የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

በአገሪቱ ያለውን ችግር አስወግዶ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያግዛል ተብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 2, 2020)፦ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን ችግር አስወግዶ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያግዛል የተባለው የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተሰናዳው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ።

ለወራት ሲመከርበት የነበረውና የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ የጸደቀው ዛሬ ታኅሣሥ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው።

በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የፍትሕ አካላት፣ ከሕዝብና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዝርዝር ውይይት ተደርጐበት ጭምር የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ፤ በምክር ቤቱም ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ መጽደቁ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ