በትግራይ ክልል የባንክ ቅርንጫፎች እየተዘረፉ መኾኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (በግራ)፣ ሕወሓት (በቀኝ)
ብሔራዊ ባንክ ቅርንጫፎቹ ተዘግተው ይቆዩ ብሏል
ኢዛ (እሁድ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 8, 2020)፦ በሕወሓት ውስጥ ያለው ቡድን በክልሉ በሚገኙ ባንኮች ላይ ዘረፋ እየፈጸመ መኾኑንና አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ ክልል ያሉ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ ተዘግተው እንዲቆዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ እሁድ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፤ ዘረፋው የሕወሓት ቡድን በባንኮች ቅርንጫፎች ላይ ዘረፋ እየተፈጸመ በመኾኑ፤ የትግራይ ሕዝብና የሚመለከታቸው አካላት ባንኮቹ እንዳይዘረፉ የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድም ጥሪ አስተላልፏል።
አሁን ባለው ሁኔታም በትግራይ ክልል ያሉ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት የማይችሉ በመኾኑ ተዘግተው እንዲቆዩ የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል። (ኢዛ)



