ሦስቱ የኢሕአዴግ እኅት ድርጅቶችና የአምስቱ አጋር ድርጅቶች ሊቃነመናብርት ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘው

ሦስቱ የኢሕአዴግ እኅት ድርጅቶችና የአምስቱ አጋር ድርጅቶች ሊቃነመናብርት ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘው

ከሕወሓት በስተቀር በኢሕአዴግ ጥላ ሥር የነበሩት ስምንት ፓርቲዎች ውሕደቱን ፈጽመዋል

ኢዛ (እሁድ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 1, 2019)፦ የኢሕአዴግ ሦስት እኅት ድርጅቶችና በአጋርነት የሚታወቁት አምስቱ ድርጅቶች ሊቃነመናብርት የብልጽግና ፓርቲን ውሕደት ስምምነት በፊርማቸው አረጋግጠዋል። ከሕወሓት በስተቀር በኢሕአዴግ ጥላ ሥር የነበሩ ድርጅቶች የብልጽግና ፓርቲ ስምምነት ፊርማቸውን ያኖሩት ዛሬ ነው።

እሁድ ኅዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ውሕደቱን ያጸደቁት እነዚህ ፓርቲዎችን በመወከል አዲሱን ፓርቲ መቀላቀላቸውን የሚያረጋግጠውንና የብልጽግና ፓርቲን የሚመሠርቱበትን ስምምነት የፈረሙት የኢሕአዴግ እኅት ድርጅቶች መሪዎች ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አቶ ደመቀ መኮንን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው።

የምሥረታውን ስምምነት የፈረሙት የኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶች ሊቃነመናብርት ደግሞ፤ ከሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) አቶ አሕመድ ሺዴ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉሕዴፓ) አቶ አድጎ አምሳያ፣ ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ ከጋምቤላ ሕዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) አቶ ኡሙድ ኡጁሉ፤ እንዲሁም ከሐረሪ ብሔራዊ ሊግ (ሐብሊ) አቶ ኦርዲን በድሪ መኾናቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ