Ethiopian Parliament

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አነጋጋሪ ኾነው የቆዩትን ሁለት አዋጆች ያጸድቃል ተብሏል

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 12, 2020)፦ ባለድርሻ አካላትን በእጅጉ ሲያሟግቱ የነበሩት ሁለት ረቂቅ አዋጆች በጥምረት ነገ በአስቸኳይ ስብሰባ በተጠራው ፓርላማ ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃሉ። በደንቡ መሠረት ፓርላማው እረፍት የሚወጣበት ጊዜ ነበር።

እነዚህ ሕጎች በረቂቅ ደረጃ ብዙዎችን ሲያሟግቱ የቆዩት የኤክሳይዝ ታክስና የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጡት ረቂቅ አዋጆች ናቸው።

ረቂቅ አዋጆቹ በባለድርሻ አባላትና በፓርላማው ጭምር በተለያዩ ጊዜያት ውይይት የተደረገባቸውና ብዙ ክርክሮች የተደረገባቸው ቢኾንም፤ በነገው ዕለት እንደሚጸድቁ ተነግሯል።

በነገው የፓርላማ ውሎ ሌሎች ረቂቅ አዋጆች ላይም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎም ይጠበቃል።

ፓርላማው ከአንድ ሳምንት በፊት በምክር ቤቱ የአሠራርና አባላት ሥነምግባር ደንብ መሠረት፤ ከየካቲት 1 እስከ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ምክር ቤቱ ለእረፍት እንደሚዘጋ አስታውቆ ነበር። ነገር ግን እነዚህን አዋጆች ለማጽደቅ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ