ነጻነታችን” የሚለው እንደሆነ ይደመጣል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሣት ነበልባል በሁሉ ሥፍራ ይንደድ!!

እኛ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ውስጥ የምንገኝ በቅድሚያ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት) መቋቋምን አስመልክቶ የተወሰደውን እርምጃ ከልብ የምናደንቅ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን። ይህ ታላቅ ራዕይ ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉትን የአማካሪዎች ቦርዱን፣ የፕሮግራም አዘጋጆችን፣ አርታኢዎችን እና በአጠቃላይ በኢሣት ሥራ ላይ ላለፉት ቀናትና ሣምንታት እንዲሁም ወራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይህ የቴሊቪዥን ጣቢያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ”ምርጫ” ከመደረጉ በፊት ተግባራዊ እንዲሆን ላደረጉት አስተዋጽዖና መስዋዕትነት ያለንን ታላቅ ምስጋና በከፍተኛ ወገናዊ ኩራት ለመግለጽ እንወዳለን። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት መርኅ ይከበር ከሚሉ አባላት የተሰጠ መግለጫ

“የአንድነት መርኅ ይከበር!” የሚሉት ወገኖች፤ “… በሃሳብ የተለዩ አባላትን የማስወገድና የማጥፋት ልክፍት የተጠናወተው የአንድነት ሥራ አስፈፃሚ ቡድን ለውይይት በሩን በመዝጋት ሕገወጥ ውሳኔዎችን እያሳለፈ ይገኛል …” በማለት በሦስት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ አውጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የተሰጠ ማብራሪያ

በ16/07/2001 ዓ.ም. በጀርመን ሬዲዮ የተላለፈውና በሌሎች የግል ጋዜጠኞች አንድነት ፓርቲ 21 የአመራር አባላት ከፓርቲው አግዷል የሚለው ዘገባ ፍፁም መሠረት የሌለው ሐሰት ዜና ነው። አንድነት በዲሞክራሲያዊና በደንባዊ አሠራር በጽኑ የሚያምንና የሚተገበር ፓርቲ ሲሆን፣ የአመራር አባላት መታገድ የብሔራዊ ም/ቤት ሥልጣንና ኃላፊነት መሆኑ በመተዳደሪያው ደንብ አንቀጽ 11.1 እና 11.4 በግልጽ አስቀምጧል። በአንድነት ፓርቲ የመተዳደሪያ ደንብ በብሔራዊ ም/ቤት ሥልጣንና ተግባር ሥር አንቀጽ 11.4 እንደሚደነግገው “የብሔራዊ ም/ቤት አባላት የዲስፕሊን ጉድለት መፈፀማቸው አግባብ ባለው አካል ሲረጋገጥ ም/ቤቱ በ2/3 ድምፅ ይሽራል” ይላል። በዚህ መሠረት በመደበኛ የአሠራር ሂደትና ዲስፕሊን ጉድለት ማንም አመራር አባላት ያለብሔራዊ ም/ቤቱ ውሳኔ ሊሻር ሊታገድ አይችልም። ስለዚህ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ከአንድነት ፓርቲ 21 ከፍተኛ አመራር ታገዱ የሚለው ትክክል ያልሆነ ሐሰተኛ ዜና መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው እንፈልጋለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...